TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን " - ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ

ጎረቤት ሀገር ኬንያ በትምህር ቤቶች ውስጥ ተንሰራፍቷል ያለችውን " የተመሳሳይ ጾታ " አጀንዳ ላይ ዘመቻ መጀመሯ ታውቋል።

የኬንያ የትምህርት ሚንስትር ኢዚኬል ማቾጉ ፥ " በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች አጀንዳ ሰርጎ ገብቷል " ሲሉ ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተናግረዋል።

ሚንስትሩ በት/ ቤቶች ውስጥ " የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳን " ለማስቀረት በኬንያ አንጀሊካን ቤተ-ክርስቲያን የሚመሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ይሾማሉ ብለዋል።

በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው #መማሪያ እና #አጋዥ_መጽሐፍትን መከለሰን ሊያካትት እንደሚችል ትምህር ሚንስትሩ ገልጸዋል።

ይህ የኬንያ ትምህርት ሚንስቴር እቅድ የተሰማው ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ " የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አደጋ ፈጥሯል " በማለት በመላው ኬንያ #ጸሎት_እንዲደረግ ካወጁ በኋላ ነው።

የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ቤተሰብ በሚባለው ተቋም ላይ አደጋ ደቅኗል " ብለዋል።

ቀዳማዊት እመቤቷ ፤ " አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአፍሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት የለውም። የቤተሰብ እሴቶችን እንጠብቅ " ብለዋል።

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ኬንያ ውስጥ #ሕጋዊ_አይደለም

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ አመለካከቶች ባለፉት ቀናት ጠንከር ብለው መታየታቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል (ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ)

@tikvahethiopia
👍2.85K149🙏93😢52👎38🤔19🥰17😱17🕊15