TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው " - አቶ አማኑኤል አሰፋ በደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህ መግለጫቸው ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በባለፈው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመሆናቸው " ፕሬዝደንትነታቸውን አንቀበልም " ብለዋል። አቶ ጌታቸውን…
#TPLF

ለመሆኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ' የቀድሞው ' ከተባሉ ክልሉን (ትግራይን) ማነው እያስተዳደረ ያለው ? ይህ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሚመራው ህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ የቀረበ ጥያቄ ነው።

አቶ አማኑኤል አሰፋ ይህን ጥያቄ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳን " የቀድሞው ፕዜዳንት " ብለው በመጥራታቸው ነው።

" የፕሬዜዳንት ውክልና ሲነሳ ፕሬዜዳንቱ በሌለበት ማን እንደሚሰራ ይታወቃል " ያሉት አቶ አማኑኤል " ኃላፊ በሌለበት ጊዜ እሱን ተክቶ የሚሰራ እንዳለ ይታወቃል ምንም የስልጣን ክፍተት አይፈጠርም ህወሓት የወከላቸውን የተወሰኑ ሰዎች ውክልና አንስቷል ውክልናውን ስላነሳን ነው የቀድሞ ፕሬዜዳንት የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት " ሲሉ ለተነሳው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።

በግልጽ አሁን ላይ በእሳቸው አመለካከት ክልሉን ማን እየመራ እንዳለ አልጠቀሱም።

" ፕሬዝዳንቱን የሚተካ ሰውን በሚመለከት ህወሓት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እየተነጋገር ነው " ያሉት አቶ አማኑኤል " ውጤቱ ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

እዚህ ላይም ከየትኛው የፌዴራል አካል ጋር ንግግር እያደረጉ እንደሆነ በግልጽ አልተናገሩም። የፌዴራል መንግሥትም በህወሓት ክፍፍል ጉዳይ ምንም ቃል ሰጥቶ አያውቅም።

በሌላ በኩል ፤ ከቀናት በፊት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን ክፍፍልና ልዩነት ካልፈቱ የክልሉን አስተዳደር ፌዴራሉ መንግሥት ሊይዘው እንደሚችል ማሰስቡን ገልጸው ነበር።

አቶ አማኑኤል ግን " ይህ ከሀቅ የራቀ ነው " ሲሉ አጣጥለዋል።

" ' እዚህ ተስማምተን ካልተንቀሳቀስን 'የጊዜያዊ አስታዳደሩን ስልጣን ብልፅግና ይረከበዋል ተብሏል ' ተብሎ የተነገረው ፍጹም የተሳሳተ ነው ወደዚህ ደረጃም አልደረስንም እንዲህ አይነት መልስም አልተሰጠም። ከፌዴራል መንግሥት ጋር የተጀመረው ውይይት ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪ አቶ አማኑኤል አሰፋ ፦
° ከባለፈው ጉባኤ በኃላ ፓርቲያቸው በወረዳና ከተሞች የአመራር ማስተካከያ ማድረጉን ፤
° የወረዳና ከተማች ምክር ቤት በህወሓት አብላጫ ወንበር የተያዘ በመሆኑ የተሻለ አመራር መመደቡን፤
° በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚገኙ ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ 13 አመራሮች ውክልና ቀድሞ መነሳቱን ገልጸዋል።

" ህወሓትንም ሆነ የመንግሥት ስልጣንን በተመለከተ ድርድር አይደረግም " ያሉ ሲሆን " በመቶ ሺህ የሚቆጠር አባል ያለው ፓርቲ ነው ያለን ከፓርቲው የወጡ ሰዎች መመለስ ከፈለጉ በአሰራሩ መሰረት የይቅርታ ደብዳቤ በማስገባት ነው መመለስ የሚችሉት " ብለዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የደብረጽዮን (ዶ/ር) ቡድን አስተዳደሩ ስራ እንዳይሰራ እንቅፋት ከመሆን ባለፈ የወረዳ ምክር ቤቶችን በመጠቀም አስተዳዳሪዎችን ከቦታቸው እንዲነሱ እያደረገ ነው ይህ " መፈንቅለ መንግሥት ነው " ብለው ነበር።

#VOATigrigna

#TPLF #Tigray

@tikvahethiopia
😡428272🕊113🤔75😭31😢25👏22😱22🙏21🥰13
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Adigrat

🚨 " በር ሰብረው ነው የገቡት " - አቶ ኪዱ ገብረ ፃድቅ (የትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የፀጥታ ኃላፊ)

➡️ " እኛ በር ሰብረን አልገባንም ህዝቡ ግቡ ብሎ በሰልፍ ስለመጣ ነው " - አቶ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔር


ከዚህ ቀደም የዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባዎች (አንድ በጊዜያዊ አስተዳደሩ አንድም እነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት) እንደተሾሙባት ይታወቃል።

ማክሰኞ በደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ቡድን የተሾሙት ከንቲባ በሰራዊት ኃይል በመታገዝ በኃይል በር በመስበር ፅ/ቤቱን እንደያዙት የምስራቃዊ ዞን የፀጥታ ኃላፊ አቶ ኪዱ ገብረ ፃድቅ አሳውቀዋል።

አቶ ኪዱ ገብረ ፃድቅ ምን አሉ ?

" የሰራዊቱ አመራሮች ' በምክር ቤት ለተመረጠው ከንቲባ አስረክቡ ' በማለት ወደ ከተማዋ ሰራዊት አስገብተዋል። ወደ ከንቲባ ፅ/ቤትም በኃይል ገብተዋል። ቁልፍ የላቸውም ሰብረው ነው የገቡት " ብለዋል።

አቶ ኪዱ ሰኞ ዕለት በዓዲግራት መግቢያ ቤተ ሓርያት በተባለ አካባቢው " ወጣቶች እያደራጃቹ ነው " በሚል በፀጥታ ኃይሎች ለ 4 ሰዓታት ታግተው ነው የተለቀቁት።

ማክሰኞ ቁልፍ ሳይኖራቸው በሩን ሰብረው ገብተዋል የተባሉት አቶ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔር ፤ " ሰብረን አልንገባንም " ብለዋል።

አቶ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔር ምን አሉ ?

" በህዝብ ሳይመረጥ በራስ ፍላጎት ብቻ በስልጣን ላይ የመቆየት ፍላጎት ስለነበረ ህዝቡ አገልግሎት አጥቶ ለሶስት ወራት ቆይቷል።

እኔ በምክር ቤት ተሹሜ ለሶስት ወራት ፅ/ቤት ሳልገባ መንገድ ዳር ነበርኩኝ። ችግሮች እንዳይፈጠሩ ስላሰብን ነው እስካሁን የቆየነው። አሁን ሰብረን አይደለም የገባነው የከተማው ህዝብ ከየአቅጣጫው ወጥቶ ' በሩ ይከፈት ' ብሎ ጠየቀ መልስ በማጣቱ ገፍቶ ነው የገባው በዚህም ወደ ፅ/ቤት ገብተናል " ብለዋል።

የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ራቅ ብለው ይከታተሉ ነበር እንጂ ወደ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ አልገቡም ሲሉ አክለዋል።

#VOATIGRIGNA

@tikvahethiopia
😁420🕊114102😭39🤔33😡16👏11🙏11😢9🥰3