TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የመምህራንድምጽ 🔴 “ ‘ለምን ደመወዛችን ተቆረጠ’ ብለው የጠየቁ 66 መምህን  ታስረዋል” - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር 🔵 “የታሰሩት በመምህራን ላይ ድንጋይ በመወርወር ሌሎቹን በመበጥበጣቸው ነው” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ 🟢 “ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። ሥራ ላይ ነኝ ስንት ሰዓት እንደምጨርስ አላውቅም”  - የዞኑ ሰላምና ጽጥታ ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ…
🔈 #የመምህራንድምጽ

#Update

የተደበደቡ ስድስት መምህራን ህክምና ተከልክለዋል። ከታሰሩት አንድም የተፈታ የለም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ ከ60 በላይ መምህራን ከደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑ መምህራን ማኀበር ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ፣ መምህራኑ ከእስር እንዳልተፈቱ፣ እየታሰሩ በነበረበት ወቅት ድብደባ የተፈጸመባቸው መምህራን እንዳይታከሙ መከልከላቸውን ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

የማኀበሩ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ለበሰጡት ቃል፣ “ በሚያስሩበት ወቅት የተደበደቡ ስድስት መምህራን ህክምና ተከልክለዋል። ከታሰሩት ውስጥ አንድም የተፈታ የለም ” ብለዋል።

ተጎጂዎቹን እንዲያዩ የማኀበሩን ሰዎች ወደ እስራት ቦታው ልኮ እንደነበር የገለጹት አቶ ተስፋዬ፣ “ አሁን ባለው ሂደት ብዙዎቹ እንደተገጎዱ ናቸው። እንዲያውም የአንዱ በጆሮው ሁሉ መግል እየወጣ ነው ህክምና ተከልክለዋል ” ብለው፣ ለማሳከም ቢጠይቁም እንደከላከሏቸው ተናግረዋል።

መምህራኑ ከታሰሩ ስንት ቀናት አስቆጠሩ ? የተቆረጠባቸው ምን ያህል ገንዘብ ነው ? ለሚለው ቲክቫህ ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ደግሞ፣ “ ረቡዕ ነው እስራቱ የተጀመረው ፤ ዛሬ አራተኛ ቀናቸው ነው። 25 በመቶ ነው የተቆረጠባቸው ” የሚል ነው።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ፣ መምህራኑ ደመወዛቸው የተቆረጠው በፈቃዳቸው እንደሆነ፣ የታሰሩትም ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው ሳይሆን፣ “ ድንጋይ ወርውረው ሌሎችን በመበጥበጣቸው ” መሆኑን ነው የገለጸው፣ እውነትም እንደዛ ነው የሆነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ?

“ ይሄ ትልቅ ውሸት ነው። ቢነጋገሩ፣ ተስማምተው ቢሆን ኖሮ መምህራኑ ቅሬታ አያቀርቡም ነበር።

መምህራኑ ለትምህርት መምሪያው በፅሑፍ ያቀረቡት ‘አልተስማማንበትም፤ ባልተስማማንበት ጉዳይ የተቆረጠብን ገንዘብ ይመለስልን’ የሚል ነው።

‘ያልተስማማንበት ስለሆነ ገንዘቡ ይመለስ’ ብሎ እያንዳንዱ መምህር ትምህርት መምሪያውን ጠይቋል። መምሪያው ይሄን ሁሉ ክዶ ነው ለመሸፈን የሚሞክረው። ባወጣው መግለጫም እርምት ቢደረግ መልካም ነው።

ትምህርት መምሪያው መምህራኑ ‘ድንጋይ ወርውረዋል’ ማለቱ ውሸት ነው። አንድም የወረወረ የለም። አንድ መምህር ለስህተት ድንጋይ የሚባል ነገር አላነሳም። ይህን ወርዶ ማረጋገጥ ይቻላል ”
ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ፕሬዜዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ በበኩላቸው፣ “ ‘አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ’ በሚል ነው መምህራኑን ሳያወያዩ ‘በዞን ደረጃ ተወስኗል’ በሚል ከደመወዛቸው እየቆረጡ ያሉት ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ ደመወዝ ያለስምምነት መቆረጥ እንደሌለበት አቅጣጫ ቢቀመጥም ይሄን የሚያደርጉ አካላት ምንም ሲያደርጉ አይታዩም ” ሲሉም ተችተዋል።

“ ከዚህ በፊት ሌላ ዞንና ወረዳ ላይ እንደዚህ አይነት ነገር ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች ተመልሰው የተሻለ ሹመት እንዲያገኙ ነው የሚደረገው እንጂ ‘ይሄን አጥፍተሃል’ ተብሎ የማጠየቅ አካል የለም ” ነው ያሉት።

ስለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ታምራት፣ ለጊዜው የማይመች ቦታ እንደሆኑ ገልጸው፣ ቀጠሮ ሰጥተው የነበረ ሲሆን፣ በቀጠሩት ሰዓት በተደጋጋሚ ቢደወልም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ትላንት በሰጠን ማብራሪያ፣ የመምህራኑ ደመወዝ የተቆረጠው በስምምነታቸው መሠረት እንደሆነ፣ የታሰሩትም፣ ድንጋይ ስለወረወሩ እንደሆነ፣ ቅሬታው እንዲፈታ እየሰራ ስለመሆኑ ገልጾ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭772😡199138🕊35👏32😢31🙏28🤔25😱24🥰18
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የመምህራንድምጽ #Update “ የተደበደቡ ስድስት መምህራን ህክምና ተከልክለዋል። ከታሰሩት አንድም የተፈታ የለም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ ከ60 በላይ መምህራን ከደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑ መምህራን ማኀበር ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ፣ መምህራኑ…
🔈#የመምህራንድምጽ

#Update

" ሰባቱን ፍርድ ቤት ዋስትና እያስሞሉ ነው። ሌሎቹን ደግሞ ፈተዋቸዋል " - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ያለፈቃዳቸው ከደመወዛቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስ በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

በአጠቃላይ ታስረው የነበሩት ከ66 በላይ እንደነበሩ፣ 22 የሚሆኑት መምህራን እስከዛሬ ድረስ በእስር ላይ እንደቆዩ፣ ቀሪዎቹ ግን ሰሞኑን እንደፈቷቸው የዞኑ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልጽ ነበር።

ከእስራት ያልተፈቱት ቀሪ 22ቱ መምህራን ዛሬ እንዲፈቱ ውይይት እየተደረገ እንደነበርም ማኀበሩ ጠቁሞ ነበር።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ በበኩሉ፣ 22ቱ መምህራን እንዲፈቱ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልጾ፣ ዛሬ እንደሚፈቱ ለቲክቫህ ተናግሯል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰርበ አሻግሬ ዛሬ ከሰዓት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ደመወዛቸው የተቆረጠው ተስማምተው ስለመሆኑ ስም ዝርዝር እንዳላቸው ፤ በእስር ላይ ያሉትም እንደሚፈቱ  ገልጸዋል።

ጥያቄያቸው ወይ የእነርሱ ይስተካከል ወይ የእኛ ይመለስ የሚል ቢሆን እኔም ከጎናቸው ነኝ ብለዋል።

አቶ ሰርበ አሻግሬ ምን አሉ ?

“ ተስማምተው ከቆረጡ በኋላ እኔም ጋ የመጡት ‘እኛ ቆርጠን ሌሎቹ አልቆረጡም፤ ልክ አይደለም ተነጋገሩ’ ብለው ነበር። እኔም ስልጠና ላይ ስለነበርኩ ነው የቆየነው።
 
መምህራኑ ይፈታሉ። ማታ ለሁለት በድን ነግሬአለሁ። የመጀመሪያዎቹ ዋና በጥባጮቹ ሰባት ናቸው። ‘እነርሱ ለምን ታሰሩ?’ ብለው የገቡት 15 ናቸው። 15ቱ ከትላንትና ወዲያም ይውጡ ተብሎ ‘አንድ ላይ ነው የምንወጣው’ ብለው ነው።

የእናንት የሁለታችሁ ኬዝ የተለያዬ ስለሆነ ነው። የእናንተ ከፓሊስ ጋር በመጋጨት ነው ውጡ ተብለው እኮ 15ቱ መምህራን አንወጣም ነው እኮ ያሉት።

የታሰሩት 22 መምህራን ናቸው። ሰባቱ ተማሪዎቹን አባረው መምህራንንም የጠበጡ ናቸው። አሁን 66 ታሰሩ የሚለው ውሸት ነው። ሰባቱ መጀመሪያ ተያዙ፤ 15  በኋላ ገቡ። ትላንት ውጡ ተብለው እምቢ ብለው ነው። ዛሬ ይወጣሉ። ”
ብለዋል።

መምህራኑ ተፈተዋል ?

የዞኑ መምህራን ማኀበር ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ምሽት 12 ሰዓት ገደማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ መምህራኑ ከእስር ተፈትተዋል።

የማኀበሩ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ ሰባቱን ፍርድ ቤት ዋስትና እያስሞሉ ነው። ሌሉሎቹን ደግሞ ፈትተዋቸዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ሁሉም ተፈትተዋል ማለት ይቻላል? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ "ኦረዲ አዎ ለሰባቱ ብቻ ተያዢ ፈልገው ነው፡፡ ተያዦቹም ኦረዲ እየጨረሱ ናቸው" ብለዋል።

ተደበደቡ የተባሉት ምህራን እስከዛሬ ህክምና አግኝተው ነበር ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ ሳያገኙ እንደቆዩ የሚታከሙት ገና ካሁን ወዲያ እንደሆነ ምላሽ ሰጥተዋል።

የተፈቱት በምን ተስማምታችሁ ነው ? ለተሚለው የቲክቫህ ጥያቄ የሰጡት ማብራሪያ ደግሞ፣ መምህራኑና ትምህርት መምሪያው እንዲወያዩ፣ መምህራኑ ይመለስ ካሉ ገንዘቡ እንዲመለስ መወሰኑን ነው የገለጹት።

#Update - መምህራኑ ከእስር ተፈተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭371143😡50👏29🙏25🤔16🕊16🥰15😱14😢14