TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥንቃቄ

(በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀረበ)

ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ምንድነው ?

ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ስልካችን ላይ ከማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፆች በምንጭናቸው መተግበሪያዎች አማካኝነት ወደ ስልካችን ሰርጎ የሚገባ ሲሆን እንደ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ፣ የመሳሰሉ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ጥቃትን የሚሰነዝር
#መተግበሪያ ነው፡፡

ጉዳቱ ምንድነው ?

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመረጃ ሥርዓት ደህንነት ክፍል ፋርማ ፕላስ (Pharma+) የተሰኘውን
መተግበሪያ ጉዳት አምጪ እንደሆነ ገልጿል።

ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ከማህበራዊ ትስስር ገጾች አውርደን በምንጭናቸው ሌሎች መተግበሪያዎች ጋር በመለጠፍ ወደ ስልካችን ሰርጎ በመግባት ፦
- የስልካችንን ስክሪን ማየት፤
- አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን ማንበብ፣
- ሀሰተኛ የመግቢያ ገጾቸን በማዘጋጀት
- የይለፍ ቃሎችን መመንተፍ እና የመሳሰሉ የግል መረጃዎችን የሚሰርቅ
መተግበሪያ ነው፡፡

የፋይናንሻል ግብይቶችን ከተጠቂው እውቅና ውጪ መፈፅሙ እና ስልካችን ላይ ተጭነው ካሉት መተግበሪያዎች ውስጥ መደበቁ ማየት ስለማንችል ለመከላከል በጣም አዳጋች ነው።

እንዴት ራሳችንን ከፋርማ ፕላስ (Pharma+) እንጠብቅ ?

➡️ ካልታመኑ ምጮቾች ማንኛውንም
መተግበሪያ ስልኮት ላይ አይጫኑ፤
➡️ በማህበራው ገጽ አማካኝነት የሚላክሎትን ማንኛውንም ማስፈንጠሪያ ወይም
መተግበሪያ ምንነቱን ሳያረጋግጡ አይክፈቱ፤
➡️ ብቅ ባይ (Pop up) ማስታወቂያዎችን ወይም አጠራጣሪ ገጾችን በፍጹም አይክፈቱ፤
➡️ እንደ ጎግል ፕሌይ፣ አማዞን፣ አፕስቶር ወይም ሳምሰንግጋላክሲ ስቶር ጥብቅ የደህንነት ፍተሻዎችን የሚያደርጉ ይፋዊ የመተግበሪያ ማከማቻዎችን ብቻ ይጠቀሙ።

ትክክለኛ የስልክ መተግበሪያዎችን በመጠቀም እራስዎትን ይጠብቁ።

(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

@tikvahethiopia
61.25K🙏716👏120😭50😡48😢44🕊43🤔31🥰28😱20