TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ ሶማሊያ #ሞቃዲሾ በረራ ይጀምራል። አየር መንገዱ በሳምንት ሶስት ጊዜ ሰኞ ረቡዕ
እና ዓርብ ወደ ሞቃዲሾ ለመብረር እቅድ ይዟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በሶማሊያ ዋና ከተማ #ሞቃዲሾ በተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የፈንጂ ጥቃት፣ የሰው ሕይወት አለፈ፡፡ በዛሬው ዕለት ከሶማሊያ ፖሊስ ኃይል የወንጀል ምርመራ ክፍል አቅራቢያ በሚገኘው የሳሃፊ ሆቴል እና በአካባቢው በደቂቃዎች ልዩነት የፈነዱት #ቦምቦች አራቱን አንጋቾች ጨምሮ ሃያ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የዓይን ዕማኞችና የሕክምና ባለሥልጣናት አመልክተዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE የኢትዮጵያ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች ቀጣይ የሶስትዮሽ ውይይታቸውን #ሞቃዲሾ ላይ ለማካሄድ መስማማታቸው ታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በረራው ተቋርጧል‼️

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ40 ዓመት በኃላ ወደ ሶማሊያ #ሞቃዲሾ ጀምሮት የነበረውን በረራ #ማቋረጡን ሸገር FM ዘገበ።

ተጨማሪ፦ ከትናንት በስትያ ዜግነቱ እንግሊዛዊ የሆነ ግለሰብ ከሞቃዲሾ ወደ አዲስ አበባ የሚመጣ በረራ ላይ #ተቀጣጣይ ነገር ይዞ ሊገባ ሲሞክር በኤርፖርት ጥበቃዎች #ተይዟል#ከአልሽባብ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል ተብሎም ተገምቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ #ላልተወሰነ ጊዜ በረራውን አቋርጧል ሲል ሸገር ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መቅዲሹ፤ በደረሰው ጥቃት 19 ተገደለዋል። ትናንት ምሽት በአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታ በደረሰባት የሶማሊያ ዋና ከተማ #ሞቃዲሾ ዛሬም ተኩስ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። በፍንዳታው የደረሰውን ጨምሮ እስካሁን ቢያንስ 29 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። በርካቶችም ተጎድተዋል። ትናንት ምሽት አንድ አጥፍቶ ጠፊ እንቅስቃሴ በሚበዛበት መንገድ ዳር ከሚገኝ ሆቴል አቅራቢያ በመኪና ውስጥ ባጠመደው ፈንጂ ራሱን ሲያጋይ እሳቱ ተዛምቶ ጉዳቱን እንዳሰፋውም ተጠቅሷል። ከፍንዳታው በኋላ የሶማሊያ ኃይሎች በአካባቢው ወደ አንድ ሕንፃ ተጠግተው ከመሸጉ #የአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር መታኮስ መቀጠላቸውንም ተገልጿል። ሆቴሉ ውስጥ የአልሸባብ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን አግተው መቆየታቸውን የሶማሊያ መንግሥት የዜና አውታር ዘግቧል። የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይል ባልደረባ አብድራህማን አሊ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል የተጎዱ ሰዎችን የማዳን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን፣ ተኩሱ በመቀጠሉም የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል አመልክተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬ #ሞቃዲሾ ውስጥ ከሶማልያው ፕሬዚዳንት ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ከሚገኝ ምግብ ቤት ውጭ ዛሬ የደረሰ የመኪና ቦምብ ፍንዳታ በትንሹ ለ5 ሰዎች ሕይወት መጥፋትና ሌሎች ዘጠኝ መቁሰል ምክንያት መሆኑ ተገለፀ። የጥቃቱን ሰላባዎች ቁጥር ያስታወቁት የደኅንነት ባለሥልጣናትና የዳስላን ምግብ ቤት ባለቤት ናቸው።

#VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

ሶማልያ ዋና ከተማ #ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ በትንሹ 17 ሰዎች #መሞታቸውን የሆስፒታል ምንጮችን ጠቅሶ ቪኦኤ ዘገበ። የሞቃዲሾ ትልቁ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሞሓመድ ዩሱፍ እንደገለፁት፣ ሌሎች 28 ቁስለኞች ሆስፒታል ገብተዋል። አደጋው የደረሰው አንድ ተጠርጣሪ አጥፍቶ ጠፊ፣ ይጓዝባት የነበረችውን ተሽከርካሪ፣ ሕዝብ በሚበዛበት የሞቃዲሾ አውራ-ጎዳና መጋጠሚያ ላይ በማፈንዳቱ እንደሆነም ተገልጿል። ለፍንዳታው አል-ሻባብ ኃላፊነት መውሰዱንም አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia