TIKVAH-ETHIOPIA
" ነጻ፤ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያለ ሰላምና መረጋጋት ውጪ ሊታሰቡ አይችልም " - የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር " ሰላምን በማጽናት የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና " በሚል ጉዳይ ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የውይይት መድረክ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል። በዚህ መድረክ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት…
#Update
የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር " ሰላምን በማጽናት የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና " በሚል መሪ ቃል በቢሾፍቱ ሲያካሂድ የነበረውን የሰላም ኮንፈረንስ ' የቢሾፍቱ ቃልኪዳን ' መግለጫ በማውጣት አጠናቋል።
ይህ ቢሾፍቱ ቃልኪዳን መግለጫ 7 አንቀጾችን የያዘ ነው።
ቃልኪዳኑ ምን ይላል ?
አንቀጽ 1. ሠላማዊና የሠለጠነ የፖለቲካ አካሄድ የመከተል ቃል ኪዳን።
" የፖለቲካ ዓላማችንን በዲሞክራሲያዊ እና በሕግና በስርዓት እናከናወናለን " ብለዋል።
" ጸጥታን በማደፍረስ፣ የስም ማጥፋትና ጥላቻ እንዲሁም ለሰዉ ህይዎትና ንብርት መጥፋት ምክንያት ባላመሆን ለሰላም እንተጋለን " ሲሉ ገልጸዋል።
አንቀጽ 2 ፦ ለዲሞክራሲ ተቋማትና እሴቶች ክብር የመስጠት ቃል ኪዳን።
" ሕግና ሥርዓት፣ የህዝብ ውሳኔ ወሳኝነት፣ የምርጫ ሂደቶችና ዉጤት እንዲከበሩ " እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
" በውሳኔዎች ላይ ልዩነት ቢኖር እንኳ ህጋዊነትን በማክበር አቋማችንን እናራምዳለን " ብለዋል።
አንቀጽ 3 ፦ ለአካታችነት፣ ለሀገራዊ መግባባትና ብሄራዊ ጥቅም አብሮ የመቆም ኪዳን።
" ያሉንን ልዩነቶችን ክብርና ልዩ ትኩረት በመስጠት ለህብረብሄራዊነት እሳቤ ግንባታ ለመስራት ተስማምተናል " ሲሉ አሳውቀዋል።
የወጣቶች፣ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እንድያድግ በትኩረት እንደሚሰሩና ለብሄራዊ ጥቅም አብሮ የመቆም የፖለቲካ ባህል እንደሚገነቡ ገልጸዋል።
አንቀጽ 4 ፦ ለዲሞክራሲያዊ መልካም አስተዳደር መስፈን የመስራት ቃል ኪዳን።
" በአጀንዳ፣ በፖሊሲ፣ በችሎታ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት ለመገንባት እንሰራለን። የተለያዩ የፖለቲካ አስተሰሰብና ፍላጎት መኖር እንደ ጤናማ ዲሞክራሲ ምልክት እንቀበላለን " ብለዋል።
አንቀጽ 5 ፦ የግጭት አያያዝ እና የሰላም ግንባታ ዉጤታማነት የመስራት ቃል ኪዳን፡፡
" በየፓርቲዎቻችን ውስጥና በሌሎች ፓርቲዎች መካከል ለግጭቶች ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ የመፍትሄ ሥርዓቶችን እንገነባለን " ያሉ ሲሆን " በማህበረሰብ፣ በአካዳሚያ፣ በተለያዩ መድረኮች እና ከፖለቲካ አመራሮች ጋር በሚካሄዱ የሰላም ውይይቶች በአጋርነት እንሳተፋለን " ብለዋል።
አንቀጽ 6 ፦ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የመዳበር ቃል ኪዳን፡፡
" በመንግስት እንዲሁም በፓርቲያችን ውስጥ ግልጽነት፣ የሐሳብ ነጻነትና መተማመን እንዲጎለብት እንተጋለን። የህዝብ ተሳትፎ የሚገድብ ሥራ እና ተቋማዊነት የሚጎዳ የፖለቲካ አካሄድ በጋራ አንታገላለን " ሲሉ በቢሾፍቱ ቃልቂዳን ላይ አስፍረዋል።
አንቀጽ 7 ፦ ለብሄራዊ ጥቅም እና ለዲሞክራሲ ስርዓት የመጽናት ቃል ኪዳን፡፡
" በሰላም፣ በዉጫዊ ችግሮች፣ በብሄራዊ ምርጫ እና በመንግሥት ልማት አካል እንደአንድ አካል እንሰራለን። በኢትዮጵያ የዜጎችና ህዝቦች ክብር እና በሀገራች የጋራ ዕጣ ፋንታችን ላይ በጋራ በመቆም ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት ለማጽናት እንሰራለን " ብለዋል።
#EthiopianPoliticalPartiesJointCouncil
#MinistryofPeace
@tikvahethiopia

❤457😡119🤔23😭14🕊13🙏9😱6😢5🥰4💔4