TIKVAH-ETHIOPIA
#Update
" ሰባቱን ፍርድ ቤት ዋስትና እያስሞሉ ነው። ሌሎቹን ደግሞ ፈተዋቸዋል " - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ያለፈቃዳቸው ከደመወዛቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስ በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
በአጠቃላይ ታስረው የነበሩት ከ66 በላይ እንደነበሩ፣ 22 የሚሆኑት መምህራን እስከዛሬ ድረስ በእስር ላይ እንደቆዩ፣ ቀሪዎቹ ግን ሰሞኑን እንደፈቷቸው የዞኑ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልጽ ነበር።
ከእስራት ያልተፈቱት ቀሪ 22ቱ መምህራን ዛሬ እንዲፈቱ ውይይት እየተደረገ እንደነበርም ማኀበሩ ጠቁሞ ነበር።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ በበኩሉ፣ 22ቱ መምህራን እንዲፈቱ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልጾ፣ ዛሬ እንደሚፈቱ ለቲክቫህ ተናግሯል።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰርበ አሻግሬ ዛሬ ከሰዓት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ደመወዛቸው የተቆረጠው ተስማምተው ስለመሆኑ ስም ዝርዝር እንዳላቸው ፤ በእስር ላይ ያሉትም እንደሚፈቱ ገልጸዋል።
ጥያቄያቸው ወይ የእነርሱ ይስተካከል ወይ የእኛ ይመለስ የሚል ቢሆን እኔም ከጎናቸው ነኝ ብለዋል።
አቶ ሰርበ አሻግሬ ምን አሉ ?
“ ተስማምተው ከቆረጡ በኋላ እኔም ጋ የመጡት ‘እኛ ቆርጠን ሌሎቹ አልቆረጡም፤ ልክ አይደለም ተነጋገሩ’ ብለው ነበር። እኔም ስልጠና ላይ ስለነበርኩ ነው የቆየነው።
መምህራኑ ይፈታሉ። ማታ ለሁለት በድን ነግሬአለሁ። የመጀመሪያዎቹ ዋና በጥባጮቹ ሰባት ናቸው። ‘እነርሱ ለምን ታሰሩ?’ ብለው የገቡት 15 ናቸው። 15ቱ ከትላንትና ወዲያም ይውጡ ተብሎ ‘አንድ ላይ ነው የምንወጣው’ ብለው ነው።
የእናንት የሁለታችሁ ኬዝ የተለያዬ ስለሆነ ነው። የእናንተ ከፓሊስ ጋር በመጋጨት ነው ውጡ ተብለው እኮ 15ቱ መምህራን አንወጣም ነው እኮ ያሉት።
የታሰሩት 22 መምህራን ናቸው። ሰባቱ ተማሪዎቹን አባረው መምህራንንም የጠበጡ ናቸው። አሁን 66 ታሰሩ የሚለው ውሸት ነው። ሰባቱ መጀመሪያ ተያዙ፤ 15 በኋላ ገቡ። ትላንት ውጡ ተብለው እምቢ ብለው ነው። ዛሬ ይወጣሉ። ” ብለዋል።
መምህራኑ ተፈተዋል ?
የዞኑ መምህራን ማኀበር ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ምሽት 12 ሰዓት ገደማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ መምህራኑ ከእስር ተፈትተዋል።
የማኀበሩ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ ሰባቱን ፍርድ ቤት ዋስትና እያስሞሉ ነው። ሌሉሎቹን ደግሞ ፈትተዋቸዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ሁሉም ተፈትተዋል ማለት ይቻላል? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ "ኦረዲ አዎ ለሰባቱ ብቻ ተያዢ ፈልገው ነው፡፡ ተያዦቹም ኦረዲ እየጨረሱ ናቸው" ብለዋል።
ተደበደቡ የተባሉት ምህራን እስከዛሬ ህክምና አግኝተው ነበር ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ ሳያገኙ እንደቆዩ የሚታከሙት ገና ካሁን ወዲያ እንደሆነ ምላሽ ሰጥተዋል።
የተፈቱት በምን ተስማምታችሁ ነው ? ለተሚለው የቲክቫህ ጥያቄ የሰጡት ማብራሪያ ደግሞ፣ መምህራኑና ትምህርት መምሪያው እንዲወያዩ፣ መምህራኑ ይመለስ ካሉ ገንዘቡ እንዲመለስ መወሰኑን ነው የገለጹት።
#Update - መምህራኑ ከእስር ተፈተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭371❤143😡50👏29🙏25🤔16🕊16🥰15😱14😢14