TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በቅርቡ በሶስት የሀገራችን ከተሞች #ለመጀመሪያ ጊዜ #በአካል_ተገናኝተን በሰላም ጉዳይ እና በሌሎች ለሀገራችን እና ለህዝባችን ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ውይይት እናደርጋለን።

የትኞቹ ከተሞች የሚለውን ሰሞኑን አሳውቃለሁ!!

ሰላም+ፍቅር+አንድነት=ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በፎቶሾፕ ከሚቀናበሩ የምርጫ ውጤቶች ተጠንቀቁ !

የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እያሳወቁ ይገኛሉ።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ናቸው የተባሉ ወረቀቶች እየተለጠፉ ነው።

ነገር ግን ወረቀቶቹ ላይ ያሉትን ቁጥሮች በፎቶሾፕ የመነካካት፣ የማስተካከል ምልክቶችን ታዝበናል።

በተለይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ ፦

1ኛ. ዘመኑ የረቀቀ ነውና የምርጫ ውጤትን በተመለከተ ትክክለኛው ሪፖርት እስኪላክላችሁ ታገሱ

2ኛ. ድምፅ የሰጣችሁበት የምርጫ ጣቢያ #በአካል ተገኝታችሁ የተለጠፈውን ውጤት እንድትመለከቱ እናበረታታለን።

የውጤት ጉዳይ በጥንቃቄ ካልተያዘ እስካሁን የተመጣበትን #ሰላማዊ ሂደትን ሊያበላሽ ስለሚችል ከሀሰተኛ መረጃዎች/በይፋ በምርጫ ቦርድ ካልተረጋገጡ ሪፖርቶች ሁሉ እንድትርቁ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WoldiaUniversity የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ እንዲደረግላቸው ውሳኔ አሳለፈ። የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። ሴኔቱ በዛሬው ዕለት ከስዓት በፊት በነበረው ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ ከነበሩት መካከል የመምህራን የደረጃ እድገት እና የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች የጥሪ ሁኔታን የሚመለከቱ ነበሩ።…
#Update

ከቀናት በፊት የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ እንዲተላለፍላቸው ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለአንደኛ ዓመትና አራተኛ ዓመት የፔዳጎጅካል ሳይንስ መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ አስተላልፏል።

ተማሪዎች ከየካቲት 30/2014ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2014ዓ.ም #በአካል ተገኝተው እንዲመዘገቡ ጥሪ ተላልፏል።

ሌሎች ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እስኪተላለፍ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ዩኒቨርሲቲው መልዕክት አስተላልፏል።

More @tikvahuniversity
👍338👎26👏25😱1813😢7🥰3