TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የጤናባለሙያዎችድምጽ

° “ የ3 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተሰጠንም ” - የጤና ባለሙያዎች

° “ ለጉዳዩ ምላሽ መስጠት ያለበት ወረዳው ነው ” - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ

° “ የጀበት ችግር ገጥሞን ነው ” - የኪንፋዝ በገላ ጤና ጽ/ቤት
  

በአማራ ክልል፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኪንፋዝ በገላ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች ከሚያዚያ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ፣ “ የ3 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተሰጠንም። ስንጠይቃቸውም ‘ አንከፍልም ’ ነው የሚሉት ” ብለው፣ ክፍያው እንዲፈጸምላቸው ጠይቀዋል።

የቅሬታ አቅራቢዎቹ ብዛት ከ30 በላይ እንደሆነ፣ የክፍያ መጠኑ እንደዬደረጃቸው እንደሚለያይ ገልጸው፣ ይህ ቅሬታ የተፈጠረው ፦ 
- በስላሬ 
- በጭቅቂ 
- በሮቢት በገላ በተሰኙ 3 የወረዳው ጤና ጣቢያዎች መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች የጤና ኤክስቴንሽን፣ ጤና ሙያተኞች ደህንነታችን ዋስትና ሳይሰጠው ‘ የክትባት ዘመቻ ካልዘመታችሁ ’ እየተባልን በስጋት ውስጥ ነው ያለነው ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎቹን ቅሬታ ይዞ የዞኑን ጤና መምሪያ አነጋግሯል።

ለምን ብራቸውን አትከፍሏቸውም ? ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ ፤  “ለጉዳዩ ምላሽ መስጠት ያለበት ወረዳ ነው። በወረዳው በጀት ዞን ጤና መምሪያው የሚመለከተው ስላልሆነ ” ብሏል።

ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ገ/ህይወት በሰጡት ቃል፣ “ የበጀት እጥረት ገጥሞን ነው ” ብለዋል።

ታዲያ ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግራችሁ ነበር ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ በሚቀጥው በአዲሱ በጀት ተይዞ ይከፈላቸዋል ” ነው ያሉት።

“ ለዚህም ደግሞ አስተዳደሩ ደብዳቤ ጽፏል። ‘በቀጣይ እከፍላለሁ’ የሚል ” ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ባለሙያዎቹ ' የጸጥታ ችግር ባለበት ለክትባት ውጡ ተብለናል ' የሚል ቅሬታ አላቸው፤ ለመሆኑ ይህን ስታደርጉ ለደህንነታቸው ከለላ ታደርጉላቸዋላችሁ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ኃላፊው በምላሻቸው፣ “ የጸጥታ ችግር የሌለበት የለም። ዞሮ ዞሮ ግን በሚቻለው አግባብ የአገር ሽማግሌዎችን ይዘን እንሰራለን ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😢13957😡21🕊9😭8🙏5😱3🥰2👏2🤔2
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የጤናባለሙያዎችድምፅ " ከ15 ወራት በላይ የዱቲ ገንዘብ አልተከፈለንም በዚህ ኑሮ ውድነት በብድር በዬ ወሩ ተሰቃየን " - ጤና ባለሙያዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ15 ቀናት የዘመቻ አበልና ከአንድ አመት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመፈጸሙ ችግር ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የጤና ባለሙያዎቹ ዝርዝር ቅሬታ ምንድን ነው…
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

🔵 " ቸግሮናልጠምቶናል፣ ርቦናል፣ ሰልችቶናል፣ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ የዱቲ ሳይከፈለን ለ17 ወራት ስንሰራ ከመንግስት አካል ማንም ያሰበን የለም " - ጤና ባለሞያዎች

🔴 " ምንም ምላሽ የለንም። ቢሮ መጥተው ይጠይቁን " - ወናጎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት

በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ያሉ ጤና ባለሙያዎች የወራት ያልተከፈለ የዱቲ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው በመጠየቃቸው ከደመወዛቸው እንዲቆረጥባቸው መወሰኑን በመግለጽ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

" ዱቲ ስላልከፈሉን የሰራነውን ገንዘብ ስለጠየቅን ብቻ ከሦስት ወራት በላይ ደሞዛችን ከ960 ብር ጀምሮ በስኬል  እየተቆረጠ ይገኛል " ብለው፣ ደመወዛቸው እንዲቆረጥ የተወሰነው የዱቲ ሥራ በማቆማቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የዱቲ ሥራ በመቆሙ ህዝቡም ችግር ላይ ስለሆነ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀው፣ " ካልሆነ ለሚፈጠር ችግር ተጠያቂ አንሆንም " ሲሉ አስጠይቅቀዋል።

በዞኑ ዲላ ዙሪያ ወረዳ ጪጩ ጤና ጣቢያ ያሉ ባለሙያዎቹ በበኩላቸው፣ የ17 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ያማረራቸውን ቅሬታ በተመለከተ በዝርዝር ምን አሉ ?

" በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የ17 ወራት የዱቲ ክፍያ ባለመከፈሉ የጪጩ ጤና ጣቢያ ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የዱቲ ሥራ በማቆም ሕዝቡ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል።

በተደጋጋሚ ለዞኑና ለወረዳው ቅሬታ ብናቀርብም ምላሽ በመስጠት ፈንታ ባለሞያዎችን ለእስር ሲዳርግ ቆይቷል። ለሦስት ዓመት ያክል በዱቲ ክፍያ እየተከራተተ የሚገኝ የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሞያ እስከ ዛሬ ተገቢ ምላሽ አላገኘም።

በጌዴኦ ዞን በወናጎ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሞያዎች የዱቲ ጥያቄ አቅርበው ተገቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው መብታቸው ለማስከበር የዱቲ ሥራ በማቆማቸው በየወሩ ከደሞዛዝ እንዲቆረጥ ተወስኗል።

ዱቲ ስላልከፈሉን የሰራነውን ገንዘብ ስለጠየቅን ብቻ ከሦስት ወር በላይ ደሞዛችን ከ960 ብር ጀምሮ በየወሩ እየተቆረጠ ይገኛል። መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን።

ቸግሮናል፣ ጠምቶናል፣ ርቦናል ሰልችቶናል ሞራላችን ተነክቷል መውጫ ቀዳዳ አሳጥቶናል ከኑሮ ውድነት ጋር የዱቲ ሳይከፈለን ለ17 ወራት ስንሰራ ከመንግስት አካል ማንም ያሰበን የለም " ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቀው የወናጎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ቀጥተኛ ማብራሪያ በመስጠት ፋንታ፣ " ምንም ምላሽ የለንም። ቢሮ መጥተው ይጠይቁን " ብሏል።

ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስልክ ለማሳት ፈቃደኛ ባይሆኑም የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ ከዚህ ቀደም ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡትን ምላሽ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸውልን ነበር።

"ጉዳዩ በእርግጥ ያለ ነው። መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው። ያን ለመፍታት በጋራ እየሰራን ነው" የሚል ቃል ነበር የሰጡን።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭580😡10578😢44🙏23🕊19👏6🥰5🤔4😱4
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ

🚨“ የሐምሌ 2016 ዓ/ም ደመወዝና፣ የ23 ወራት የዱቲ ክፍያ ስላልተከፈለን የዱቲ ሥራ ለማቆም ተገደናል” - የሀላለ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች

🔴 “ የ23 ወራት ባይሆንም የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈላቸውም ” - ሆስፒታሉ

🔵 “ የአንድ ወይም ሁለት ወራት እንጂ የዚህን ያክል የተወዘፈ ክፍያ የለም ” - የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ

በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሀላለ ሆስፒታል የሚገኙ 78 ጤና ባለሞያዎችና ሌሎች ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዝና የ3 ዓመት የዱቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው የትርፍ ሰዓቱን ሥራ ለማቆም መገደዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ጤና ባለሞያዎቹ በሰጡን ቃል ምን አሉ?

“መንግስት ከሚመድበው በጀት ክፈሉ ብለን በደብዳቤ ብንጠይቅም ‘እንከፍላለን አሁን ግን የካሽ እጥረት አለብን’ አሉን። ከዚህ ባለፈ ማስፈራሪያ፣ እስራት፣ ድብደባ ይደርስብናል።

የመጀመሪያ የስምነት ወራት የዱቲ ክፍያ በተመለከተ ተካስሰን ፍርድ ቤት እንዲከፈለን ውሳኔ ቢሰጠንም በፖለቲካ ሰዎች ጣልቃ ገብነት ውሳኔ ባለመከበሩ አልተከፈለንም።
 
ከዚያ ወዲህ የሰራነውን የ15 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያንም ቢሆን ባለመክፈላቸው፣ ለመክፈልም ፍላጎት የሌላቸው በመሆኑ ከሆስፒታሉ ሠራተኞች ኃላፊ ውጪ በአጠቃላይ ተፈራሪመን የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማቆም ተገደናል።

በደላችንን፣ ድምፃችንን ለህዝብ እና ለመንግስት አሰሙልን። ጤና ሚንስቴር በህይወት ካለ መብታችንን ያስከብርልን” ሲሉ አሳስበዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የአንድ ወር ደመወዝና የ23 ወራት ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ያልተፈጸመበት ምክንያት ምንድን ነው? ሲል ለሆስፒታሉ ጥያቄ አቅርቧል።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ በረከት ሌራ ምን ምላሽ ሰጡ?

“የኛ ተቋም የሚያስተዳድረው ገንዘብ የለም ስራዎች ከተሰሩ በኋላ ለወረዳ ፋይናንስ ሪፓርት ቀርቦ ያንን መሠረት በማድረግ ነው ክፍያ የሚፈጸመው። 

የ2016 ዓ/ም የሐምሌ ደመወዝ 13% ብቻ ነው የሚቀረው 87% ተከፍሏል። የ23 ወራት ባይሆንም የ20 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ሰፊ ነው ችግሩ። የካሽ እጥረት በሚል ብዙ ነገር እየተባለ ነበር።

የዱቲ ክፍያ በተመለከተ ፍርድ ቤት ክፍያ እንዲፈጸም የሚል ውሳኔ ሰጥቷል። የወረዳው መንግስት ከክስ ሂደቱ በኋላ መክፈል ከጀመረ በኋላ ነው የቆመው።

‘በንግግር ችግሮችን እየፈታን እንመጣለን’ በሚል ቃል ከተገባልን በኋላ ነው በመካከል ክፍያው የቆመው።  የሚያዚያ ወር በከፊል መከፈል ከተጀመረ በኋላ ነው ቆመ”
ብለዋል።

የዱቲ ሥራ በመቆሙ በማታ የሚመጡ ወላድ እናቶችን ብቻቸውን እያከሙ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፣ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ባለሙያዎቹ የ23 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ቅሬታ አቅርበዋል፣ ሆስፒታሉም የ20 ወራት የዱቲ፣ የሐምሌ ደመወዝ 13 በመቶ ክፍያ አለመፈጸሙን ገልጿል፣ ይህ ለምን ሆነ? ጉዳዩን ተመልክታችሁት ነበር? ስንል ለወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ጥያቄ አቅርበናል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ምን አለ?

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ፣ “የ23 ወራት እንዳልተከፈለ መረጃው የለኝም። ተከፍሎ ነው እየተሰራ ያለው። ትክክል ነው ለማለት እቸገራለሁ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥተዋል።

የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ሆስፒታሉም እንዳረጋገጠ ስንገልጽላቸውም፣ “20 ወራት አይደርስም እኔ እንደማውቀው። ማጣራት ይጠይቃል” ነው ያሉት።

“የአንድ ወይም ሁለት ወራት እንጂ የዚህን ያክል የተወዘፈ ክፍያ የለም” ያሉት ኃላፊው፣ ጉዳዩን አጣርተው ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ሆስፒታሉ ያልተከፈላችሁ የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ መሆኑን ገልጿል፣ እናንተ ደግሞ ያልተከፈላችሁ የ23 ወራት እንደሆነ ገልጻችኋል ፣ የትኛው ነው ትክክል ? ስንል የጠየቅናቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ከ23 ወራት የዱቲ የ3 ወሯን ለተወሰኑ ሰዎች ነበር የከፈሉት። በትምህርት፣ በዝውዝውር፣ ሥራ በመልቀቅ ሄዱት ሳይከፊሉ ነው ‘ከፍለናል’ የሚሉት ነገር ግን እነዚህ ባለሙያዎች ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ህብረተሰቡን እንዳገለገሉ መረሳት አልነበረበትም ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭583194😡81🙏64🕊28😢25👏21🤔17🥰6😱2
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ

“ ማንም መልስ የሰጠን የለም። ችግሮቹም ከቀን ወደ ቀን እየተባበሱ ነው ” - የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር

የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር፣ “ በተለያዩ በሽታዎች ተይዘው ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሀኪሞቻችን ተገቢውን ህክምና በፍጥነት ባለማግኘታቸው የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ ” ሲል ወቅሷል።

ማኀበሩ ይህን ያለው፣ ከየካቲት 14 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ/ም ስለሚያካሂደው 61ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባዔ በተመለከተ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

ጉባኤው፣ “ በኢትዮጵያ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች ደህንነት አሁናዊ ሁኔታና አማራጭ መፍትሄዎች ” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ አመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለሀኪሞች ህክምና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ምን እንደሚመስል፣ ለኢትዮጵያ ሀኪሞች ምን መደረግ እንዳለበት ማኀበሩን ማብራሪያ ጠይቋል።

የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት፣ በሰጡት ምላሽ “ በብዛት በኢንሹራስ ከቨር የሚደረግበት ሁኔታ አለ በጥናት የተደገፈ መረጃ ባይኖርም የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በተመለከተ ” ብለዋል።

አክለው፣ “ የኛ አገርን በተመለከተ የኢንሹራንስ ከቨርም ስለማይደረግ ጤና ባለሙያዎች እንደማናቸውም ማኀበረሰብ በትንሽ በሀገር ታክመው የማይዳኑ በጣም የተወሳሰቡ ህመሞች ሲታመሙ እናያለን ” ነው ያሉት።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የማኀበሩ የቦርድ አባል ዶ/ር በሀሩ በዛብህ ፣ “ ችግሩ የቆዬ ነው። ማንም መልስ የሰጠን የለም። ችግሮቹም ከቀን ወደ ቀን እየተባበሱ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

ዶ/ር በሀሩ በዛብህ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ለሀኪሞች የኢንሹራንስ ከለላ መኖር አለበት። ራሳችን ያመጣነው በሽታ እንኳ ሳይሆን ስናክም ብዙ በሽታዎችን ነው የምናገኘው። ብዙ የጤና ባለሙያዎች በህክምና ሂደት ላይ ግራጁዋሊ በሚያገኙት በሽታ ሞተዋል።

ክብደት ያለውን ታካሚ እያነሳ የአካል ጉዳተኛ የሚሆንም አለ። ከተላላፊ በሽታዎች ጋር እንሰራለን። ስለዚህ ጤና ባለሙያዎች በእነዚህ በሽታዎች ይጎዳሉ።

ብዙዎች እንደዚህ አይነት ችግሮች መኖራቸውን ሲያውቁ ሙያቸውን ሁሉ የቀየሩ አሉ። ወጣቶች ትምርታቸውን አቋርጠው ወደ ሌላ ሙያ የሚሄዱበት ሁኔም አለ።

ለሀኪሞች ተላላፊ የሆነ በሽታ መከላከያ ሂደቶች የሉም። መካላከያ ኖሮም በሽታ የሚተላለፍበት ሁኔታ አለ። ግን ለማገገም የሚሰጥ ህክሞና የለም። 

አንዳንድ መከላከያዎች ውድ ናቸው። ያን ለማቅረብም የኢኮኖሚው ሁኔታ ያን ያክል አይፈቅድም”
ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ሀኪሞች ብዙ ጭናዎችን ተቋቁመው እየሰሩ የሰሩትን የዲዩቲ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ሲጠይቁ ለእስር ሲዳረጉ መስተዋሉን የገለጸው ማኀበሩ፣ በጉባዔው ወቅት ውይይት እንደሚደረግበት ጠቁሟል።

(የማኀበሩ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢356😭9392🙏49🥰13🕊9😡8🤔5😱1
🔊 #የጤናባለሙያዎችድምጽ

🔴
የጸጥታ አካላት ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ድብደባ ፈጽመዋል፣ ዘጠኝ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላትን አስረዋል ” - የሆስፒታሉ ሠራተኞች

➡️ “ እነርሱ ጋ ብቻ አይደለም ያልተከፈለው፤ ከ2000 በላይ ሠራተኞች እንደ ዞን ያልተከፈላቸው አሉ ”  - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ

በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ፣ የይርጋጨፌ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ባለሙያዎች “ በጸጥታ አካላት ድብደባና እስራት ተፈጽሞባቸዋል ” ሲሉ ሠራተኞቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ተፈጽሟል ስላሉት እስራትና ድብደባ ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገልጹ፣ እንደ ሀገር የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ ባለመፈጸሙ የሥራ ማቆም አድማ መደረጉን ተከትሎ መሆኑን ሠራተኞቹ አስረድተዋል።

የአራት ወራት የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ ከ150 በላይ ለሚሆኑ የሆስፒታሉ ሠራተኞች አለመፈጸሙን፣ እስከ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ/ም እንዲፈጸምላቸውና እስከተጠቀሰው ጊዜ ድረስ ካልተፈጸመላቸው ሥራ የማቆም አድማ ለማድረግ እንደሚገደዱ በደብዳቤ ጭምር ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም ክፍያው ባለመፈጸሙ የሥራ ማቆም አድማ እንዳደረጉ፣ የተወሰኑት ሥራ ማቆም አድማ ያላደረጉ ሰራተኞች ቢሮ ባሉበት “ አድማ አስመትታችኋል ” በሚል እስራትና ድብደባ እንደተፈጸመባቸው በመግለጽ አማረዋል።

በዚህም፣ “የካቲት 10 እና 11 ቀን 2017 ዓ/ም ሥራ አልገባንም። በቀን 12/2017 ዓ/ም ደግሞ ሙሉ ፓትሮል ፓሊስ መጥቶ በሥራ ላይ የነበሩ የማኔጅመንት አባላትን ይዘው ወጡ ” በማለት ተናግረዋል።

አክለው፣ “ ከየቤቱ ያሉት ሠራተኞችም መረጃው ደርሷቸው ‘ካሰራችሁ ሁላችንንም እሰሩን የሁላችንም ጉዳይ ነው’ ብለው እስሩ ከተፈጸመበት ፓሊስ ጣቢያ ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል ” ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

የታሰሩት ምን ያክል ግለሰቦች ናቸው? ስንል የጠየቅናቸው ሠራተኞቹ በሰጡት ምላሽ፣ “የታሰሩት የሆስፓታሉ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት ናቸው፡፡ የጸጥታ አካላት ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ድብደባ ፈጽመዋል፣ 9 ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላትን አስረዋል ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሠራተኞቹን ቅሬታ በመያዝ፣ ድርጊቱ ለምን እንደተፈጸመ የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮን ምላሽ የጠየቀ ሲሆን፣ እስራቱ መፈጸሙን እና ደመወዙ አለመከፈሉን አምኖ ምላሽ ያለውን ሰጥቷል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ በዝርዝር ምን መለሱ ?

“ ባለሙያዎቹ የካቲት 7 መጥተው ነበር። ከኛ ጋ ውይይት አድርገዋል፡፡ ውይይት ካደረግን በኋላ ፕሮሰስ እያደረግን ለማክሰኞ ጠዋት ክልል ቀጠሮ እንደነበረ ገልጸንላቸው ነበር፡፡ ማክሰኞ ሂደን ዘጠኝ ሰዓት ላይ ምላሽ ታገኛላችሁ ብለናቸው ነበር፡፡

እነሱ ጋ ብቻ አይደለም ክፍያው ያልተከፈለው ከ2000 በላይ ሰራተኞች እንደ ዞን ያልተከፈላቸው አሉ፡፡ እንደ ዞንም ሶስት ሆስፒታል ላይ ነው ክፍያው ያልተከፈለው፡፡ የተለያዩ የጤና ባለሙያዎችም በወረዳ ደረጃ ያልተከፈላቸው አሉ፡፡

በሦስቱ ሆስፒታሎች ነው ያልተፈጸመው። ግን ሁለቱ ሆስፒታሎች የስራ ማቆም አድማ አላደረጉም፡፡ እነርሱ ግን ለማክሰኞ ቀጥረናቸው እያለ ቀጠሮውን አንቀበልም ብለው ሙያዊ ሥነ ምግባር በማይፈቅድ መንገድ ስራ የማመጽ ነገር አድርገው ነበር።

ግን የተወሰኑ ልጆች ደግሞ ስራ ገበታ ላይ ተገኝተው ነበር፡፡ ስለዚህ ኦሬዲ ድስከስ አድርገን ጉዳዩን ፈተን ልጆቹ ስራ ጀምረዋል አሁን፡፡ ስራ ላይ ናቸው ሁሉም ” ብለዋል።

ታሰሩ የተባሉት የሆስፒታሉ ባልደረቦች ሳይፈቱ እንዴት ሁሉም ስራ ላይ ሊገኙ እንደቻሉ ምላሽ የጠይቅናቸው ኃላፊው፣ “እነርሱ ያልተገባ አካሄድ የሄዱ አሉ፡፡ ከስነ ስርዓት ውጭ ያልተፈቀደ ሰልፍ የወጡበት ሂደትም አለ፡፡ እንግዲህ ከእስር እንዲወጡ እየተሰራ ያለበት ሂደት አለ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሠራተኞቹ ቅሬታ ያቀረቡት የአራት ወራት ገደማ ደመወዝ አለመጨመሩን ተከትሎ ነውና የመብት ጥያቄ በመቅረቡ እስርና ድብደባ መፈጸም አግባብ ነው? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ አንዷለም በሰጡት ማብራሪያ፣ “ሠራተኞቹና ባለሙያዎቹ፣ ‘የፈጸምናቸው ድርጊቶች ትክክል አይደሉም ህዝቡን በድለናል ብለው’ ይቅርታ ጠይቀው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ውይይት ተደርጎ ጤናማ ስራ ጀምረዋል አሁን” ሲሉ አስተባብለዋል።

ይቅርታ የጠየቁት ማን ናቸው? ሰራተኞቹ ወይስ አሳሪዎቹ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም  ኃላፊው፣ “ሰራተኞቹ ” ሲል የመለሰ ሲሆን፣ ታስረው እያለ እንዴት ይቅርታ ይጠይቃሉ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።

እሳቸውም፣ “ሙያዊ ክብር በጣሰ መልኩ ሰልፍ የወጡትም ይቅርታ እየጠየቁ ነው ያሉት አሁን፡፡ ‘እነርሱ ናቸው ጥፋተኛ’ በሚል ልከውልናል ቤተሰቦቻቸው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የተወሰኑት ሠራተኞች የስራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር፤ በአንጻሩ ደግሞ የተወሰኑት ደግሞ ስራ ላይ ተገኝተው ነበር፤ ነገርግን ‘ሌሎቹን አሳምጻችኋል’ በሚል ስራ የገቡትም ናቸው የታሰሩት። ሥራ ላይ እያሉ ታስረው ሳለ “ይቅርታ ጠይቀዋል” መባሉ ምን ማለት እንደሆም በድጋሚ ምላሽ ጠይቀናል።

አቶ አንዷለም በምላሻቸው፣ “ነገሩ እንግዲህ እንደዚሁ ነው። አሁን ውይይት ላይ ነን፡፡ እነርሱ የሰሩት ጥፋት ስለነበረ ነው የተጠየቁት። አሁን ይቅርታ ጠይቀው ውይይት ላይ ነን ችግሩን ለመፍታት” ነው ያሉት፡፡

እንዳጠቃላይ ችግሩን ለመፍታትስ ምን እየተሰራ ነው? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ “አሁን በጀቱ እውቅና አግኝቷል፡፡ ለሰራተኞች የጸደቀላቸው በጀት እጃችን ላይ ገብቷል፡፡ የክፍያ ሂደት ለማመቻቸት ጥረት እየተደረገ ነው” ብለዋል።

“ከክልል ፋይናንስ ገንዘብ እንድለቀቅ ሂደት ላይ እንደሆነና ያው ከዚያ እንደተለቀቀ ክፍያ እንደሚከፈል ተግባቦት ላይ ተደርሷል” ሲሉም አክለዋል፡፡

(ጉዳዩን እስከመጨረሻ የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😭561😡199129🙏24👏23🤔22😱13😢13🕊12🥰3
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ

🔴 " በየጊዜው ቃል ከመግባት የዘለለ ምንም መፍትሄ የሰጠን አካል የለም !! " - የጤና ባለሙያዎች

➡️ " ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈለን ለ2ኛ ጊዜ ስራ ለማቆም እየተገደድን ነዉ !! "


በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ-አባያ ወረዳ ሀንጣጤ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በበዓላት፣ በማታና የእረፍት ቀናት የሰሩበት ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸዉ ለሁለተኛ ጊዜ ስራ ለማቆም እየተገደዱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በቁጥር 102 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎቹ ተፈራርመዉ ለሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በአድራሻ በፃፉትና ለሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ፣ ለሎካ አባያ ወረዳ እና ለማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ እንዲሁም ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮና ለክልሉ ብልፅግና ፓርቲ በግልባጭ ባስታወቁት የቅሬታ ማመልከቻ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2017 ዓ/ም የያዝነዉ ወር ድረስ በተለያዩ ጊዜያት ያልተከፈለ በእያንዳንዱ ሠራተኛ ከ6 እስከ 9 ወር ድረስ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸዉና በዚህም ለልዩ ልዩ ችግሮች መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸዉ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታቸዉን በየደረጃው ለሚመለከታቸው አካላት ሲያቀርቡ ቢቆዩም በየጊዜው ቃል ከመግባት የዘለለ ምንም መፍትሄ የሰጠን አካል የለም ብለዋል።

" ባሳለፍነዉ ዓመት በተመሳሳይ መልኩ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በወቅቱ ባለመከፈሉ ምክንያት ለአንድ ወር ሙሉ የስራ ተዘግቶ ነበር " የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ " አሁንም ያለዉ ሁኔታ ወደዚያ እያመራ ነዉ" ብለዋል።

በተለያዩ ጊዜያት ያልተከፈላቸውን የትርፍ ሰዓት ክፍያ በሰራተኞች ቁጥርና ባልተከፈላቸዉ ወር ተባዝቶ ከ2.4 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ የሚገልፁት ሰራተኞቹ ፤ የኑሮዉ ጫና ተጨምሮበት ቀርቶ በቀደሙት ጊዜያት እንኳን ያለ ክፍያ እየተመላለሱ መስራት አዳጋች በመሆኑ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች መጋለጣቸዉን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሠራተኞችን ቅሬታ ሰምቶ የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳዳሪና የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪን በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግሯቸዋል።

የሎካ አባያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘሪሁን ጥላሁን የሀንጣጤ ሆስፒታል ለሎካ አባያ ወረዳ ብቻ ሳይሆን ለአጎራባች አከባቢዎችም ጭምር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ከዚህ ቀደም የነበሩ አመራሮች በሆስፒታሉ አሰራር ዉስጥ ጣልቃ በመግባት የሰራተኞች የትርፍ ሰዓት ክፍያ ብቻ ሳይሆን የጥቅማጥቅምና ሌሎችንም በጀቶች በማጉደል በአሁኑ ወቅት በሕግ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ተናግረዉ ለሆስፒታሉ ሰራተኞች ያልተከፈላቸዉ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከወረዳዉ አቅምና በላይ ነዉ ብለዋል።

የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ በበኩላቸው የሕክምና ባለሙያዎች እንዲሁም ሕብረተሰቡ የሚያነሷቸዉ ቅሬታዎች ተገቢ መሆናቸውን በመግለፅ የችግሩ መንስኤ የቀድሞ የወረዳዉ አመራርና የሆስታሉ ስራ አስኪያጅ ባደረጉት የሃብት ብክነትና ሌብነት መሆኑን ጠቁመዉ እሳቸው ወደ ዞን አስተዳዳሪነት ከመጡ ወዲህ የሆስፒታሉም የቦርድ ሰብሳቢ መሆናቸዉንና ነባሩን አመራር ከስልጣን እንዲወርድና በሕግ እንዲጠየቅ በማድረግ ከነበረዉ 13 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ዉዝፍ የተወሰኑ ወራት እንዲከፈል መደረጉን ተናግረዋል።

ችግሩ በሀንጣጤ ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የጤና ጣቢያዎች ጭምር ያለ በመሆኑ በወረዳዉና በዞኑ በጀት ለመሸፈን ከአቅም በላይ ስለሆነ ከክልሉ ብድር መጠየቃቸዉንና በቀጣይ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ የቀሪ ወራቶችን ክፍያ በሙሉ ለሙሉ ለመክፈል መዘጋጀታቸዉን ገልፀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭13153😢16🕊11😡8😁3🤔2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ተመላላሽ የሕክምና ቀጠሮ ቢኖረንም ሆስፒታሉ ዝግ ስለሆነ አገልግልት ማግኘት አልቻልንም " - ተገልጋዮች ➡️ " ከ6 እስከ 9 ወራት ታግሰን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ከአቅማችን በላይ ሆኖ ስራ አቁመናል" - የጤና ባለሙያዎች 🔴 " የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " - የዞን አስተዳዳሪ በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ…
#Update
#የጤናባለሙያዎችድምጽ

" የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ጨምሮ 14 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች ከስራ ቦታቸዉ ተወስደው ታስረዋል " - የሀንጣጤ ሆስፒታል ባለሙያዎች

" ' ለሚዲያ መረጃ ስለሰጣችሁ ሚዲያ የሚከፍላችሁ መስሏችኋል ' የሚሉ አመራሮችም አሉ ! "

በሲዳማ ክልል፤ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፊያ ባለመከፈሉ ለሎካ አባያ ወረዳ፣ ለማዕከላዊ ሲዳማ ዞንና ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በደብዳቤ ካሳወቁ በኋላ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆማቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ማሳወቃቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ስለ ጉዳዩ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ ፥ የሠራተኛዉ ጥያቄ ትክክለኛ መሆኑን ገልፀዉ ክፍያዉ እንዲፈፀም ከክልሉ መንግስት ብድር መጠየቃቸዉንና በቅርቡ እንደሚከፈላቸዉ ገልፀዉ የነበረ ሲሆን " የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆም መብታቸዉ ነዉ " ሲሉ ገልጸውም ነበር።

ትላንት የሆስፒታሉ ሠራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት " ሁሉም ሰራተኛ በአንድነት ተፈራርሞ ባስገባዉ ደብዳቤ መሰረት ከባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ የትርፍ ሰዓት ስራ ብቻ ያቆሙ ቢሆንም የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክር እና 7 የማኔጀመንት አካላትን ጨምሮ 14 የሚሆኑ የሆስፒታሉ ባለሙያዎችን ፖሊስ ከስራ ቦታቸዉ ጭምር ወስዶ አስሯቸዋል " ብለዋል።

" ሁሉም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆሙ ሰበብ ተደርጎ በመደበኛ ስራዉ ላይ እንከን እንዳይፈለግበትና ላለመከሰስ የስራ ሰዓቱን በአግባቡ እየተጠቀመ ነዉ " የሚሉት ሠራተኞቹ  " ትላንት ጠዋት በድንገት 2 ዶክተሮች፣ 7 ነርሶችንና ሌሎች ባለሙያዎችን 'ትፈለጋላችሁ' በሚል ያለ ፍርድ ቤት መጥሪያ ከነ ጋዎናቸዉ ጭምር ወደ ሀንጣጤ ፖሊስ ጣቢያ አስገብተዋቸዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

" ሁሉም የሆስፒታሉ ሠራተኞች አንድ ላይ በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ብንሄድም ' ከበላይ አካላት ታዘን ነዉ ' የሚል ምላሽ ነዉ የተሰጠን " ብለዋል።

ሠራተኞቹ ቀኑን ሙሉ እዛዉ ለመሆን መወሰናቸዉንና ከአስራ አንድ ሰዓት በኋላ የተወሰኑ አመራሮች ወደ ፖሊስ ጣቢያ የመጡ ቢሆንም የታሰሩት ሳይፈቱ ወደ ' ቤታችሁ ሂዱ ' ተብለው እስኪጨላልም እዛዉ የቀሩ ባለሙያዎች እንደነበሩ አስረድተዋል።

" የትርፍ ሰዓት ክፍያ ካልተከፈለን ብለን ስራ አላቆምን " የሚሉት የጤና ባለሙያዎቹ " አይደለም መደበኛ ስራ ለማቆም ምንም ሳይከፈለን በብዙ ችግሮች ዉስጥ ሆነን እራሳችንን እየጎዳን ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓቱን ስራ ጭምር ስንሰራ ቆይተናል ነገሮች ከአቅማችን በላይ ሲሆኑ በደብዳቤ አሳዉቀን የትርፍ ሰዓቱን ስራ ለማቆም ተገደናል " ብለዋል።

ሁሉም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ስራ ባቆመበት ሁኔታ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ጨምሮ የማኔጅመንት አባላትንና የተወሰኑ ሠራተኞችን ለይቶ የማሰሩ ጉዳይ ተገብነት የሌለው እና የሚመለከታቸዉ አካላት በአፋጣኝ እልባት ሊሰጡበት የሚገባ ጉዳይ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

" ' ሚዲያ ላይ ስለከሰሳችሁ ሚዲያ የሚከፍላችሁ መስሏችኋል' የሚሉ አመራሮች ነበሩ " ያሉን ቅሬታ አቅራቢዎቹ " ሜዲካል ዳይሬክተሩንና ማኔጅመንቱን ' ለምን ሠራተኛ ታሳምፃላችሁ፣ ከወረዳዉና ከዞኑ መንግስት የሚተላለፍላችሁን መመሪያ ለምን አታስፈፅሙም ' ብለዉ የሚያስፈራሩም ነበሩ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የከፍተኛ አመራሮችን ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርጓል።

ከዚህ ቀደም የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ በስልክ መረጃ የሰጡን ቢሆንም አሁን ላይ " ወደ ቦታዉ በአካል ካልመጣችሁ መረጃ መስጠት አልችልም " በማለታቸዉ ሳይሳካ ቀርቷል።

ፈቃደኛ ሲሆኑ ምላሻቸዉን የምናካትት ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

@tikvahethiopia
😭500😡22255😢29🙏10🥰8🤔7👏5🕊5
TIKVAH-ETHIOPIA
“ በሙያው ጠቅላላ ሀኪም ነው ቤተሰብ ለመጠየቅ እየሄደ ነው በጥይት ተመትቶ የተገደለው ” - የሟች ጓደኛ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መራቢቴ ወረዳ በእናት ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሀኪሙ “በተተኮሰበት ጥይት” መገደሉን የቅርብ ሰዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ዶክተር ገብረሚካኤል ወልደ መላክ ተገደለ የተባለው ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ በመኪና እየተጓዘ መራቢቴ አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል። ቃላቸውን የሰጡን…
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

“ ጤና ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለው የግድያ ወንጀል ከቀን ወደ ቀን አሳሳቢ እየሆነ ነው ” - ማኀበሩ

በደመወዝ ከመበደላቸው በባሰ ሁኔታ ጤና ባለሙያዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች እየተሰባባሱና አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የማኀበሩ ፕሬዚደንት አቶ ዮናታን ዳኛው በሰጡን ቃል፣ “ ጤና ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለው የግድያ ወንጀል ከቀን ወደ ቀን አሳሳቢ እየሆነ ነው ” ብለዋል።

የማኀበሩ ፕሬዚደንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

“ የሀገርን ስብራት የሚጠግኑ ጤና ባለሙያዎችን፣ ሀኪሞችን መግደል የትውልድን የነገ ተስፋ ማጨለም ነው። በኢትዮጵያ ሀኪሞች ተገደሉ ሚለው መርዶ ከመደጋገሙ የተነሳ የዘወትር ዜና ሆኗል።

ብዙ ዋጋ ከፍለው የሰውን ሕይወት የሚታደጉ፣ ችግሮችን ተጋፍጠው የተቀማን ህልም የሚያለመልሙ ሀኪሞች ለምን ይገደላሉ?

እድሜያቸው ለጋ የሆነ፣ ሀገርን ብዙ የሚያገለግሉ፣ ሀገር ብዙ የደከመችባቸውን ሀኪሞች መግደል የሀገርን የነገ እጣ ፈንታ የሚያበላሽ አሳፋሪ ተግባር በመሆኑ ሁሉም ዜጋ በእኩል ሊያወግዘውና ሊታገለው ይገባል።

መንግስት ጤና ባለሙያዎች የሚሰሩበትን አካባቢ ከየትኛውም አደጋ ነፃ መሆኑን ማረጋገጥና ምቹ የሥራ አካባቢ መፍጠርን ቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ ሊሰራ ይገባል።

አብዛኞቹ ጤና ተቋማት ደህንነታቸው በበቂ ሁኔታ የተጠበቀ አለመሆኑ ደግሞ ጉዳዩን የበለጠ ውስብስብ ያደርገዋል።

በገቡት ቃል ኪዳን መሰረት ሁሉንም ዜጋ ያለ ምንም ልዩነት ሚያገለግሉ፣ የፓለቲካ ውግንና የሌላቸው ጤና ባለሙያዎችን ያነጣጠር የግድያ ወንጀል በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም።

በአስቸኳይ እልባት ይሻል ” ነው ያሉት።

ከቀናት በፊት መራቢቴ ወረዳ በእናት ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሀኪም የነበረው ዶክተር ገብረሚካኤል ወልደ መላክ ቤተሰብ ጥየቃ በመኪና እየሄደ በነበረበት ወቅት  “ በተተኮሰበት ጥይት ” መገደሉን የቅርብ ሰዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

ከወራት በፊት ደግሞ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥበበ ግዮን ግቢ ስፔሻላንስድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ዳኘ በተተኮሰባቸው ጥይት መገዳላቸው አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭994💔11284😢33😡24🕊17🥰8🤔8😱7
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

" አስተዳደራዊ በደል በድሬዳዋ ጤና ቢሮ ተፈፅሞብኛል " - የሳቢያን ሆስፒታል ሀኪም ዶክተር ሀብታሙ አለሙ

➡️ " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት የለም " - የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ


በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሳቢያን ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሃኪም የሆኑት ዶክተር ሀብታሙ አለሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች ያቀረቡትን ቅሬታ በመደገፋቸው በቢሮው አስተዳደራዊ በደል ተፈፅሞብኛል በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተውና ለባለሞያው የተጻፈው ደብዳቤ " ለስራ በተመደበበት ክፍል የሙያ ስነምግባርን በተፃረረ መልኩ በእናቶች እና በህፃናት ክፍል ወላድ እናቶችን በተደጋጋሚ ማመናጨቅ፣ መሳደብ እና ያለአግባብ ማመላለስ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ባለመታረሙ ወደ ገኦዳ ጉዱንፈታ ጤና ጣቢያ አዘዋውረናል " የሚል ነው።

የጤና ባለሙያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ ይደረግልን ተብሎ ቅሬታ ሲያቀርቡ ለምን ሃሳቡን ደገፍክ ብለው የድሬዳዋ ከተማ ጤና ቢሮ ሃላፊ እና ምክትል ደውለው ለምን ይሄን አደረክ አሉኝ፣ እኔም ጥያቄው እንደሀገር ነው የቀረበው፣ እንደ ድሬዳዋ አይደለም፣ ይሄ ደግሞ የመብት ጥያቄ ነው ብየ መለስኩኝ ።

የሃላፋዎች ምላሽም በድሬዳዋ ከተማ አንደዚህ መንቀሳቀስ አትችሉም፣ የከተማችንን ስም ያቆሽሽብናል፣ ስለዚህ የህክምና ባለሙያው ዝም ነው ማለት ያለበት አሉኝ።

በነጋታው ከሰዓት የዝውውር ደብዳቤ እና የዲስፕሊን ጉድለት አለብህ ብለው ከሃላፊዎች ሲሰጠኝ የጤና ቢሮ ሃላፊዋን ዶክተር ፅጌሬዳን ለማናገር ቢሮ ስሄድ ባለማግኜቴ ስልክ በመደወል ሳናግሯቸው ቅድሚያ ስሜን አጥፍተሀል እና ፌስቡክ ላይ ይቅርታ ብለህ ፃፍ ከዚያ ውጭ አላናግርህም አሉኝ " ሲሉ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ላይ ስማቸው የተጠቀሰው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ እንዲሁም ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰይድ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልካቸው ላይ ቢደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልም።

በጉዳዩ ላይ የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ምን አለ ?

ዶ/ር ሀብታሙ " እንደ ሆስፒታል በዲስፕሊን ተፅፎብኝ የሚያውቅ ደብዳቤ የለም " ማለታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ዶክተር አባይነህን ጠይቋል።

በምላሻቸውም " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት ክስ #የለም " ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ እያዘጋጀ በነበረበት ወቅት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ሲስተር መስከረም አሰፋ በኃላፊነት ቦታቸው ላይ እንደሌሉ ሰምቷል።

ሲስተር መስከረም ይኽ መረጃ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ከሥራ እረፍት እንዲያደርጉ እንጂ ዝውውርም ሆነ እድገት እንዳልተሰጣቸው ለማረጋገጥ ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደመወዝ ጥያቄው ጋር በተገናኘ እንዲሁም በዚህ መረጃ ላይ ለቀረቡት ቅሬታዎች የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊዎችን ለማናገር ያደረግው ጥረት ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ማካተት ሳይቻል ቀርቷል።

በጉዳዩ ላይ ቢሮውም ሆነ ማንኛውም አካል ምላሽ እና ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭911😡166128💔33🤔23😢20🥰10🕊10👏8🙏8😱5