TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🚨#Alert

በትግራይ ክልል ላጋጠመ የደን ቃጠሎ የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠየቀ። በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ እንዲደረግ ነው የተጠየቀው።

የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዛሬ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም ለፌደራል የአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን በደብዳቤ እንዳስታወቀው ፤ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወረዳ ቃልአሚን ቀበሌ  ሓይለ-ቡሐለ ልዩ ቦታ በሚገኘው የዱስኣ ጥብቅ ደን የእሳት ቃጠሎ አጋጥሟል።

" በዓፋር ክልል ልዩ ቦታ ገረብ ዋሕለ የጀመረው ቃጠሎ በሃይለኛ ንፋስ እየተስፋፋ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል " ብሏል።

" የአከባቢው ማህበረሰብ ቃጠሎው በባህላዊ መንገድ ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል " ያለው ኮሚሽኑ " ባለው ደረቅ የአየር ሁኔታና ሃይለኛ ንፋስ እየተባባሰ የከፋ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው " ሲል ገልጿል።

የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ከአከባቢው ማህበረሰብ አቅም በላይ በመሆኑ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደርና የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠይቋል።

የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ለማዋል የፌደራል መንግስት በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ በአስቸኳይ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
1.03K😢257😭116🕊84🤔29😡23👏22🙏22😱19🥰4
#Alert🚨

" በጥቆማው መሰረት መድኃኒቱ ችግር ያለበት መሆኑን በመታወቁ ከሁሉም ተቋማት እንዲወገድ ተደርጓል " - የምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን

የኢትዮጵያን ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን " NURATION (10mg Thiamine monohydrate+3mg Pyridoxine Hydrochloride+15mcg Cyanocobalamin) sugar coated tablet supplement " የተሰኘ መድኃኒት ከደረጃ በታች ሆኖ በመገኘቱ ማህበረሰቡ እንዳይጠቀመው አሳስቧል።

ይህ ከደረጃ በታች የሆነ ፕሮዳክት የ ሦስት (ቢ 1 ፣ቢ 6 እና ቢ 12 የተሰኙ) ቫይታሚኖች ስብጥር ሲሆን የቫይታሚን እጥረት እና የነርቭ ችግር ላለባቸው ሰዎች የሚታዘዝ መድኃኒት መሆኑን ባለሥልጣኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ባለሥልጣኑ " በህጋዊ መንገድ የተመዘገበው መድኃኒት ገበያ ላይ አለ ነገር ግን በማመሳሰል የተሰራው እና ማህበረሰቡ እንዲያውቀው ያልነው መድኃኒት ከህጋዊው መድኃኒት ጋር በይዘት (Content) በማመሳሰል ገበያ ላይ የወጣውን ነው "  ብሏል።

ሃሰተኛው መድኃኒት ማሸጊያ ላይ " Zhejiang Medicine and Health care product " የሚል ጽሁፍ ስለመኖሩም አሳውቋል።

በኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን የመድኃኒት ደህንነት እና ማርኬቲንግ ሰርቬላንስ ዴስክ ሃላፊ አቶ ተሽታ ሹቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" ይህ ቫይታሚን ከፍተኛ የሆኑ የ ይዘት (Content) ችግር አለበት።

የተቀመጡት ቫይታሚኖች መጠንም :-

° ' ቫይታሚን ቢ 1 ' 100 mg መሆን ሲገባው የያዘው 10 mg ነው።

° ' ቫይታሚን ቢ 6 ' 200 mg መሆን ሲገባው የያዘው 3 mg ነው።

° ' ቫይታሚን ቢ 12 ' 1000 micro gram መሆን ሲገባው የያዘው 15 micro gram ብቻ ነው።

ይህ ከፍተኛ የሆነ የይዘት ልዩነት ከመኖሩም በላይ መድኃኒት ነው ብለን መጥራትም አንችልም።

እስካልተመዘገበ እና ፈዋሽነቱም እስካልተረጋገጠ ድረስ በአናሳ ሚሊ ግራምም ቢሆን መድኃኒት ነው ብለን የምንቀበልበት ምክንያት የለም።

ህብረተሰቡ መድኃኒት ነው ብሎ እንዳይጠቀም፣ ጤና ባለሞያዎችም እንዳያዙ፣ የክልል ተቆጣጣሪዎችም የራሳቸውን እርምጃ እንዲወስዱ በሚል አሳውቀናል።

ይህንን ያሰራጨው አቅራቢ የብቃት ማረጋገጫው ተሰርዞበታል በህጋዊ መንገድም ፍርድ ቤት ይቀርባል።

ራስ ደስታ ሆስፒታል በጨረታ ከአቅራቢው እነዚህን መድኃኒቶች ወስዶ እየተጠቀመው ነበር።

መድኃኒቱ በ ጴጥሮስ ሆስፒታል ላይ እጥረት ባጋጠመበት ወቅት በመንግስት ሆስፒታሎች መካከል የመድኃኒቶች የውስጥ ዝውውር ስለሚፈቀድ ከራስ ደስታ ሆስፒታል የተጠቀሰው መድኃኒት ወደ ጴጥሮስ ሆስፒታል በሄደበት ወቅት ከጴጥሮስ ሆስፒታል ለ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ መድኃኒቱ ችግር ያለበት ስለመሆኑ ጥቆማ ደርሷል።

በጥቆማው መሰረት መድኃኒቱ ችግር ያለበት መሆኑን በመታወቁ ከሁሉም ተቋማት እንዲወገድ ተደርጓል።

በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ ሌላ ቦታ የተጠቀሰው ፕሮዳክት አለ ወይ የሚል ማጣራት ተደርጓል ባጣራነው መሰረትም መድኃኒቱን አላገኘንም በሁለቱ ሆስፒታሎች የነበረውም እንዲወገድ ተደርጓል።

አቅራቢውም በፍርድ ቤት ለመጠየቅ እየተንቀሳቀስን ነው " ብለዋል።

NB. ህጋዊው እና ህገወጥ መድኃኒቱ ስላላቸው ልዩነት ከተያያዘው ምስል ላይ ይመልከቱ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
1.09K😭83🙏55🤔16😱16🕊13😡11👏9🥰8😢7💔5