TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዓለምአቀፍ

የጣሊያኗ " ላምፔዱሳ " ደሴት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች።

አዋጁን ያወጀችው ባለፉት ሁለት ቀናት ከአፍሪካ የተነሱ ወደ 8,000 የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ደሴቷ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።

ስድተኞች ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ወደ ጣልያን እየገቡ የሚገኙት በጀልባ ለህይወታቸው እጅግ አስጊ በሆነ መንገድ ተጉዘው ነው ተብሏል።

አንድ ከጊኒ ተነስቶ ጣልያን የገባ ስደተኛ ፤ በሕይወት ተርፎ ጣልያን በመግባቱ ዕድለኛ እንደሆነ ተናግሯል።

ሀገሪቱ አሁን እየገቡ ያሉትን ስደተኞች ወደ ሌሎች የመቀበያ ቦታዎች ለማዘዋወር እየሰራች ነው ተብሏል።

የጣልያን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ማትዮ ሳልቪኒ ፤  በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስደተኞች ጣልያን መድረሳቸውን " የጦርነት አነይት ድርጊትን " ይወክላል ብለዋል።

ሚኒስትሩ " ጣሊያንን ለማተራመስ ሆን ተብሎ የተነደፈ ስልት መሆኑን እርግጠኛ ነኝ " ያሉ ሲሆን ከዚህ ሴራ ጀርባ ማን እንዳለ ለመግለፅ አልወደዱም።

" ከዚህ በስተጀርባ አንድ እቅድ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ " ያሉት ሚኒስትሩ " ከ100 በላይ ጀልባዎች በጥቂት ሰአታት ውስጥ መድረሳቸው ድንገተኛ ሳይሆን የተደራጀ የጦርነት አይነት ድርጊት ነው። " ብለዋል።

" ይህ የሚያመጣው ተፅእኖ በላምፔዱሳ ላይ  ብቻ የሚያበቃ አይደለም ፤ ወደ ሮም፣ ሚላን፣ ቱሪን፣ ኔፕልስ፣ ፓሌርሞ ስለሚሄዱ አሳዛኝ መዘዞችን ያስከትላል። " ሲሉ ተናግረዋል።

ጣልያን ከፍተኛ የስደተኞችን ቁጥር የምታስተናግድ አውሮፓዊት ሀገር ስትሆን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየው ያለው ነገር ውጥረት መፍጠሩ ተገልጿል።

በላምፔዱሳ ያለው ከመደበኛ በላይ ሁኔታ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አስገድዷል።

ባለፉት 2 ቀናት ብቻ 8,000 ከአፍሪካ የተነሱ ስደተኞችን የቀበለችው የጣልያኗ ደሴት ላምፔዱሳ አጠቃላይ የነዋሪዎቿ ብዛት 6000 ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በሌላ በኩል ፤ የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በጣሊያን በኩል ወደ #አውሮፓ የገቡ አዲስ ስደተኞችን ለጊዜው መቀበል እንዳቆመ አስታውቋል።

ጀርመን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ጣልያን ባአውሮፓ ህብረት በኩል በስደተኞች ላይ የተደረሰውን ስምምነት ለማክበር ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው ተብሏል።

የጀርመን መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት " ከፍተኛ የስደተኞች ጫና አለ " በሚል ምክንያት ጀርመን ከጣሊያን የሚገቡ አዲስ ስደተኞችን ላልተወሰነ ጊዜ መቀበል አቋርጣለች።

ፈረንሳይ በበኩሏ ወደ ግዛቷ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ከጣሊያን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የሚገኙ የፖሊስ እና የጦር ሃይሎች ጥበቃን በከፍተኛ ሁኔታ እንደምታጠናክር ይፋ አድርጋለች።

ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያዎች የተገኘ

@tikvahethiopia
👍1.11K😢235158👎46😱41🕊29🙏15🥰6
#ዓለምአቀፍ #ፖላንድ

በፖላንድ ፤ እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ ለቪዛ ያመለከቱ ሰዎች ዝርዝር ላይ #ኦዲት ሊደረግ ነው ተባለ።

በፖላንድ ለአፍሪካውያን በክፍያ ቪዛ እየተሰጠ ነው በሚል መንግሥት ላይ ጥያቄ ማስነሳቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

የፖላንድ የላይኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቶማዝ ግሮዲዚ በአገሪቱ ገንዘብ እየተቀበሉ ቪዛ የመስጠት አካሄድ ተባብሷል ብለዋል።

መንግሥት ስለ ጉዳዩ ምን መረጃ እንዳለው ይፋ እንዲያደርግም ጠይቀዋል። ነገሩ የአገሪቱን ስም እያጠለሸ ነው ብለዋል።

መንግሥት የተወሰነ መረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን ፤ እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ግን ስደተኞች እስከ 5,000 ዶላር እየከፈሉ የሥራ ቪዛ የማግኘት ሂደቱን ያፋጥናሉ ተብሏል።

እስካሁን ሰባት ሰዎች ላይ ክስ ቢመሠረትም ከመካከላቸው የመንግሥት ባለሥልጣን እንደሌለ ታውቋል።

የአገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒዮር ዋውዚክ ፤ ባለፈው ሳምንት ክሶችን ተከትሎ ከሥራ ተነስተዋል። የፖላንድ ፀረ ሙስና ኮሚሽን መሥሪያ ቤቱ ላይ ምርመራ ካደረገ በኋላ ነው የተባረሩት።

የሕግ ክፍሉ ዳይሬክተርም ተባረዋል።

እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ ለቪዛ ያመለከቱ ሰዎች ዝርዝር ላይ ኦዲት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ተቃዋሚ የምክር ቤት አባል ፤ እስከ 250,000 ቪዛዎች ሕግ ሳይከተሉ ለእስያ እና አፍሪካ አመልካቾች ተሰጥተዋል ሲሉ ገልጸዋል።

መንግሥት ግን ቁጥሩ በጥቂት መቶዎች ብቻ የሚቆጠር ነው ሲል አስተባብሏል።

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶናልድ ተስክ ፤ " ከአፍሪካ ፖላንድ መምጣት የፈለገ ሁላ ከኤምባሲያችን ቪዛ ገዝቶ አገራችን በቀላሉ ይገባል " ብለዋል።

የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን ይህ ንግግር ቀውስ እንደሚያስከትል ገልጸው ችግሩ የተባለውን ያህል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

" አገራችን ኃላፊነት የሚሰማት ዴሞክራሲያዊ አገር ሆና ሳለ የነጻውን ዓለም ደኅንነት አደጋ ውስጥ የምትከት ሆና እንድትታይ የሚያደርግ አካሄድ ስለሆነ በጥልቀት ሊብራራ ይገባል። ይህ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትልቁ ቅሌት ነው። ሙስና በመንግሥታችን ተንሰራፍቷል " ሲሉ የላይኛው ምክር ቤት አባል አሳስበዋል።

የፍትሕ ሚኒስተሩ ዚግኒው ዚዎብሮ ፤ ይህ አባባል የተጋነነ ነው ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

ይህ ጉዳይ ከስደተኞች ጉዳይ ጋር በተያያ በቀጣዩ የፓርላማ ምርጫ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር መገለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
👍43564😢13👎12🕊10😱9🥰4🙏2