TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኦዲት

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለቋሚ የሥራ ቅጥር መደቦች የቀን ሠራተኞችን በመቅጠር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ መፈጸማቸው ተገለጸ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የመንግሥት ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የበጀት ኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ ነው የተገለጸው፡፡

ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በሪፖርቱ እንደጠቀሰው 12 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይፈቀድላቸው ለቋሚ የሥራ መደቦች ላይ የቀን ሠራተኞችን ቀጥረው ተገኝተዋል ብሏል።

ተቋማቱ በጠቅላላው 61,882,081 ብር ለቀን ሠራተኞች ክፍያ እንደፈጸሙ የገለጸው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ፦
➡️ ጅማ ዩኒቨርሲቲ 25,310,211 ብር፣
➡️ አምቦ ዩኒቨርሲቲ 10,938,834 ብር፣
➡️ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 7,888,374 ብር፣
➡️ ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ 5,170,600 ብርና ዲላ ዩኒቨርሲቲ 4,414,974 ብር በመክፈል ዋነኞቹ እንደሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም 17 የመንግሥት ተቋማት በጡረታ፣ በሞትና በሌሎች ምክንያት ከሥራ ለለቀቁ ሠራተኞች 408,462 ብር ያላግባብ ደመወዝ መክፈለቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር የሠራተኞች ቅጥር፣ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር እንዳይፈጸም ቢከለክልም በስምንት መሥሪያ ቤቶችና በአንድ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በጠቅላላው 24,073,003 ብር የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ሳያስፈቅዱ ለቋሚ የሥራ መደቦች ሠራተኞችን በኮንትራት በመቅጠር ክፍያ ፈጽመዋል ተብሏል፡፡

ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ሳያስፈቅዱ የኮንትራት ቅጥር ከፈጸሙት ተቋማት መካከል ፦
- የቅደስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣
- ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ፣
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋነኞቹ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በ2015 በጀት ዓመትና ከዚያ በፊት በተከናወኑ የኦዲት ሪፖርቶች መሠረት ዕርምጃ የተወሰደ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ በአጠቃላይ እንዲመለስ አስተያየት ከተሰጠበት 20.5 ቢሊዮን ብርና 23,230 ዶላር ውስጥ፣ የተመለሰው ሦስት ቢሊዮን ብርገደማ ብቻ መሆኑን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አስታውቋል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች አገልግሎትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በአጠቃላይ 37,304,100 ብር የአገልግሎት ገቢ ተመናቸውና በሚመለከተው አካል ሳያፀድቁ ገቢ መሰብሰባቸውም ተገልጿል፡፡

እንዲሁም 28 የፌዴራል መሥሪያ ቤቶችና ሰባት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የፈጸሙት 348 ሚሊዮን ብር ክፍያ የተሟላ የወጪ ማስረጃ አልቀረበበትም ተብሏል።

የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ ከተመዘገቡት መሥሪያ ቤቶች መካከል የጤና ሚኒስቴር፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የቤተ መንግሥት አስተዳደር ዋነኞቹ ናቸው።

በ70 የፌዴራል መሥሪያ ቤቶችና በሰባት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከ404 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥትን የግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ ግዥ ተፈጽሞ መገኘቱን ዋና ኦዲተር ገልጿል።
- ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣
- የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣
- የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽንና አርሲ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከሕግ ውጪ ግዥ ከፈጸሙ ተቋማት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።

ስምንት ተቋማት ደግሞ በጠቅላላው ከ6.5 ሚሊዮን በላይ ብር ዋጋ ያላቸውና ተገዝተዋል የተባሉ ንብረቶች እስካሁን ገቢ እንዳላደረጉ ሲገለጽ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ የቤተ መንግሥት አስተዳደርና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ግዥውን ፈጽመው ዕቃዎቹን ገቢ ያላደረጉ

እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት 20 የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ከተመደበላቸው ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ሳይጠቀሙበት ወደ መንግሥት ካዝና ተመላሽ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የዚህ መረጃ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
1.39K😱149😭71😡67🤔58👏27🙏22🕊20🥰19