TIKVAH-ETHIOPIA
#MinistryofAgriculture : ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአቶ አዲሱ አረጋ ተተኩ። ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ አዲሱ አረጋን የግብርና ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል። ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከግብርና ሚኒስትርነት ተነስተዋል። ለምን ከቦታው እንደተነሱ፣ ለሌላ ኃላፊነት ተፈልገው እንደሆነ፣ ወይም ሌላ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው እንደሆነ ለጊዜው የሚታወቅ ነገር የለም። አዲሱ የግብርና ሚኒስትር አቶ…
#Update
የቀድሞው የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት (ጄኔቫ) የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ተሹመዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ግርማ አመንቴን (ዶ/ር) ለዚህ ትልቅ ኃላፊነት ለመሾም ያሳለፉትን ውሳኔ በአድናቆት እንደምትመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ውሳኔው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች አፍሪካን በመወከል ለምትጫወተው ሚና ሕብረቱ ያለውን ትልቅ ግምት የሚያመላክት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
Via Ministry of Foreign Affairs
@tikvahethiopia

3❤1.02K👏194😡78🙏45🤔40🕊26💔26🥰20😭10😱7