በረራው ተቋርጧል‼️
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ40 ዓመት በኃላ ወደ ሶማሊያ #ሞቃዲሾ ጀምሮት የነበረውን በረራ #ማቋረጡን ሸገር FM ዘገበ።
ተጨማሪ፦ ከትናንት በስትያ ዜግነቱ እንግሊዛዊ የሆነ ግለሰብ ከሞቃዲሾ ወደ አዲስ አበባ የሚመጣ በረራ ላይ #ተቀጣጣይ ነገር ይዞ ሊገባ ሲሞክር በኤርፖርት ጥበቃዎች #ተይዟል። #ከአልሽባብ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል ተብሎም ተገምቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ #ላልተወሰነ ጊዜ በረራውን አቋርጧል ሲል ሸገር ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ዘግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ ' እስካሁን ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ እናመሰግናለን ' ብለው ከስራ አስቆሙን ”- የአል ዓይን አማርኛ ጋዜጠኛ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) ሚድያ እንደሆነ የሚነገርለትና መቀመጫውን በአቡዳቢ ከተማ ያደረገው አል አይን ዲጂታል ሚዲያ፣ ላለፉት 6 አመታት የቆየውን የአማርኛ የአገልግሎት ማቋረጡን ጋዜጠኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል፡፡
የአል አይን ኒውስ ዲጂታል ሚዲያ፣ በ2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ ቢሮ በመክፈት በ7 ጋዜጠኞች የአማርኛ ዜና አገልግሎት መጀመሩን እና በሒደት ደግሞ ሌሎች ጋዜጠኞችን ቀጥሮ ሥራውን ሲያከናውን እንደቆየ ነግረውናል፡፡
በዚሁ የአዲስ አበባ ቢሮ፣ 7ዲ ለሚባል እህት የዜና ተቋም በእንግሊዚኛ ቋንቋ ከኢትዮጵያ የሚዘግቡ ሁለት ጋዜጠኞችም ተቀጥረው እንደነበረ የገለፁት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ በአረብኛ የሚሰሩ 4 ጋዜጠኞችም ነበሩት ብለዋል፡፡ ሆኖም፣ ብዙም ሳይቆይ የእንግሊዝኛው አገልግሎት መቋረጡን ጠቅሰዋል፡፡
በድምሩ በ13 ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረው አል ዓይን ኒውስ ዲጂታል ሚዲያ፣ ከ2 አመት በፊት፣ በስሩ ከነበሩት ሰራተኞች አምስቱን መቀነሱንና ቦሌ አካባቢ የነበረውንም ቢሮ ዘግቶ፣ የተቀሩት ጋዜጠኞች ከቤታው ተቀምጠው እንዲሰሩ መወሰኑን ገልፀዋል፡፡
አሁን ደግሞ የቀሩትን 5 ጋዜጠኞች አሰናብቶ፣ የአማርኛ አገልግሎቱን #ማቋረጡን ነው የሚገልፁት፡፡
ማንነቱ እንዳይጠቀስ በመጠየቅ አስተያየት የሰጠን አንድ ጋዜጠኛ፣ “ ከሦስት ቀን በፊት ጀምሮ እየሰራን አይደለንም፣ ካለፈው ዕሮብ መጋቢት 10 ቀን2017 ዓ.ም ጀምሮ ስራ እንድናቆም ተነግሮናል ” ብሏል፡፡
የአል አይን ሚዲያ ጋዜጠኛው በዝርዝር ምን አለ ?
“ ስራችንን እንድናቆም በኢሜይል ነው የተነገረን፡፡ ' ከእኛ ጋር የነበራችሁ የሥራ ኮንትራት ውል ከዛሬ ጀምሮ ተቋርጦዋል፣ እስካሁን ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ አድናቆት አለን፣ እናመሰግናለን ' ይላል የደረሰን
መልዕክት፡፡ ቢያንስ በቅድመ ማስጠንቀቂያ የመዘጋጃ ጊዜ ሰጥተው ቢያስቆሙን ጥሩ ነበር፡፡
ድንገት ነው ከስራ ያስቆሙን፡፡ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ መልዕክት፣ የስራ ውላቸውን በማቋረጥ ከስራ ያስቆማቸው ሰራተኞች ነበሩ፡፡ ሚዲያው፣ ሰራተኛ የመቀነስ ዕቅዱን ያኔ ያጠናቀቀ መስሎን ነበር፡፡
በመጨረሻ ግን ሁላችንንም አስቁሞ፣ የአማርኛ ዜና አገልግሎቱን ዘግቷል፡፡ በአብዛኛው በአማርኛ ዜናዎችን እንሰራ ነበር፣ ለአረቡ አለም አድምጭ የሚሆን አርዕስት ሲኖር ደግሞ ወደ አረብኛው አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
የአማርኛው የዜና አገልግሎት መረጃዎችን በመስጠት ረገድ ስኬታማ ነበር፣ ከሐላፊዎቹ ተደጋጋሚ የሆነ አድናቆትም ይደርሰን ነበር፣ በደብዳቤም ጭምር፡፡ በይዘትም በጥራትም የተሻሉ ስራዎች ሲተላለፉበት እንደነበረ ሲመሰክሩ ነበር፡፡ ከአል ዓይን አረብኛ እና ከአል አይን ፈረንሳይኛ በተሻለ አማርኛው
የበለጠ ይታይ ነበር፡፡
በዚህም ሐለፊዎቹ ደስተኞች ነበሩ፡፡ ይህን ሲታይ ሚድያውን ዘግተው ስራ ያስቆሙናል ብለን አልጠበቅንም፡፡ ድንገት ይዘጉታል የሚል ግምት አልነበረንም፡፡
የሆነ ሰዓት ላይ፣ ከአማርኛው በተጨማሪ፣ በኦሮሚኛ፣ ትግርኛ እና ሶማሊኛ ቋንቋዎች የዜና አገልግሎት ለመጀመር እቅድ እንደነበራቸው እናውቃለን፡፡ እነዚህን ቋንቋዎች እንደሚጀምሩም ጠብቀን ነበር፡፡ ” ብሏል።
ለሚድያው መዘጋት ምክንያቱን መገመት ይችል እንደሆነ ላቀረብንለት ጥያቄ፣ ጋዜጠኛው “ በእውነቱ አላውቅም፣ እሱን መገመት በጣም ከባድ ነው ” የሚል አጭር መልስ ሰጥቷል፡፡
ማንነቴ እንዳይገለፅ ብሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየት የሰጠ በዚሁ ሚድያ ሲሰራ የነበረ ሌላ ጋዜጠኛ፣ “ ለመዘጋቱ ምክንያት የሚሆን ነገር በትክክል አላውቅም፣ የግብፆች እጅ እንዳለበት ግን እገምታለሁ ” ብሏል፡፡
ጋዜጠኛው በሰጠው አስተያየት ምን አለ ?
“ ለአማርኛው አገልግሎት መዘጋት ምክንያት የሚመስለኝ ግብፆች ናቸው፡፡ የአል ዓይን ሐላፊዎች ለግብፅ ያደሉ ነበር፡፡ ሚድያው ከዛም የዜና አገልግሎት ስለሚሰጥና በግብፅም ቢሮ ስላለው፣ እዛ ያሉት አርታእያን በእኛ ላይ ተፅዕኖ ሲያሳሩብን ነበር፡፡ ለአንድ ገለልተኛ ሚድያ ሳይሆን ለኢትዮጵያ የምንሰራ ነበር የሚመስላቸው፡፡
ለሚድያው ሳይሆን ለሀገራችን እየሰራን እንዳለን አድርገው ይቆጥሩናል፡፡
በህዳሴ ግድብ ዘገባዎቻችን ላይ በጣም ነበር የምንከራከረው ከእነሱ ጋር፡፡ ዜናዎቻችን ላይና ስራዎቻችን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሲያሳድሩ ነበር፡፡ በግብፅ ያለው ቢሮ እና ጋዜጠኞቹ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ናቸው፡፡
አሁን የኢትዮጵያው ቢሮ ሲዘጋ፣ የግብፅ ግን አልተዘጋም፡፡ የኢትዮጵያ ቢሮ እንዲዘጋ ግብፆች ግፊት አድርገው ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው የምገምተው፡፡ ” ሲል ተናግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በግብፆች ላይ የቀረበውን ክስ በተመለከተ ከተቋሙ ምላሽ ካገኘ ወደፊት የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
አልአይን ኒውስ ዲጂታል ሚድያ፣ አይ ኤም አይ በሚባል ካምፓኒ ስር የሚንቀሳቀስ ተቋም እንደነበረ ጋዜጠኞቹ ተናግረዋል፡፡
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤234😭103🤔29😢17👏16🙏13🕊9🥰8😡4😱1