TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሁንም ጥንቃቄ📌 ከዝህ በፊት ብያለሁ። አሁንም ደግሜ እላለሁ! ከትናንሽ አጀንዳዎች እንዉጣ። ስለ ምልክት ሳይሆን ስለሀገር ከልብ እናስብ! #ሀገር ካለች #ባንዲራ መስቀል እና #ሀዉልት መገንባት አይከብድም! ሀገር #ከሌለ ግን ባንዲራ ብቻዉን ትርጉም የለዉም! አሁን #ሊቢያ ወይም #የመን ላይ ባንዲራ መያዝ ወይም ሀዉልት መትከል ምን ያደርጋል? ችግራችን በባንዲራ ወይም በሀዉልት አይፈታም። የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ።

ጆሮ ያለዉ ይስማ!
.
.
Ammas of eeggannoo📌

Kanaan duras jedheera. Ammas irran deebi'a! Ajandaa xixinnoo keessaa haa baanu. Waan mallattoo dhiifnee waan biyyaa onnee irraa haa yaannu! Biyyi yoo jiraatte alaabaa fannisuu fi siidaa dhaabuun hin dhibu. Yoo biyyi hin jirre garuu alaabaan qophaatti hiika hin qabu! Amma #Liibiyaa ykn #Yemen keessatti alaabaaqabatuun ykn siidaa dhaabuun maal godha? Rakkoon keenya alaabaa ykn siidaan hin hiikkatu! Shira diinaa haa fashalsinu!

Dubbii kana qalbisaa!

©አቶ ታዬ ደንደአ (የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ሊቢያ

የዓረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ተጠየቀ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተፋላሚ ሃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡ ተፋላሚዎቹ የኢድ አል አድሃ(ዓረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ነው በመንግስታቱ ድርጀት ጥሪ የቀረበው፡፡

እስከ ዛሬ ምሸት ድረስም ሁለቱ ተፋላሚዎች ጥሪውን ስለመቀበል አመቀበላቸው ለመንግስታቱ ድርጅት የሊቢያ መልዕክተኛ የጽሁፍ ማረጋገጫ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከአውሮፓውኑ ሚያዚያ ወር ጀምሮ በጄኔራል ከሊፋ ሃፍጣር የሚመራው ሃይል የሊቢያን መዲና ትሪፖሊን ለመቆጣጠር በሚያደርገው ዘመቻ በተመድ እውቅና ከተሰጠው የፋይዝ አል ሳራጅ አስተዳደር ጋር ግጭት ውስጥ ገብቷል።

በዚህ ግጭት ሳቢያም ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ህይወት ሲያልፍ 5 ሺህ 700 ያህሉ ለአካል ጉዳት ዳርጓል፡፡ ከዚህም ሌላ 120 ሺህ ያህል ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ማፈናቀሉን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲኤ ን/fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሊቢያ የመጀመሪያው ሰው ከቫይረሱ አገገመ!

አንድ (1) ሞትና አስራ ዘጠኝ (19) በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡባት #ሊቢያ በትላንትናው ዕለት የመጀመሪያውን ከኮሮና ቫይረስ ያገገመ ሰው ሪፖርት አድርጋለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

በ21ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም ኃይል እንደሆነች የሚነገርላት አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዛን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ በጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

አሜሪካ እጇን ባስገባችባቸው ሀገራት ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ የምትሞግት ሲሆን በምታካሂዳቸው ዘመቻዎች ከሽብር ጥቃት ዜጎቿን መከላከል /የሀገሯን ደህንነት ማስጠበቅ እንደቻለች በተለያየ ጊዜ ታነሳለች።

@tikvahethiopia
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

#Repost

በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዟን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

#ሶሪያ

አሜሪካ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር ሆና በሶሪያ ጦርነት ውስጥም እጇ ያለበት ሲሆን በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የበሽር አል አሳድ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በምትወስደው እርምጃ የሶሪያ ከተሞች ክፉኛ አውድማለች።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ ጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

@tikvahethiopia
👍3
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ " የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና/ቻን " እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ዝግጅት ዛሬ ሞሮኮ ካዛብላንካ በሰላም መድረሱን የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል። ቡድኑ ወደ ሞሮኮ ከመሄዱ በፊት በሀገር ውስጥ ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል። በሞሮከ የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ለሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የሚያደርግ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ…
#Update

የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና / CHAN AFRICA እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ከምድቡ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

ብሄራዊ ቡድኑ #ከሞዛምቢክ#አልጄሪያ እና #ሊቢያ ጋር በአንድ ምድብ ነበር የተደለደለው። ከሞዛምቢክ 0 ለ 0 ሲለያይ በአልጄሪያ 1 ለ 0 ተሸንፎ ነበር።

በምድብ የመጨረሻው ጨዋታ #ከሊብያ ጋር የገጠመው ብሔራዊ ቡድናችን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከወዲሁ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

ቡድኑ በውድድሩ ላይ በአጠቃላይ 4 ጎሎች ሲቆጠሩበት ማስቆጠር የቻለው አንድ ጎል ብቻ ነው።

በተመሳሳይ ምድብ ውስጥ የነበሩት አልጄሪያ እና ሞዛምቢክ ከምድቡ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

የዘንድሮው የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና እየተካሄደ የሚገኘው በአልጄሪያ ነው።

ተጨማሪ : https://tttttt.me/+VvwzStMNcNHmhK0x    

@tikvahethiopia
👎1.14K👍635😢168🥰52🙏31😱2621🤔18🕊16
#ሊቢያ

በምስራቃዊ ሊቢያ የምትገኘውን " ዴርና " ከተማን በመታው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ምክንያት 2000 የሚደርሱ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

7000 ሰዎችም የገቡበት አይታወቅም ተብሏል።

በቤንጋዚ የሚገኘው የቀይ ጨረቃ ኃላፊ ካይስ ፋከሪ እንደተናገሩት " ዳንኤል " በተባለው አውሎ ንፋስ በዴርና ከተማ ባደረሰው ጥፋት ቢያንስ 150 ሰዎችን ሞተዋል።

በከተማዋ ሁለት ግድቦች መደርመሳቸውም ተነግሯል።

ከቀናት በፊት በሌላኛዋ የአፍሪካ ሀገር #ሞሮኮ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ2000 በላይ ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopia
😢1.16K👍37783🕊50🙏32😱29👎10🥰6