TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Fana Live🔝

የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አሮፕላን አደጋው #መንስኤ ቅድመ ሪፖርት በአሁን ሰዓት ይፋ እየተደረገ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውሮፕላን ተከሰከሰ👆

በጅማ ዞን ኦሞ ቤየም ወረዳ በአቢሲኒያ ፍላይት መለማጀማ አውሮፕላን ላይ #መከስከስ አደጋ መድረሱ ተገለፀ። የአቢሲኒያ ፍላይት ሰርቪስ የፕሮጀክት ማናጀር አቶ #አሸናፊ_ፀጋዬ ለfbc እንዳስታወቁት፥ አደጋው በዛሬው እለት ጠዋት ላይ ጎና ቤየም በሚባል ቀበሌ አሰንዳቦ አካባቢ ነው የደረሰው።

በአውሮፕላኑ ላይ የመከስከስ አደጋው የደረሰው አንድ ተለማማጅ የአውሮፕላን አብራሪ በማብረር ላይ እያለ መሆኑንም አስታውቀዋል። የመከስከስ አደጋው የደረሰበት አውሮፕላን “C 172” ሞዴል ሲሆን፥ አራት መቀመጫዎች ያሉት ነው ብለዋል አቶ አሸናፊ።

በአሁኑ ወቅትም የአደጋውን የጉዳት መጠን እና #መንስኤ ለማጣራት የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንም አስታውቀዋል። ወደ ስፍራው የተጓዘው የባለሙያዎች ቡድን ወስጥም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የፍለጋ እና የነብስ አድን ሰራተኞች እና የአቢሲኒያ ፍላይት የደህንነት አባላት የተካተቱበት ነው።

የአደጋው መንስኤም እስካሁን አለመታወቁን እና በመጣራት ላይ መሆኑንም የአቢሲኒያ ፍላይት ሰርቪስ የፕሮጀክት ማናጀር አቶ አሸናፊ ፀጋዬ ተናግረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia