TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰኞ ሀምሌ 7/2017 ዓ.ም በትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ሁለት እንስቶች አሲድ ተደፍቶባቸው ጉዳት እንደደረሰባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል። ለጊዜው ስሙ ይፋ ያልተደረገ አንድ ግለሰብ በከተማዋ በሚገኘው አንድ መጠጥ ቤት በሚሰሩ ሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ከባድ የአካል ጉዳት አድርሶባቸዋል። ድርጊቱ በርካቶችን አስደንግጧል። የተፈጠረው ምንድነው ? በማለት ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ…
#Update

በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት አረሜናዊ ድርጊት የፈፀመው ተጠርጣሪ " እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም " ሲሉ የትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

" አሲድ የተደፋባቸው ወገኖች በከፍተኛ ስቃይ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ አክለዋል።

አሲድ የተደፋባቸው እንስቶቹ ለተሻለ ህክምና ከእንዳስላሰ - ሽረ ወደ አክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ሪፈር መባላቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው ሀምሌ 7/2017 ዓ/ም እስካሁን ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአንድ መጠጥ ቤት በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ማድረሱ ይታወሳል።

የድርጊቱ ፈፃሚ ግለሰብና ?  አስቃቂ ተግባር የተፈፀመባቸው እንስቶች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ለማጣራት ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ኣባል ዛሬ ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ ከተማዋ ፓሊስ ስልክ ደውሎ ነበር።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የከተማዋ ፓሊስ አመራር " በአካል ወደ ከተማችን ካልመጣችሁ በስቀር በስልክ መረጃ አንሰጥም " በማለት መረጃውን ከልክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማዋ ነዋሪ ከሆኑ ታማኝ ምንጮቹ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጭካኔ ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ የሚታወቅ የከተማዋ ነዋሪ ሆኖ እያለ እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋሉ ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል።

" ተጠርጣሪ ወንጀለኛው እስካሁን በከተማዋ ተደብቆ እንደሚገኝ የሚሰሙ ጭምጭምታዎች አሉ " ያሉት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ፤ ፓሊስ የጭካኔ ድርጊቱ የፈፀመው ግለሰብ አድኖ በመያዝ ህግ እንዲያስከብር አደራ ብለዋል።

የከተማዋ ነዋሪ ተጥርጣሪውን ለፓሊስ አሳልፎ በመስጠት ዜግነታዊ ሃላፊነቱ እንዲወጣም ነዋሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የእንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ፓሊስ ለሚድያ የሚፈቀድ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር እየጠየቀ ጉዳዩ ተከታትሎ መዘገቡ እንደሚቀጥል ቃል ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia
556😢157😭104😡60🙏19🕊15💔14🤔7😱6👏5🥰4