TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#updateሀዋሳ የኢህአዴግ ጉባኤ⬇️

ኢህአዴግ በ11ኛው ጉባኤው #በርዕዮተ_ዓለም ለውጥ ላይም ሆነ በአርማ ለውጥ ላይ #እንደማይወያይ ተገልጿል። የጉበኤውን ውሎ በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የጉባኤው ቃል አቀባይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንደገለፁት ጉባኤው አጀማመሩ ያማረና ከሌላው ጊዜ በበለጠ በርካቶችን ያሳተፈ ነበር ብለዋል።

የተፎካከሪ ፓርቲዎች መሳተፍ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓና የእስያ ሀገራትን የወከሉ የፓርቲ አመራሮችም በመክፈቻው መገኘታቸው ጉባኤውን #ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

ጉባኤው ከመክፈቻ ፕሮግራሙ በኋላ በጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ የቀረበለት ሪፖርት ላይ መወያየቱን እና ይህ በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

ጉባኤው በቆይታው የሚመክርባቸው በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም በርዕዮተ ዓለም ለውጥም ሆነ በስምና አርማ ለውጥ ላይ እንደማይመክር ግን ቃል አቀባዩ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia