TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሐይማኖት ሐገር የሆነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህልና ልምድ  ያላት ሀገር ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት መቸገር  የለባቸውም ! " - የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና  የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ሚኒስትሩ በሰላም…
" የሃይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነት ለሰላም ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና አለው " - አቶ መሀመድ እድሪስ

የሰላም ሚኒስትር ከሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች ጋር እያደረጉ ያሉትን ትውውቅና ውይይት ቀጥለው ዛሬ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር ተገናኝተዋል።

በዚህም ወቅት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ፥  " የሃይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነት ለሰላም ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና አለው " ብለዋል።

" በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳይ ሰላማዊና የተረጋጋ ማህበረሰብ እንዲኖር የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ አስተዋፆ ሊኖራቸው ይገባል "  ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በቀጣይ በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ እያከናወነ ያለውን  ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተው የሰላም ሚኒስቴርም በትብብርና በቅንጅት ከካውንስሉ ጋር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ፤ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) ፥ ከመገፋፋት ይልቅ በመተባበር እና በመደጋገፍ ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ሃይማኖቶች ትልቅ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ሲሰራ የቆያቸውን የሰላም ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በሀገራችን ሰላም ጉዳይ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነ አሳውቀዋል።

#MinistryofPeace

@tikvahethiopia
🕊160😡9557🤔11👏9🥰8😭6😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
" ነጻ፤ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያለ ሰላምና መረጋጋት ውጪ ሊታሰቡ አይችልም " - የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር " ሰላምን በማጽናት የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና " በሚል ጉዳይ ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የውይይት መድረክ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል። በዚህ መድረክ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት…
#Update

የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር " ሰላምን በማጽናት የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና " በሚል መሪ ቃል በቢሾፍቱ ሲያካሂድ የነበረውን የሰላም ኮንፈረንስ ' የቢሾፍቱ ቃልኪዳን ' መግለጫ በማውጣት አጠናቋል።

ይህ ቢሾፍቱ ቃልኪዳን መግለጫ 7 አንቀጾችን የያዘ ነው።

ቃልኪዳኑ ምን ይላል ?

አንቀጽ 1. ሠላማዊና የሠለጠነ የፖለቲካ አካሄድ የመከተል ቃል ኪዳን።

" የፖለቲካ ዓላማችንን በዲሞክራሲያዊ እና በሕግና በስርዓት እናከናወናለን " ብለዋል።

" ጸጥታን በማደፍረስ፣ የስም ማጥፋትና ጥላቻ እንዲሁም ለሰዉ ህይዎትና ንብርት መጥፋት ምክንያት ባላመሆን ለሰላም እንተጋለን " ሲሉ ገልጸዋል።

አንቀጽ 2 ፦ ለዲሞክራሲ ተቋማትና እሴቶች ክብር የመስጠት ቃል ኪዳን።

" ሕግና ሥርዓት፣ የህዝብ ውሳኔ ወሳኝነት፣ የምርጫ ሂደቶችና ዉጤት እንዲከበሩ " እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

" በውሳኔዎች ላይ ልዩነት ቢኖር እንኳ ህጋዊነትን በማክበር አቋማችንን እናራምዳለን " ብለዋል።

አንቀጽ 3 ፦ ለአካታችነት፣ ለሀገራዊ መግባባትና ብሄራዊ ጥቅም አብሮ የመቆም ኪዳን።

" ያሉንን ልዩነቶችን ክብርና ልዩ ትኩረት በመስጠት ለህብረብሄራዊነት እሳቤ ግንባታ ለመስራት ተስማምተናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

የወጣቶች፣ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እንድያድግ በትኩረት እንደሚሰሩና ለብሄራዊ ጥቅም አብሮ የመቆም የፖለቲካ ባህል እንደሚገነቡ ገልጸዋል።

አንቀጽ 4 ፦ ለዲሞክራሲያዊ መልካም አስተዳደር መስፈን የመስራት ቃል ኪዳን።

" በአጀንዳ፣ በፖሊሲ፣ በችሎታ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት  ለመገንባት እንሰራለን። የተለያዩ የፖለቲካ አስተሰሰብና ፍላጎት መኖር እንደ ጤናማ ዲሞክራሲ ምልክት እንቀበላለን " ብለዋል።

አንቀጽ 5 ፦ የግጭት አያያዝ  እና የሰላም ግንባታ ዉጤታማነት የመስራት ቃል ኪዳን፡፡

" በየፓርቲዎቻችን ውስጥና በሌሎች ፓርቲዎች መካከል ለግጭቶች ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ የመፍትሄ ሥርዓቶችን እንገነባለን " ያሉ ሲሆን " በማህበረሰብ፣ በአካዳሚያ፣ በተለያዩ መድረኮች እና ከፖለቲካ አመራሮች ጋር በሚካሄዱ የሰላም ውይይቶች በአጋርነት እንሳተፋለን " ብለዋል።

አንቀጽ 6 ፦ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የመዳበር ቃል ኪዳን፡፡

" በመንግስት እንዲሁም በፓርቲያችን ውስጥ ግልጽነት፣ የሐሳብ ነጻነትና  መተማመን እንዲጎለብት እንተጋለን። የህዝብ ተሳትፎ የሚገድብ ሥራ እና ተቋማዊነት የሚጎዳ የፖለቲካ አካሄድ በጋራ አንታገላለን  " ሲሉ በቢሾፍቱ ቃልቂዳን ላይ አስፍረዋል።

አንቀጽ 7 ፦ ለብሄራዊ ጥቅም እና ለዲሞክራሲ ስርዓት የመጽናት ቃል ኪዳን፡፡

" በሰላም፣ በዉጫዊ ችግሮች፣ በብሄራዊ ምርጫ እና በመንግሥት ልማት አካል እንደአንድ አካል እንሰራለን። በኢትዮጵያ የዜጎችና ህዝቦች ክብር እና በሀገራች የጋራ ዕጣ ፋንታችን ላይ በጋራ በመቆም ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት ለማጽናት እንሰራለን " ብለዋል።

#EthiopianPoliticalPartiesJointCouncil
#MinistryofPeace

@tikvahethiopia
457😡119🤔23😭14🕊13🙏9😱6😢5🥰4💔4