#ኢትዮጵያ
በግብይት ወቅት ከ 10,000 ብር በላይ ጥሬ ገንዘብን መጠቀም፤ ለከፋዩ በወጪነት፣ ለተቀባዩ ደግሞ አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጣልበት ያደርጋል ተባለ።
አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ሲጸድቅ ከ10,000 ብር በላይ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መፈጸም የሚያስቀጣ ይሆናል ተብሏል።
ረቂቅ አዋጁ ላይ ሃሳብ ለማዋጣት ከተሳተፉ ባለሙያዎች የተወሰኑት ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው አሰራር ላይ ጥያቄ አንስተዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊው አቶ ተወዳጅ መሐመድ እንዳሉት አዋጁ ተግባራዊ የሚደረገው በጥሬ ገንዘብ የሚፈፀም ግብይትን መገደብን ታሳቢ አድርጎ ነው።
በአንድ ግብይት የሚፈፀም የጥሬ ገንዘብ ክፍያ ከ10ሺህ ብር ከበለጠ፣ ትርፉ ብር ለከፋዩ በወጪነት አይያዝም።
ገንዘቡን የተቀበለውም የትርፉን ገንዘብ እጥፍ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚጣልበት ተቀምጧል።
ለምሳሌ ፦ የ20,000 ብር ግብይት በጥሬ ገንዘብ ቢፈፀም ለነጋዴው፣ ከ10 ሺህ ብር በላይ ያለው በወጪነት አይያዝም፣ ለተቀባዩ ደግሞ ከ10,000 በላይ ያለው ቀሪ 10,000 ብር እጥፍ ማለትም 20,000 ብር ይቀጣል እንደማለት ነው።
በረቂቅ አዋጁ ላይ የተሳተፉ፣ በጥሬ ገንዘብ ግብይት እንዲፈፀም ምክንያት የሚሆነውን በንግድ ስርዓቱ ውስጥ ያለውን ችግር መፍታት የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችልና፣በሌሎች መመሪያዎች የጥሬ ገንዘብ ግብይት ስለሚፈቀድ አዋጁ የተናበበ እንዲሆን ጠይቀዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ባሰናዳው ረቂቅ አዋጅ መሰረት ከ10,000 ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ግብይት እንዳይፈፀም የሚጣለው ግዴታ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ በባንኮችና በማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም ይላል።
ሌሎች አዋጁ ተፈፃሚ የማይሆንባቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ዝርዝራቸው ይፋ ይሆናል ይላል ረቂቁ።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
#ShegerFM
@tikvahethiopia

😡3.05K❤1.33K🤔191😭105👏48💔38😱34🥰32😢26🙏26🕊24
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይነበብ🚨 " በወንጀል የተገኘን ንብረት #ህጋዊ_ማስመሰልና #ሽብርተኝነትን_በገንዘብ_የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር " የወጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቀርቧል። በዚሁ ረቂቅ ላይ በክፍል 5 ' ስለ ምርመራ ' ሰፍሯል። ረቂቁ ስለ #ምርመራ ምን ይላል ? - በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ወይም የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት…
#ኢትዮጵያ
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከ #ግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ጸደቀ፡፡
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡
አዋጁ በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ (Under cover investigation) እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው፤ በግዴታ ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያትና ከፈቃዱ ውጪ በሆነ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም ይላል።
የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) በአዋጁ 5/15 ላይ የቀረበው ዐረፍተ ነገር ትንሽ ከባድ መስሎ እንደታያቸው ተናግረው አዋጁ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
" እንደዚህ ዓይነት አዋጅ በተለይ ሽብርን ለመከላከል ለሀገራችን ያስፈልጋታል " ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ተናግረዋል፡፡
‘’ የሆነው ሆኖ ግን ' አንድ ሰው በግዳጅ ላይ እያለ ከግድያ በስተቀር ለሚፈጽመው ወንጀል አይጠየቅም ' ይላል፡፡ አንደኛ ወንጀል ፈጽሟል ይላል፣ ወንጀል ፈጽሞ አለመጠየቅ ትክክለኛ አይመስለኝም፡፡ ወይም ድርጊቶቹ ተዘርዝረው ህጋዊ መብት የተሰጠው ሰው ሚወስዳቸው እርምጃዎች ወንጀል አይደሉም ብለን ማለፍ እንጂ አንድ ሰው በግዳጅ ላይ እያለ ለሚፈጽመው ወንጀል ከግድያ በስተቀር የሚለውን ሰው እንደፈለገ እንዲሆን የሚያደርግ ነው’ " ሲሉ አለሙ (ዶ/ር) ሃሳበቸውን አስረድተዋል፡፡
ሌላ ሙሉቀን አሰፋ የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው " እኔ በግሌ እንደተፎካካሪ የፖለቲካ ሰው አዋጁ ባለሀብቶችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እና የታዋቂ ሰዎችን መብት የሚገድብ ነው " ብለዋል፡፡
" እንዲያውም የመናገር መብትን ይከለክላል የሚል እምነት ነው እኔ ያለኝ " ያሉት የምክር ቤት አባሉ ‘" ምክንያቱም አዋጁን ስናየው በ10 ዓመት ገድቦ ነው የወጣው’ " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" ህግ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው ተግባራዊ መደረግ ያለበት’ " ያሉት አቶ ሙሉቀን " ስለዚህ ከ10 ዓመት ወዲህ ብሎ ማውጣቱ የተወሰኑ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን ለማጥቃት ያሰበ ስለሆነ ለሀገራችንም ጥሩ አይደለም የሚል እምነት አለኝ " ብለዋል፡፡
" በአለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ እንደተገለጸው ሀይልን በመጠቀም፣ ንጹሃንን በማስገደድ አላማቸውን ለማስፈጽም የሚሳተፉ ተዋናዮችን ተጠያቂ ለማድረግ ሳይሆን አዋጁ እየዋለ ያለው በዋነኝነት የመንግስት ተቃዋሚዎችን፣ መንግስት ውስጥ ሆነው መንግስትን የሚተቹትን እና ጋዜጠኞችን ነው " ያሉት ደግሞ ሌላው የምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
" የአዋጁን ዝርዝር ካየንው በጣም አስገራሚ የሆኑ ድንጋጌዎችን ይዟል " ያሉት የምክር ቤት አባሉ " ለምሳሌ የፋይናንስ ድህንነት አገልግሎት አጠራጣሪ ግብይትን ለ7 ቀን አግዶ ማቆየት ይችላል ይላል ያውም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ " ብለዋል፡፡
" አዋጁ በሽፋን ስር ምርመራ የሚያካሄድ መርማሪ ከግድያ ወንጀል ውጭ በሌላ ወንጀል አይጠየቅም ይላል " ያሉት ደሳለኝ ጫኔ(ዶ/ር) " ለምሳሌ መርማሪው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ተደራድሮ ከሆነ ከወንጀለኛው ጋር መቀበሉን ብናውቅ አይጠየቅም ማለት ነው? ማሰቃየት ቢፈጽም፣ የመብት ጥሰት ቢፈጽም አይጠየቅም ማለት ነው? መሆን ያለበት ግን ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው አለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተካተቱ ወንጀሎችን አለመፈጸሙ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሌላው አቶ ዘካሪያስ የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው " አዋጁ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት እንደሚሉት ተቃዋሚን እና የሚዲያ ሰዎችን ለማፈን አይደለም " ብለዋል፡፡
አቶ ሳዲቅ አደም የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው " አዋጁ ጠንከር ያለ መሆኑን ተናግረው ጠንከር ያለበት ምክንያትም ግልጽ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" ያለንበት ቀጠና አስቸጋሪ ነው፤ ሽብርተኝነት የሚበዛበት በመሆኑ የአዋጁ ከበድ ማለት ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከመብት አንፃር ሊታዩ የሚችሉ ነገሮች አሉ ያሉት አቶ ሳዲቅ ከህገ መንግስታችንም ስንነሳ ፍጹም የሚባል መብት የለም " ብለዋል፡፡
" ከመብቶች ሁሉ የላቀ ዋና መብት የሚባለው በህይወት የመኖር መብት ነው ይህ መብትም ፍጹም አይደለም " ሲሉ የተናገሩት የምክር ቤት አባሉ " ስለዚህ መብት የሚባለው ነገር ለህዝብ፣ ለማህበረሰብ እና ለሀገር ድህንነት ሲባል በየትኛውም ሀገር መብቶችን ፍጹማዊ አድርጎ የሚያስቀምጥ የለም " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" ስጋት አድርጎ የሚወስድ ወገን ሊኖር ይችላል ግን ለምን ይሰጋል? " ሲሉ የጠየቁት የምክር ቤት አባሉ " ይህ አዋጅ ሲወጣ ለመጠርጠርም መሟላት ያለበት ነገር አለ ማንኛውም ወገን እነዚህ በአዋጁ የተቀመጡ ነገሮችን ካሟላ አይነካም ዋናው መስፈርቱን ማሟላት ነው " ብለዋል፡፡
" አዋጁ የወጣው በንድፍ ሃሳብ የምንፈራቸውን ለመከላከል ሳይሆን በተግባር እያየን እየኖርንበት ያለውን ነው " የሚሉት አቶ ሳደቅ " ሽብርተኝነት በሀገራችን በስፋት አለ ኤ ቤ ሲ ብለን ልንጠራቸው የምንችላቸው ግለሰቦች እና ወገኖች አሉ ስለዚህ ይህን ለመከላከል ለምን እንሰጋለን " ብለዋል፡፡
የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሮ በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ የሚደረገው ምርመራ ልዩ መሆኑን ተናግረው አዋጁ አንድን ቡድን ለማጥቃት ታስቦ የወጣ አይደለም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው በማሻሽያ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ በሶስት ተቃዉሞ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

❤1.04K😭959😡363🤔66😱28💔28😢20🕊16🙏14🥰5👏5
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከ #ግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ጸደቀ፡፡ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡…
አዋጅ ቁጥር 1387/2017
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ‘ን ለማሻሻል የወጣው ሰሞኑም የፀደቀውን አዋጅ ቁጥር 1387/2017ን በተመለከተ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ምን አለ ?
" ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር ተቋም ያቋቋመችው በ2002 ዓ.ም ነው።
በዚህም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተቋቁሟል፤ ተልዕኮው ደግሞ ሀገራችን የአለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል የሚባለው ምከረሃሳብን መተግበር ከሚጠበቅባቸው ከ200 በላይ ሀገራት አንዷ በመሆኗ ነው።
የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል 40 ቀጥታ አባል አገራት አሉት፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዘጠኝ ቀጠናዊ አባል ሀገሮች አሉ።
ከአፍሪካም ሶስት የምስራቅ እና ደቡቡን የሚያካትተው 21 አባል ሀገሮችን የያዘው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካን የያዘው ኢስተርን ኤንድ ሶውዘርን አፍሪካ አንቲ ላውንድሪ ግሩፕ (eastern and southern africa anti money laundry group) ይባላል፡፡
ኢትዮጵያም ከ21 አባል ሀገራት አንዷ ናት።
እነዚህ አባል ሀገራት የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችሉ 40 ምክረ ሃሳቦችን ይተገብራሉ፤ በየአምስት ዓመቱም የእርስ በእርስ ግምገማ ያካሂዳሉ ያሉት ሶስተኛውም ገምገማ በመጪው ዓመት ይካሄዳል።
እነዚህን ምከረ ሃሳቦች ተግበባራዊ ከምናደርግባቸው ህጎች አንዱ ባለፈው የተሸሻለው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ነው።
የተሸሻለው አዋጅ ኢትዮጵያ ለ12 ዓመታት ስተገለገልበት ቆይታለች። የተሸሻለበት ምክንያት ደግሞ አለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ምክረሃ ሃሰቦቹን እያሻሻለ በመሄዱ ነው።
በዚህም የተሸሻሉ ምከረ ሃሳቦች ስላሉ እነሱን ሊመልስ የሚችል ህግ በማስፈለጉ እና ግብረ ሃይሉም ወንጀሎች እየተለዋወጡ ስለመጡ ሀገራት እነሱን ለመከላከል የሚመጥን የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ስለሚያዝ ነዉ።
የቀድሞው አዋጅ አመንጪ ወንጀሎችን በዝርዝር አያስቀምጥም ይህም አንዱ የአዋጁ ችግር ነበር " ብሏል።
#MinistryofJustice #FinancialIntelligenceService #ShegerFM

❤525😡126🤔13😭11🙏9🕊8👏6😱5😢4💔4🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
አዋጅ ቁጥር 1387/2017 በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ‘ን ለማሻሻል የወጣው ሰሞኑም የፀደቀውን አዋጅ ቁጥር 1387/2017ን በተመለከተ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ምን አለ ? " ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን…
#UndercoverInvestigation
" ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን አዋጁ አይፈቅድም " - የፍትሕ ሚኒስቴር
የፍትሕ ሚኒስቴር ፤ በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን እንደማይፈቅድ አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ሰሞኑን በፓላማው የፀደቀውን የተሻሻለ አዋጅ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።
በዚህም " አዋጁን አንዳንዶች የተረዱበት መንገድ ልክ አይደለም " ብሏል፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴር ምን አለ ?
" አዲሱ አዋጅ ከመደበኛ የወንጀል መርመራ ሂደት የወጣ መንገድን የሚከተል እንደሆነ ሰው ሊረዳው ይገባል።
አዲሱ አዋጅ ልክ በመደበኛው የምርመራ ሂደት እንደሚደረገው ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት መያዣ መያዝ ፣ ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ ምስከሮችን መስማት እና መሰል ሂደቶችን አይከተልም።
አዋጁ ወስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን ከመሰረቱ ለመለየት የሚስችል የምርመራ ሂደትን የሚከተል ነው።
ለምሳሌም፦ መርማሪው አካል ወንጀለኞችን መስሎ ተቀላቅሎ ወይንም አብሮ በመስራት፣ ተባባሪ መስሎ አብሮ ውሎ በማደር፣ ሲሸጡ ገዢ መስሎ ፣ ሲገዙ ሻጭ መስሎ ሊሆን ይችላል።
ምርመራውን የሚየካሂደው አካል ምረመራ ማድረግ የሚችለው የፍርድ ቤት ተዕዛዝ ካገኘ ብቻ ነው።
ፍርድ ቤት በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ ተግባራዊ እንዲደረግ በአሳማኝ ምክንያት ሲፈቅድ ምርመራው የሚፈጸምበትን ዘዴ ፣ የአተገባበር ሁኔታ ፣ የሚከናወንበትን ጊዜ በትዕዛዙ ላይ በግልጽ ማስቀመጥ እንዳለበት አዋጁ ደንግጓል።
እንደሚባለው አዋጁ ተጠርጣሪን አስሮ እያሰቃዩ አይመረምርም ይህም ፍጹም ስህተት ነው። በማስገደድ ማስረጃ የሚሰበሰብበትም አይደለም።
መርማሪው ፍርድ ቤት አሳማኝ ምክንያት ሲፈቅድለት በሽፋን ስር የሚደረግ ልዩ የምርመራ ዘዴን ይተገብራል ሲባል በተጠርጣሪዎች ወይም በሌላ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ወንጀል ሊፈጽምባቸው ይችላል፤ ወንጀሉን ከፈጸመባቸው በኋላ በወንጀል አይጠየቅም የሚል አይደለም።
ከተጠርጣሪዎች ጋር የወንጀል ተካፋይ ወይም ግብረ-አበር በመሆን በራሱ ፈቃድ አስቦና ፈቅዶ ሳይሆን ፦
- ያለፈቃዱ፣
- ተገዶ፣
- በተጽእኖ፣
- በተጠርጣሪዎች ሕገ ወጥ ትዕዛዝ ወይም ከአቅሙ በላይ በሆነ ማንኛውንም ምክንያት ሌላ ከባድ ጉዳትን ለማስቀረት ወይም የተሰጠውን ሕጋዊ ተልእኮ ለማሳካት ሲል ወንጀል የሚፈጽምበት ሁኔታ ሲኖር ከወንጀል ክስ #ነጻ የሚደረግበትን ሁኔታ ለማመላከት የተደነገገ ድንጋጌ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። " ብሏል።
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ከሰሞኑ መፅደቁ ይታወሳል፡፡
ይህም መርማሪዎችን ወንጀል እንዲፈፅሙ በር ይከፍታል በሚል ከምክር ቤት ትችት ሲቀርብበት ነበር።

❤1.16K😡270🙏62🤔51😭31😢20🕊20💔19👏17😱4🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ እንደሚሻሻል ተገልጿል። ዛሬ 48ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ተካሂዶ የአዋጁ መሻሻል ላይ ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ " ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ አሁን ከምንገኝበት ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ሲታይ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት ነው " ብሏል። " የአዋጁን ድንጋጌዎች በማሻሻል የታክስ ስርአቱ…
#Ethiopia🇪🇹
" አሁን የ2,000 ብር ደሞዝ የለም በሌለ ነገር ከዚያ በታች ያለው ነጻ ነው ብንል ታክስ መቀነስ አይደለም ! " - የምክር ቤት አባል
በገቢ ግብር ማሻሽያ አዋጅ ላይ ዝቅተኛ የግብር ከፋይ መነሻ ደመወዝ 5,000 ብር እንዲሆን በምክር ቤት ተጠየቀ፡፡
ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዛሬ ከሰዓት በጠራው ልዩ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
አሁን በስራ ላይ ያለው የገቢ ግብር አዋጅ ከዘመኑ የኢኮኖሚ ሁኔታ አብሮ እንደማይሄድ እና ከዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር እንደማይጣጣም በአዋጁ ላይ በቀረበው አጭር ማብራርያ ተመላክቷል፡፡
የማሻሽያ አዋጁን በተመለከተ ሃሳብ የሰጡት የምክርቤት አባሉ አቶ ባርጠማ ፍቃዱ ምን አሉ ?
- በአዋጁ አንቅጽ 11 ላይ የቀድሞው ተሰርዞ አዲስ ሃሳብ ገብቷል። ከዚህ በፊት ተቀጣሪ ከደሞዘ የሚከፍለው ግብር ከ600 ብር በላይ ጀምሮ ነው። ተሻሽሎ በቀረበው አዋጅ ግን ከ600 ብር ወደ 2,000 ብር አድጓል።
- በመሰረቱ 2 ሺ ብር አሁን በአገራችን የሚቀጠር ሰው የለም።
- ከዚህ ቀደም በመንግስት ተቋም ጽዳት ፣የጉልበት ስራ እና የመሳሰሉ ስራዎች ነበሩ ከ600 ብር እስከ 1,000 ብር ደሞዝ አሁን ባለው ሁኔታ ከ4,500 ብር በላይ ነው ቅጥር ያለው።
- አሁን የ2,000 ብር ደሞዝ የለም በሌለ ነገር ከዚያ በታች ያለው ነጻ ነው ብንል ታክስ መቀነስ አይደለም።
- ቢያንስ እንኳን ዝቅተኛ ተቀጣሪው ከግብር ነጻ ቢሆን ጥሩ ነው።
- ግብር ከፋይዉም ከ5,000 በላይ ያለው ስራተኛ ቢሆን።
- የ35 በመቶ ግብር እንዲከፍል የተቀመጠው ከ14ሺ 100 በላይ ነው። ይህም ከወቅቱ ገበያ አንጻር ሲታይ ምንም ነው፤ በዚህ ላይ 35 በመቶ ግብር ሲቆረጥበት ደግሞ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ወደ 20 ሺ በላይ ከፍ ቢል።
- በስራ ላይ ባለው አዋጅ #መነሻ_ግብር 10 በመቶ ነው። ተሻሽሎ በቀረበው ረቂቅ አዋጁ ግን 15 በመቶ ብሎ ነው የሚጀምረው ይህም ወደ ቀድሞው ወደ 10 በመቶ ቢመለስ ሲሉ ጥሩ ነው።
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን በስራ ላይ ባለው አዋጅ ላይ ያለው ከፍተኛ ግብር የሚከፈልበት ደሞዝ በተሸሻለው አዋጅ የዝቅተኛ ግብር መነሻ እንዲሆን መጠየቁ ይታወሳል።
ኮንፌደሬሽኑ የሰራተኛውን ኑሮ ያገናዘበ የገቢ ግብር ማሻሽያ እንዲደረግም ጠይቆ ነበር፡፡
ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህበረተሰብ ክፍል ፦
- የሚያርፍበትን የግብር ጫና መቀነስ፤
- የግብር መሰረትን ማስፋት፤
- የግብር ስርአቱ ላይ የሚታዩ የፍትሃዊነት ችግሮችን መቅረፍ፤
- የአነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች የግብር አከፋፈል ስርአት ቀላል እንዲሆን ማድረግ፤
- ከአዋጁ አላማዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል፡፡
ም/ቤቱ እነዚህን እና ሌሎች ከአባላት የተነሱ ሃሳቦች ታክለውበት ረቂቅ አዋጁ ለፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳይዎች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቶታል፡፡

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1.85K👏245🙏64😡60😢43🕊23😭22🤔20😱19🥰7