እናት ፓርቲ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር በተያያዘ መግለጫ ልኮልናል።
ፓርቲው " መንግሥት እየተገበረው ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፍቱን መድኃኒት ሳይሆን በጫናና አጣብቂኝ የመጠ የሥርዓቱን እድሜ ማራዘሚያ ኪኒን ነው " ሲል ገልጾታል።
በዚሁ መግለጫው ላይ ፤ የሚፈራ ማኅበራዊ ቀውስ እንዳለ በማመላከት ይህ ቀውስ ሊታከም ከማይችልበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን እንደገና እንዲያጤነው አሳስቧል።
መንግሥት በግል ዘርፉና ማኅበረሰቡ ላይ የጫነውን እንቅፋቶች ሁሉ እየመረመረ በአስቸኳይ እንዲያነሳም ጠይቋል።
የሠራተኛውና ደሞዝተኛው የዛሬ 6 ዓመቱ የኑሮ ደረጃን የሚመልሰውን (የሚያስተካክለውን) የደሞዝ ጭማሪ በአስቸኳይ እንዲያደርግም መንግስትን ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርሶ እንዳይበላና አቅርቦት እንዳይጨምር የምርት ግብዓቶች (factors of production) ሁሉ ከካድሬ እጅ ወጥቶ አምራቹ/ባለቤቱ እንዲይዘውና እንዲያዝበት እንዲደረግም ፓርቲው እናሳስቧል።
እናት ፓርቲ በላከው መግለጫ ፤ " በአጠቃላይ ሲንከባለል የመጣውና አሁን የባሰበት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በካድሬዎች ሳይሆን በባለሞያዎች እንዲመራ በማድረግ ግልጽ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ እንዲቀመጥ እንጠይቀለን " ብሏል።
በተጨማሪ ፥ መንግሥት ራሱ ፈቅዶና ፈርሞ ያመጣው ፖሊሲ የፈጠረውን ምስቅልቅል በነጋዴው ማኅበረሰብ ላይ እያመካኙ ሱቅ ማሸግና እጅ መንሻ መቀበል ሥራዬ ብለው የያዙትን ባለስልጣኖቹን አደብ እንዲያስገዛ አሳስቧል።
ፓርቲው ፤ " መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ " ሁሉንም ድስት እኔ ካልጣድኩ " ማለቱን አቁሞና ከሁለገብ ተጫዋችነቱ ወጥቶ ወደ የመንግሥት ዳኝነቱ ብቻ እንዲገባ፤ " ነጻ ገበያን ተቀብያለሁ " ካለ በነጻነት መሥራትንና ሀብት ማፍራትንም እንዲቀበልና ዜጎች እድሜ ልካቸውን ሠርተው ያፈሩትን ንብረት ያለ ካሳ እያፈረሱ ሕዝብን ማደህየቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም " ሲልም በጥብቅ አሳስቧል።
#እናትፓርቲ
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏921❤168😡62🙏50🕊31😭20🤔19😢18😱12🥰10
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC በአረጋዊው መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌውና አራት ቤተሰባቸው ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያን በልዩ ሁኔታ እንደሚከታተለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አሳውቋል። በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ (ሞጆ ) ወረዳ ቤተ ክህነት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ለ41 ዓመታት ያህል ከድቁና እስከ…
#እናትፓርቲ
" አንዱን ሰቆቃ ማን ፣ እንዴት ፣ ለምን እንዳደረገው በበቂ ሳይጠናና ጠያቂም፣ ተጠያቂም ሳይኖር ለጥቂት ጊዜያት ዝም ያለና የቆመ ካስመሰለ በኋላ ያለፈውን በሚያስንቅ እልቂቱ ይቀጥላል " - እናት ፓርቲ
እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልኳል።
ፓርቲው " በሀገራችን ኢትዮጵያ ሥርዓታዊ የሆነ በእምነት ተቋማት፣ በሃይማኖት አባቶችና ምእመናን ላይ የሚደርስ ጥቃት አቻ በሌለው መልኩ ከዳር ዳር ሲያምሳት ማየትና ምንም እንዳልተፈጠረ በዝምታ ማለፍ የተለመደና በተዘዋዋሪ ይኹንታ የመስጠት የሚመስል ክስተት ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል " ብሏል።
" የግፉ መጠን ከዕለት ዕለት እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ መልኩንና ቦታውን እየቀያየረ አሰቃቂነቱንም በየወቅቱ የከፋ እያደረገ ቀጥሏል " ሲል ገልጿል።
" አንዱን ሰቆቃ ማን፣ እንዴት፣ ለምን እንዳደረገው በበቂ ሳይጠናና ጠያቂም፣ ተጠያቂም ሳይኖር ለጥቂት ጊዜያት ዝም ያለና የቆመ ካስመሰለ በኋላ ያለፈውን በሚያስንቅ እልቂቱ ይቀጥላል። እንደማኅበረሰብም ጣት መቀሳሰርና አኹን አኹን ደግሞ እልቂትን በጥንቃቄ በመለማመድ ላይ ያለን ይመስላል " ብሏል።
" ባለፈው መስከረም 16/2017 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሞጆ ወረዳ የቢቃ ደ/መ/ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የነበሩት ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው እና 4 ቤተሰባቸው በግፍ በአሰቃቂ ኹኔታ መገደል ተራ ግድያ ሳይሆን በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ፣ ቤተሰብን በሙሉ በአንድ ላይ በመፍጀት ዘር እንዳይተርፍ ጭምር የተወሰደና ቀደም ሲል ከተፈጸሙ መሰል ግድያዎች የጥፋት ደረጃውን ከፍ አድርጎ ያሳየ ጭፍጨፋ ነው " ሲል ፓርቲው ገልጿል።
ፓርቲው " ይኽንና ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት የደረሱ ጥቃቶችና የጅምላ ፍጅቶች በአጋጣሚና በዘፈቀደ እየሆኑ ያሉ ሳይሆን በተጠና መልኩ ሀገርን አጽንተው ባቆሙ ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ላይ ያነጣጠሩና ፈርጀ ብዙ አንድምታ ያላቸው በመጣህብኝ ሰበብ የተጠና ዘር ማጽዳትና ማሳሳት/systemic ethnic cleansing/፣ በቀል/revenge/፣ ማዋረድ/humiliation/፣ የአዲሱን ዓለም አስተሳሰብ/new world order/ ትግበራ አካል እንደሆነ በጽኑ እናምናለን " ብሏል።
" በዓለም ላይ የተፈጸሙ መሰል ድርጊቶች ያለመንግሥት መዋቅር ቀጥተኛም ይኹን ተዘዋዋሪ ተሳትፎ አልተፈጸሙም " የሚለው ፓርቲው " የእኛውም ከዚያ ሊለይበት የሚችል አመክንዮና ዕውናዊ ማሳያ ይኖራል ተብሎ አይታመንም " ሲል ገልጿል።
" እንዲህ ያሉ ድርጊቶች በጥንቃቄና አሻራ በማይተው መልኩ፣ ገፋ አድርጎ ቢሄድም በማዳፈን የሚፈጸሙ ናቸው። እርግጥ ነው የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የዚኽም ሆነ የቀደሙ ጅምላ ጭፍጨፋዎች ተዋንያን ለፍርድ አደባባይ መቅረባቸው አይቀሬ ነው " ብሏል።
" የእኛን ፓርቲ ጨምሮ መሰል ተቋማትና ግለሰቦች በቀደሙት ጊዜያት በተደጋጋሚ ያሰማነው ዜጎችና ተጋላጭ የሆኑ የሃይማኖት ተቋማት /hotspot areas/ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያስተላለፍነው ጥሪ ሰሚ በማጣቱ ወይም ሆነ ተብሎ በመታለፉ ዛሬም ጭፍጨፋውና ግድያው በከፋ መልኩ እንደቀጠለ ነው " ብሏል።
" ኢትዮጵያውያን አንዳችን የአንዳችንን ደህንነት እየጠበቅን የእምነት ተቋማቶቻችንን ከሥርዓታዊ ጥቃት ለመታደግ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቆምና ለተሻለ ጊዜ እንድንተጋ " ሲል እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

❤669👏139😭77🙏35🤔20😡20🕊14😢7🥰6😱5