እናት ፓርቲ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር በተያያዘ መግለጫ ልኮልናል።
ፓርቲው " መንግሥት እየተገበረው ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፍቱን መድኃኒት ሳይሆን በጫናና አጣብቂኝ የመጠ የሥርዓቱን እድሜ ማራዘሚያ ኪኒን ነው " ሲል ገልጾታል።
በዚሁ መግለጫው ላይ ፤ የሚፈራ ማኅበራዊ ቀውስ እንዳለ በማመላከት ይህ ቀውስ ሊታከም ከማይችልበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን እንደገና እንዲያጤነው አሳስቧል።
መንግሥት በግል ዘርፉና ማኅበረሰቡ ላይ የጫነውን እንቅፋቶች ሁሉ እየመረመረ በአስቸኳይ እንዲያነሳም ጠይቋል።
የሠራተኛውና ደሞዝተኛው የዛሬ 6 ዓመቱ የኑሮ ደረጃን የሚመልሰውን (የሚያስተካክለውን) የደሞዝ ጭማሪ በአስቸኳይ እንዲያደርግም መንግስትን ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርሶ እንዳይበላና አቅርቦት እንዳይጨምር የምርት ግብዓቶች (factors of production) ሁሉ ከካድሬ እጅ ወጥቶ አምራቹ/ባለቤቱ እንዲይዘውና እንዲያዝበት እንዲደረግም ፓርቲው እናሳስቧል።
እናት ፓርቲ በላከው መግለጫ ፤ " በአጠቃላይ ሲንከባለል የመጣውና አሁን የባሰበት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በካድሬዎች ሳይሆን በባለሞያዎች እንዲመራ በማድረግ ግልጽ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ እንዲቀመጥ እንጠይቀለን " ብሏል።
በተጨማሪ ፥ መንግሥት ራሱ ፈቅዶና ፈርሞ ያመጣው ፖሊሲ የፈጠረውን ምስቅልቅል በነጋዴው ማኅበረሰብ ላይ እያመካኙ ሱቅ ማሸግና እጅ መንሻ መቀበል ሥራዬ ብለው የያዙትን ባለስልጣኖቹን አደብ እንዲያስገዛ አሳስቧል።
ፓርቲው ፤ " መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ " ሁሉንም ድስት እኔ ካልጣድኩ " ማለቱን አቁሞና ከሁለገብ ተጫዋችነቱ ወጥቶ ወደ የመንግሥት ዳኝነቱ ብቻ እንዲገባ፤ " ነጻ ገበያን ተቀብያለሁ " ካለ በነጻነት መሥራትንና ሀብት ማፍራትንም እንዲቀበልና ዜጎች እድሜ ልካቸውን ሠርተው ያፈሩትን ንብረት ያለ ካሳ እያፈረሱ ሕዝብን ማደህየቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም " ሲልም በጥብቅ አሳስቧል።
#እናትፓርቲ
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏921❤168😡62🙏50🕊31😭20🤔19😢18😱12🥰10