TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia

🕊 " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም ! " - ነዋሪዎች

🟢 " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " - አቶ ሽመልስ አብዲሳ

" የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው፤... ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ ይሰጣል " - ጃል ሰኚ

" ስምምነቱን ቀድሞውኑ ከተባረሩ ግለሰቦች ጋር ነው የተፈጸመው " - ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጋር ለድርድር ቁጭ ብሎ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት


ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የቀድሞው የማዕከላዊ ዞን አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የሰላም ስምምነት ተፈርሟል።

የስምምነት ሰነዱ ምን እንደያዘ ፣ ምን ምን ጉዳዮች ላይ መግባባት ተደርሶ ስምምነት እንደተፈረመ ፣ በጃል ሰኚ ስር ምን ያህል ታጣቂ  ወደ ሰላም እንደሚመለስ (በቁጥር) ፣ የነዚህ ታጣቂዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ በይፋና በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።

ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ይህ የሰላም ስምምነት ለዜጎች እረፍትን የሚሰጥ ሰላም የሚያሰርጽ መሆኑን ገልጿል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤ " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " ብለዋል።

" የኦሮሞ ህዝብ በባህልና በወጉ መሰረት በሮቹን ጠምዶና ፈረሶችን ጭኖ በመውጣት ሰላም ይውረድ ባለው መሰረት ጥሪውን ተቀብላችሁ በመምጣታችሁ በራሴና በክልሉ መንግስት ስም አመሠግናለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ሂደት ትልቁን ስራ ለሰራው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ምስጋና አቅርበዋል።

ጃል ሰኚ " የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የኦሮሞ ህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዓለም ላይ የሰው ልጅ የፖለቲካ ልዩነት አለው ፤ እኛም ያለንን የፖለቲካ ልዩነት በጠመንጃ ከመፍታት ይልቅ በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ወስነን ነው ስምምነቱን የመረጥነው " ብለዋል።

ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጋር ውጭ ሀገር ለሰላም ድርድር ቁጭ ብሎ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ባወጣው መግለጫ " ስምምነቱ ህዝቡን ለማምታታ የተፈጸመ ነው " ሲል ተችቷል።

ስምምነቱን ቀድሞውኑ ከተባረሩ ግለሰቦች ጋር ነው የተፈጸመው ብሏል።

ያም ሆነ ይህ ስምምነቱን ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው ወደ ማዕከል እየገቡ እንደሆነ ተነግሯል።

ለመሆኑ ነዋሪዎች ምን ይላሉ ?

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች በርካታ ታጣቂዎች ወደተዘጋጀላቸው ማዕከላት እየገቡ እንደሆነ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

በርካታ የታጣቂ አባላት የሰላም መንገድ መርጠው በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን እና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች እየተመለሱ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ምዕራብ ሸዋ ጮቢ፣ ኢልፈታ፣ ዳኖ እና ጅባት ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ እና ዳው በሚባሉ ወረዳዎች የቡድኑ አባላት ቅብላ እየተደተገላቸው ነው።

ጃለታ አበበ ፤ " ትላንት እና ዛሬ ብቻ 7 መኪና ነው የተሃድሶ ትምህርት ለመውሰድ ወደ ዞን ከተማ የገቡት። የሰላም ጥሪውን ከተቀበሉት ምንም የቀሩ አይመስለኝም ፤ ክላሽ መትረየስ እና ስናይፐር ይዘው ነው ያሉት " ብለዋል።

" ኢልፈታ፣ ግንደበረት ፣ ወዴሳና አምቦ አጠቃላይ ምእራብ ሸዋ ላይ ብዙ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባል የሰላም ጥሪ ተቀብሎ እየገባ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በዚህ ልክ የሰላም ጥሪ ተቀብሎ የተመለሰ የታጣቂ ቡድን አባላትን አይተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ጀልዱ ወረዳ በተመሳሳይ ቅበላ እየተደረገላቸው እንደነበር ተሰምቷል።

አቶ ግርማ ሌሎ የጀልዱ ወረዳ ኪልቤ ቀበሌ አስታዳዳሪ ፥  " በትክክልም በሁሉም አቅጣጫ እየተመለሱ ናቸው። ዛሬ እና ትላንት ጀልዱ ወረዳ ጉጁ ከተማ ሲደረሱ ሰው ሁሉ ወጥቶ ሲመለከታቸው ነበር " ብለዋል።

" መጀመሪያ ሲመጡ በየቀበሌያቸው በየቦታው ይሰበሰባሉ ከዛ ወደ መንግሥት ኃይሎች ስልክ ደውለው ነው የቅበላ ሰርዓት የሚደረገው። በጀልዱ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ነው እየተበልን ያለነው " ሲሉ አክለዋል።

ዊቱሺኩቴ፣ ኢልኬ ፣ጎሮ ቀበሌዎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የመጡባቸው እንደሆኑ ጠቁመዋል።

አሁን ላይ በጃል ሰኚ የሚመሩት የሰላም አማራጭ ተከትለው እየተመለሱ ቢሆንም የሌሎች የቀሩትን እንደማያውቁ አቶ ግርማ ገልጸዋል።

" የህዝቡን ፍላጎት ተመልክተው ይመለሳሉ ብለን እናምናለን " ብለዋል።

ባለፈው ጥቅምት ወር በኪልቤ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በመንግሥት የፀጥታ አካላት መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ የብዙ ሰው ህይወት አልፏል።

" አሁን ሰላም መውረዱ መሰል የሰው ህይወት ቀጥፈትን ይታደጋል " ሲሉ አቶ ግርማ ተናግረዋል።

እርስ በእርስ መተኳኮሱ ከቆመ በአካባቢው የተደናቀፈው ልማት ይቀጥላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ፤ የህዝቡ ፍላጎትን ስለሚያስጠብቅ ሰላም መውረዱ አስደሳች እንደሚሆን አክለዋል።

የጮቢ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ጃለታ በቀለ ፤ " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም። አሁን ህዝቡ ለ5 ዓመታት በቀጠለው ጦርነት ተጎድቷል መንግሥት እና ግብረሰናይ ድርጅቶች የህዝቡ ህይወት የሚንሰራራበትን መላ ይዘው ቢመጡ መልካም ነው " ብለዋል።

[ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዋሪዎች ቃል ምንጭ ቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ሬድዮ እንደሆነ ይገልጻል ]

ኦሮሚያ ባለፉት አመታት ?

ከ6 ዓመታት በፊት " ለውጥ መጥቷል " ከተባለና መንግሥት ኤርትራ አስመራ ላይ ከኦነግ ጋር ስምምነት ደርሷል ከተባለ በኃላ (ምንም እንኳን የስምምነት ሰነዱ ለህዝብ ይፋ ባይደረግም) ወደ ክልሉ በርካታ ታጣቂዎች ገብተዋል።

ከነዚህም ውስጥ ትጥቅ ሳይፈቱ የገቡ በርካቶች ነበሩ።

ወደ ሃገር ከገቡት ውስጥ " ከኦነግ ፓርቲ ጋር ተለያይተናል " ያሉ አባላት " መንግሥትን በትጥቅ ነው የምንታገለው " ብለው ወደ ጫካ ገብተዋል።

ይህን ተከትሎ በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች መካከል በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ በርካቶች አልቀዋል።

እገታ፣ ዘረፋ ተስፋፍቷል።

ተማሪዎች ትምህርት መማር አልቻሉም ፡ ገበሬዎች ማረስ አልቻሉም። ንፁሃን ዛሬም ድረስ ፍዳቸውን እያዩ ነው።

ሰላም ወጥቶ መግባትም የማይታሰብ የሆነባቸው በርካታ ቦታዎች ተፈጥረዋል።

በተለያዩ ቦታዎች ትጥቅ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ትንንሽ ቡድኖችንም እንዲበዙ ሆኗል።

በክልሉ ያለውን የትጥቅ እንቅስቃሴ ሆነ ሰላም የራቃቸውን ቦታዎች ወደ ሰላም ለመመለስ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና መንግሥት መካከል የጠረጴዛ ድርድር ሁለት ጊዜ ከሀገር ውጭ ቢደረግም ጠብ ያለ ተስፋ ያለው ውጤት ሳይመጣ ቀርቶ የትጥቅ እንቅስቃሴ በክልሉ ቀጥሏል።

አሁን ተደርጓል የተባለው የሰላም ስምምነት በጃል ሰኚ ከሚመራው ቡድን ጋር ቢሆንም ሌሎችም የሚመሯቸው ታጣቂዎች በክልሉ ይንቀሳቀሳሉ።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ኦሮሚያ

@tikvahethiopia
🕊853255😡255🤔42😭37😢20👏15🙏15🥰13😱13
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
ሶሪያ በቀጣይ ወዴት ?

የ24 ዓመታት የበሽር አላሳድ አገዛዝ አክትሟል።

ቤተሰባቸውን ይዘውም ሩስያ ገብተዋል። ጥገኝነትም ተሰጥቷቸዋል።

አሁን ላይ የታጠቁ ተቃዋሚዎች መንበሩን ይዘዋል።

አላሳድን አንባገነን እንደሆኑ የሚገልጹ በርካቶች ክስተቱን ለሶሪያ ዘላቂ ሰላም እድል ያመጣል ይላሉ።

ከዚህ በተቃራኒ በሀገሪቱ ብዙ ታጣቂዎች ነፍጥ ስለያዙ  ለስልጣን ሲባል ወደ 2ኛው ዙር የእርስ በእርስ እልቂት ሊገባ ይችላል የሚሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።

ሶሪያ ከፊቷ ተስፋ እና ስጋት ተደቅኗል።

ሶሪያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት እነማን ናቸው ?

እ.ኤ.አ 2011 ነው የሶሪያ እርስ በርስ እልቂት የጀመረው።

የተሳታፊው ብዛት በርካታ ነው። እነዚህ የየራሳቸው ተሳትፎ፣ አመለካከት፣ ዓላማ ያነገቡ ናቸው።

ጉዳዩ ወስብስብ ያለ ነው።

👉 የአሳድ መንግሥት ኃይሎች

የሶሪያ አረብ ጦር (SAA) እና የብሔራዊ መከላከያ ኃይል (NDF) እኚህ የአላሳድ የጀርባ አጥንት ናቸው። SAA ኦፊሴላዊ የሆነው የሶሪያ መከላከያ ነው። NDF በመንግሥት የሚደገፍ ሚሊሻ ነው። SAA በኢራን እና ሩስያ ይደገፋል። በቀጣዩ መንግሥት ምስረታ ዕጣ ፋንታቸው ምን ይሆን ? የሚለው ምናልባትም በነ ሩስያ እና ኢራን ተፅእኖ ስር የወደቀ ሊሆን ይችላል።

👉 ነጻ የሶሪያ ጦር (FSA)

ቡድኑ መጀመሪያ የተቋቋመው ከሶሪያ ጦር ከድተው በወጡ አካላት ነው። ከዛም ወደ ተለያዩ አንጃዎች እና ጥምረት ተለውጣል። ብዙ ጊዜ ከምዕራባውያን እና ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ድጋፍ ያገኛል። በብዙ የሶሪያ ክፍሎች ይንቀሳቀሳል ነገር ግን በተለይ በሰሜን የአሳድን ጦር ሲዋጋ ነበር። በኃላም ISISን ሲዋጋ ነበር።

👉 ሀያት ታህሪር አል-ሻም (HTS)

ይህ በመጀመሪያ የሶሪያ የአልቃይዳ ክንፍ ነበር ፤ አልኑስራ በሚል ነበር ይንቀሳቀስ የነበረው። 2017 ላይ ግን በኢድሊብ እና ከፊል አሌፖ ፈርጠም ብሎ ወጥቷል። አላማው እስላማዊ መንግሥት መመስረት እንደሆነ ይነገርለታል። በቅርቡ አሳድን በመገርሰስ ጥቃት ላይ ቁልፍ ሚና ነበረው። በአዲሱ መንግሥት መመስረት ውስጥ የራሱን አላማ ለማስረጽ ግፊት ሊያደርግ ይችላል በዚህም ሴኩላር ከሚባሉት እና መሃከል ላይ ካሉት ጋር ሊጋጭ ይችላል። በኢድሊብ ከነበራቸው የመንግሥት አስተዳደር ጥብቅ የሸሪያ ህግ ለመተግበር ሊሰራ ይችላል።

👉 የሶሪያ ብሔራዊ ጦር (SNA)

እኚህ በቱርክ የሚደገፉ ናቸው። በዋነኝነት በሰሜናዊ ሶሪያ ነው የሚንቀሳቀሱት። የኩርዲሽ ኃይሎችን በመዋጋት የቱርክን ተፅእኖ ለማስረጽ ይንቀሳቀሳሉ ይባላሉ። በአዲሱ መንግሥት የቱርክን ፍላጎት የያዘ ሃሳብ ይዘው ሊቀርቡ ይችላሉ።

👉 የሶሪያ ዴሞክራቲክ ኃይል (SDF)

እኚህ በኩርዲሽ ዋይፒጂ ነው የሚመሩት። በአሜሪካ ድጋፍ ISISን በማሸነፉ ረገድ ትልቁን ሚና ተጫውተዋል። እኚህ ቡድኖች ሰሜናዊ ምስራቅ ሶሪያን ተቆጣጥረው የያዙ ናቸው። ራዕያቸው የፌዴራል፣ ያልተማከለ ሶሪያ እንድትኖር ነው። በማንኛውም አዲስ መንግስት ውስጥ፣ የኩርድ የራስ ገዝ አስተዳደር ወይም ፌደራሊዝም እንዲሰፍን ግፊት ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ ደግሞ እንደ SNA ካሉ ሌሎች ቡድኖች ጋር ሊያጋጫቸው ይችላል።

እንግዴ እኚህ ሁሉ አላማቸው የሚለያይ ነፍጥ ያነገቡ ቡድኖች ናቸው ሶሪያ ውስጥ ያሉት።

ከአሳድ አገዛዝ ወደ አዲስ መንግሥት ለሚደረገው ሽግግር ምናልባትም እጅግ ወሳኝና ጥልቅ ድርድር አልያም የእርስ በእርስ ግጭት በቡድኖቹ መካከል ሊፈጠር ይችላል።

🚨 SAA እና የአሳድ ደጋፊ ሚሊሻዎች ለውጡ ለነሱ ወይም አጋሮቻቸው ምቹ ሁኔታ ካልፈጠረ ሊቃወሙ ይችላሉ።
🚨 HTS ይበልጥ ሃይማኖታዊ የመንግሥት አስታዳደር ለመመስረት ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ።
🚨 FSA እና ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ቡድኖች ዴሞክራሲያዊ ሂደትን ይደግፋሉ ነገር ግን ጉልህ ተፅእኖ እንዲኖራቸው በአንድ የፖለቲካ ጥላ ስር መጠቃለል አለባቸው።
🚨 SDF ፌዴራሊዝም (ክልላዊ ራስን በራስ የማስተዳደር) እንዲተገበር ግፊት ሊያደርግ ይችላል። ይህን ሞዴል ሌሎች ከተቃወሙት ግጭት መቀጠሉ አይቀሬ ነው።
🚨 ቱርክ በSNA በኩል በምታደርገው ተፅእኖ ጠንካራ ፣ የተማከለ የኩርድ አካል እንዳይፈጠር ለመከላከል በመሆኑ ይህ ወደ ቀጣይ ውጥረት ሊያመራ ይችላል።


በአዲሱ የሶሪያ መንግሥት መስረታ የኃይል መመጣጠን ፣ በቡድኖቹ መካከል ያለው የአስተሳሰብ ልዩነት እና የውጭ ኃይሎች ተፅእኖ ትልቅ ፈታና ይሆናል። የእያንዳንዱ ቡድን ወታደራዊ ጥንካሬ በውጭ ኃይሎች ድጋፍ እና በውስጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የተቀረጸ በመሆኑ ሰላማዊ  ሽግግር ይኖር ይሆን ? የሚለው አሳሳቢ ነው።

አንዳንዶች ለውጡን በአግባቡ መያዝ ካልተቻለ ሀገሪቱ የመበታተን አደጋ እና ከበፊቱም የባሰ ሰቆቃ ውስጥ ልትገባ የምትችልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ እየገለጹ ነው።

እኚህ ሁሉ ነፍጥ ያነገቡ ቡድኖች ወደ አንድነት መጥተው ጠንካራ ሶሪያን ይመሰርቱ ይሆን ? ወይስ ሁለተኛው ዙር የሶሪያ እርስ በርስ እልቂት ይቀጥላል ? ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል !

🛑 ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ፅሁፍ ለማዘጋጀት በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚተነትኑትን ቻክ ፈረን ጨምሮ የተለያዩ ድረገጾችን ተጠቅሟል።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
🙏437189🕊118👏32😢24🤔20😱18🥰11😡11😭9
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመሬት መንቀጥቀጡ የቦታ ለውጥ አድርጓል ?

" በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም " - ፕ/ር አታላይ አየለ

በትላንትናው ዕለት በቀን፣ በምሽትና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸው ዓለም አቀፍ ጁኦሎጂካል ተቋማት ዘግበዋል።

ትላንት ምሽት 2:10 የተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተሰማው በሬክተር ስኬል 5.0 ሆኖ ከተመዘገበው መንቀጥቀጥ በተጨማሪ ለሊት 7:20 ላይ 5.1 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በተጠቀሰው መጠን መከሰቱን እና ዛሬ ጠዋት 2:11 ላይም ሌላ መንቀጥቀጥ በመታየቱ የመተንተን ስራ እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም፤ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ትላንት ለሊት 7:20 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከደብረ ሲና 52 ኪሜ ርቀት ላይ ምሽት ላይ የተከሰተው ደግሞ ከአዋሽ 14 ኪሜ ርቀት ላይ የተከሰተ ነው መባሉ ከዚህ ቀደም ይከሰት ከነበረበት የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የቦታ ለውጥ አለ ማለት አለመሆኑን አስረድተዋል።

ተመራማሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

" ትላንትና ከሰዓት ጀምሮ በጣም የተደጋጋመ ከፍተኛ መጠን ያለው ከ4.6 ጀምሮ እስከ 5.0 የተመዘገበ መንቀጥቀጥ ተከስቷል ፤ ነገር ግን ደብረ ሲና ሲል ከፈንታሌ በወፍ በረር ሲለካ ነው ከተለያየ አቅጣጫ በማየት ነው እንጂ መነሻው ስለተቀየረ አይደለም።

አንድ አካባቢ ላይ መሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት በአቅራቢያው ያለው ከተማ የትኛው ነው ? የሚለው ይታያል ከዛ የተለያዩ ከተሞችን እንደ ሪፈረንስ ይጠቅስና ከዛ ከተማ ምን ያህል ነው የሚርቀው የሚለውን ሪፈር ያደርጋል፤ እንደዛ ሲሆን ሌላ ሰው መንቀጥቀጡ ለዛ ከተማ ቀርቧል ማለት ነው የሚል ስጋት ሊያድርበት ይችላል ነገር ግን እስካሁን የተቀየረ ነገር የለም፤ ፈንታሌ ዙሪያ ነው እንቅስቃሴው እየተታየ ያለው።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ እና የጀርመኑ የጂኦ ሳይንስ ተቋማት የሚጠቀሙት ዳታ አውቶማቲክ ነው ሲስተሙ ቶሎ አናላይዝ አድርጎ የተከሰተበትን መጠን እና አካባቢ ከርቀት ጋር ይናገራል ነገር ግን ይህ አይነቱን አዘጋገብ የሚከተሉት ለማህበረሰቡ በምን ያህል ርቀት ላይ ነው የተከሰተው የሚለውን ለማስረዳት ነው።

ለምሳሌ፦  አንድ ብቻ አይደለም የተለያዩ ቦታዎች ይጠቅሳሉ  ከመተሃራ፣ከደብረሲና ፣ከደብረ ብርሃን እና ከአዲስ አበባስ ምን ያህል ርቀት ላይ ይገኛል ሊል ይችላል በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም።

አዲስ ነገር አይደለም ስንመዘግብ የኖርነው ነገር ነው ነገር ግን መሃንዲስም፣ ኢንቨስተርም ሆነ የሚመለከተው አካል ጆሮ ሰጥቶ ጥንቃቄ አድርጎ አያውቅም አሁን የሚከሰተውንም መአት እንደተከሰተ አድርጎ የሚያወራ አለ እንደዛ አይደለም በተለያየ ጊዜ ይመዘገባል።

በ1997 በአፋር ታይቶ የማይታወቅ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ነበር ብዙ አለም አቀፍ ሳይንቲስቶች ሁሉ መጥተው አብረን የሰራናቸው ስራዎች አሉ፣ ፈንታሌም በፈረንጂዎቹ 1981 እንደ አሁኑ 3 እና 4 ወር የቆየ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ነበር።

የመረጃ ውንዥብር እየተፈጠረ ነው ሳይንቲስት የምንለው ማነው ? ታማኝነቱስ ምን ያህል ነው ?የሚለው አስቸጋሪ ሆኗል ያልሆነውን ሆኗል እያሉ የሚያወናብደውም ብዝቷል ተማረ የምንለውም መሬት ላይ ያለውም ህብረተሰብ።

መሬት በራሷ ጉዞ እየሄደች የምታስተነፍሰው ሃይል ነው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ቦታውም፣ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሆነ ይታወቃል በተለይ አዲስ አበባ ያለ ሰው ምንም ሊደነግጥ አይገባም።

ከትላንት እኩለ ቀን ጀምሮ ጎላ ጎላ ያሉት መንቀጥቀጦች የመደጋገም ፍጥነታቸው ጨምሯል ቀጣይነትም ያለው ሊሆን ይችላል እየተከታተልን እየመዘገብን እንገኛለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#AAU
#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
😭372217🙏70🕊54🤔32😱24👏19😢17😡17🥰7
የትራምፕ የታሪፍ ጦርነት ወዴት ያመራ ይሁን ?

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገራት ላይ የሚጣል አዲስ ታሪፍ ይፋ ካደረጉ በኋላ በተለይም ከቻይና ጋር ተፋጠዋል።

ትራምፕ ከዚህ በፊት ሌሎች ሀገራት የአሜሪካ ምርቶች ላይ ከሚገባው በላይ ታሪፍ ጥለዋል ብለው እንደሚያምኑ እና ይህንን የሚስተካከል ታሪፍ እንደሚጥሉ ከተናገሩ በኋላ ነው አዲሱን ታሪፍ ያስተዋወቁት።

በመጀመሪያው ዙር ፕረዚዳንት ትራምፕ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ 104 % ቀረጥ ጥለው የነበረ ሲሆን ቻይና በምላሿ (Reciprocal Tariff በተለምዶ አንድ ሃገር የሆነ ሃገር ላይ ታሪፍ ስትጥል በምላሹ ሌላኛዋ ሃገር የምትጥለው ታሪፍ) 84% ከአሜሪካ በሚገቡ እቃዎች ላይ ቀረጥ መጣሏን ገልጻለች።

አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችው ቀረጥ ዝርዝር ምን ይመስላል ?

➡️ 10% አዲስ ቤዝ ታሪፍ (ይህ በኢትዮጵያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የተጣለ ትንሹ ቀረጥ ነው)

➡️ 20% ነባር ታሪፍ

➡️ 34% ተመጣጣኝ / reciprocal ታሪፍ (በፊት ቻይና በአሜሪካ ላይ ጥላው የነበረችውን ታሪፍ መጠን ያክል)

➡️ 50% ለቻይና ያለፉት ድርጊቶች ቅጣት የተጣለ ታሪፍ ያካተተ ነው።

አሜሪካ ይህንን የታሪፍ ዝርዝር ይፋ ካደረገች በኋላ በርካታ ሀገራት ግብረ መልስ ቢሰጡም ዛሬ ከአሜሪካ በኩል የተሰማው መረጃ ተደራራቢ ታሪፍ የተጣለባቸው ሀገራት (ከ10 በመቶ በላይ) ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለመነጋገር መጠየቃቸውን ይገልጻል።

በዚህም ምክንያት የአሜሪካ አስተዳደር ለ75 ሀገራት ከፍተኛ ሽኩቻ ውስጥ ገብታ የነበረችው ካናዳን ጨምሮ ሜክሲኮ፣ ጃፖን ፣ደቡብ ኮሪያ እና ለአውሮፖ አባል ሀገራት የ90 ቀን የታሪፍ እቀባ (አዲሱ ታሪፍ እንዳይፈጸም የተቀመጠ #የእፎይታ_ጊዜ) ሰጥቷል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ እነዚህ 75 ሀገራት ከአሜሪካ መንግስት ጋር ድርድር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተቃራኒው ግን የቻይና መንግስት ለአሜሪካ አዲስ ታሪፍ ተመጣጣኝ ያለውን የ84 በመቶ ታሪፍ መጣሉን ባስታወቀ በሰዓታት ውስጥ አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችውን የታሪፍ መጠን ወደ 125 ከፍ አድርገዋለች።

ቻይና ከዚህ በተጨማሪ 18 የአሜሪካ ተቋማትን በተለይም ከወታደራዊ ምርት ጋር የተያያዙ ተቋማትን ዝርዝር በማውጣት እገዳ ጥላለች።

እንደ አማራጭም የቻይና የመገበያያ ገንዘብ የሆነው ይዋን (yuan) የመግዛት አቅምን ከዶላር አንጻር በማዳከም ምርቶቿ ይበልጥ በገቢያው ተወዳዳሪ እንዲሆኑም እየሰራች ነው።

ለምሳሌ ፦ አሜሪካ በቻይና ላይ የምትጥለው ታሪፍ የቻይናን ምርቶች የሚያስወድዱት ከሆነ የይዋን መዳከም ምርቶቹን ርካሽ ያደርጋቸዋል።

የዓለም ንግድ ድርጅት ይህ በዚህ ከቀጠለ የአሜሪካ-ቻይናን ንግድ እስከ 80% ሊቀንስ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ዓለምአቀፍ
@tikvahethiopia
700🤔191😭81🕊80🙏48👏39💔29🥰28😢20😡13😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
" ' ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው ' የሚለው አመራሩ የሚጠቀምበት ማጭበርበሪያ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ " ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው " የሚለው አመራሩ የሚጠቀምበት ማጭበርበሪያ እንደሆነ የቀድሞ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። ይህ የተናገሩት ከ ' ፋና ቴሌቪዥን ' ጋር በነበራቸው ዘልግ…
" እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ እስካሁን የታገስኩት ይበቃኛል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

በትግራይ ያለው ህገወጥ የወርቅ ንግድ  ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ የጀመረ ሳይሆን በጦርነቱ ጊዜም ሳይቀር ሲሰራ የነበረ እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አደረጉ።

አቶ ጌታቸው፤ "ብዙ ሰው የወርቅ ንግድ የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈራረምን በኃላ የጀመር ይመስለዋል" ያሉ ሲሆን ግን ጦርነቱም እየተካሄደ ንግዱ ነበር ብለዋል።

"እኔ የማምንበትን ትግል ነው ያካሄድኩት ብዬ አምናለሁ በዛ በማምንበት ትግል ውስጥ የትግራይን ህዝብ አጀንዳ ይዘው የታገሉ ብዙ የጦር መኮንኖች አሉ ለሰሩት ስራ ያለኝ ክብር በፍጹም አይቀንስም ግን ደግሞ ገና ገና ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይበላ በነበረበት ወቅት ሳይቀር ምሽግ ለመቆፈር ብለን የወሰድነው ኤክስካቫተር ወርቅ ለመልቀም ይጠቀሙበት የነበሩ አዛዦችም ነበሩ" ሲሉ አጋልጠዋል።

"ሲዋሹ በጣም ነው የሚገርመኝ" ያሉት አቶ ጌታቸው "እኔ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል እስካሁን የታገስኩትም ይበቃኛል" ብለዋል።

አቶ ጌታቸው "የኤርትራን ሰራዊት እናፍርሰው" በሚል አላማ ዘመቻ የጀመረና ዘመቻውን የሚመራው አመራር ሰዎችን እያፈነ ገንዘብ ሲበስብ እንደነበር ተናግረዋል።

"ሰው ሲሸጡ የሚኖሩ ሰዎች አሉ፤ ኤርትራዊ መሸጥ ' ንብረት ' ነው የሚባለው ወርዷል ወይ ? ይባላል፤ ታፍንና ይዘህ 27 ወጣት አንድ ቤት ትዘጋና ቤተሰቦች አላቸው ውጭ ሀገር የሚባሉት ሰዎች አካውንት እየተጠየቀ እያንዳንዱ ሰው በትንሹ 4000 ዶላር እንዲያስገባ ተደርጎ (20 ሰው ካፈንክ 80 ሺህ ዶላር ታስገባለህ) በዚህ የውጭ አካውንት ከፍተው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እየሸጡ፣ እያገቱ ገንዘብ እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ አመራር የሚሰጡ ከፍተኛ አመራሮች አሉ" ብለዋል።

ይህ ተግባር መጀመሪያ በኤርትራውያን መጀመሩን ከዛም ወደ ትግራይ ተወላጆች መዞሩን ተናግረዋል።

እዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ተደርጎ አመራሮቹ ለህግ እንዲቀርቡ ሙከራ ቢደረግም ማቅረብ እንዳልተቻለና 2 ዓመት እንደሆነው ጠቁመዋል።

አቶ ጌታቸው "ይሄን የሚመራ የመረጃ መምሪያ ኃላፊ እርምጃ እንዲወሰድበት ወይ ከስራ እንዲነሳ ብለን ወስነን ስናበቃ ለማስፈጸም ኃላፊነት የሚሰጣቸው የፀጥታ አመራሮች አላስፈጸሙም" ሲሉ ተናግረዋል።

የፀጥታ አመራሮች በባህሪያቸው ጥፋት ያጠፋውም ያላጠፋውም የመተጋገዝ ባህሪ አላቸው ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ ጌታቸው በወርቅ ንግድ ውስጥ ስላሉ አመራሮችም በዝርዝር ተናግረዋል።

"ወርቅ ንግድ ውስጥ የገባ ' ለትግራይ ነጻነት እስከመጨረሻው እሰዋለው ' እያለ የሚፎክር ጀነራል አለ አሁንም፤ እንዲህ አይነቱን የወርቅ ንግድ ውስጥ ነው ያለኸው ሊባል ይገባል" ብለዋል።

አቶ ጌታቸው እነ ጀነራል ምግበ በወርቅ ንግድ ውስጥ ተሰማርተው እንደሚገኙ በስም ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል።

"እነ ምግበ የሰሩት ጀግንነት የወጣት መስዕዋት መሰረት ተደርጎ የመጣ ጀግንነት ነው" ያሉት አቶ ጌታቸው "እነዛን ወጣቶች ለስደት በሚዳርግ ደረጃ ወደ ተራ የወርቅ ንግድ ገብተው ሲያበቁ የስርቆት ተግባራቸውን የትግራይ ግዛት አንድነት የማረጋገጥ አርገው እየገለጹ እንደገና ይሄን ወጣት ለሌላ መስዕዋትነት ሊዳርጉ እየተንቀሳቀሱ ነው" ብለዋል።

"እነ ኃይለስላሰም አሁን በትግራይ ህዝብ አንድነት ስም የትግራይን ወጣት ከኤርትራም ጋር ቢሆን አብሬ ለማገዶነት እንዳርገዋለው በሚል በጀግንነት ስም እየፎከረ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

እነ ምግበ ፣ እነ ኃይለስለሰ ፣ ኮሎኔል ተወልደን "በወንጀል የተነከሩ ሰዎች ናቸው" ብለዋቸዋል።

ድንገት ሰላም ቢፈጠር "ተጠያቂ እሆናለሁ፤ አደጋ ውስጥ እገባለሁ" ብለው ስለሚያስቡም ግርግር እንዲያልቅ አይፈልጉም ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

የትግራይን ህዝብ ለሌላ ጦርነት ለማስገባት እያሰቡ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ጌታቸው " የፌዴራል መንግሥት ድንገት ውጊያ ይገጥመናል " በሚል ስጋት ውጊያው ትግራይ ውስጥ እንዲካሄድ የሚያስችል ስትራቴጂ ተቀይሶ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል።

" ሰላም መፈጠር አለበት፤ በኢትዮጵያም በኤርትራም መካከል ጦርነት መፈጠር የለበትም፣ የኤርትራ ህዝብ ለአደጋ መዳረግ የለበትም እምነቴ ነው። ግን መምረጥ ካለብኝ የትግራይ ህዝብ ድጋሚ የጦር አውድማ የሚሆንበት ሁኔታ እስከመጨረሻው ድረስ እንዳይሆን እታገላለሁ " ብለዋል።

በዚህ ትግል እንቅፋት የሆኑት የወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩት ዘራፊዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

" ' ግንባር አዛዥ ነኝ ' ይላል ወርቅ ሲዘርፍ ነው የሚውለው " ብለዋል።

"በ2014 ወጣቶች በየግንባሩ ሲተናነቁ በርቀት ዳባት፣ደባርቅ ፣ሊማሊሞ ሆኖ ውጊያ ይመራ የነበረ ሰው በተመሳሳይ ሰዓት በኤክስካቫተር ወርቅ እየቆፈረ ይሸጥ ነበር" ሲሉ ተደምጠዋል።

በዚህ የዝርፊያ ኔትዎርክ ፖለቲከኛውም እንዳለ ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈ አቶ ጌታቸው በመቶ ሚሊዮን ዘርፏል ስላሉት ኃለስላሰም ተናግረዋል።

" ኮምቦልቻ issue account ነበር፤ በዛ ሰዓት ጦርነት ላይ ገንዘብ ስለሚያስፈልገን ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰነው የግል ባንኮች ሳንነካ የመንግሥት እንውሰድ ብለን ፓለቲካሊ ወሰንን እኔ እንደማውቀው 4 ቢሊዮን ብር ነበረው issue account ላይ ይሄን ከብሔራዊ ባንክ ማረጋገጥ ይቻላል ጊዜያዊ አስተዳደር ከሆንኩም በኃላ ወረቀት መጥቶልኛል ምን እንደተፈጠረ ባንኮች ውስጥ ግለጹልን የሚል እና issue account ውስጥ ያለውን ገንዘብ እንዲሰበስቡ ከተመደቡት ሰዎች መሃል አንዱ የግንባር አዛዥ የሚባለው ኃይለስላሰ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ነው የወሰደው ወደ አንድ ቢሊዮን አካባቢ ገንዘብ ነው የወሰደው እሱ ስር ተፍ ተፍ የሚሉ የሱ አገልጋዮች የተወሰነ ድርሻቸውን የወሰዱ አሉ " ብለዋል።

አብዛኛው ሰው ትግሉን ለትግራይ ህዝብ ካለው የህልውና ጥቅም አንጻር እንጂ "ገንዘብ አገኝበታለሁ" ብሎ አይደለም የተሳተፈው ሲሉ ተናግረዋል።

"እኔ በማውቀው ባረጋገጥኩት በሰነድ ጭምር እነ ኃይለ የወርቅ ማሽኖችን ሲያስገቡ ነው የሚውሉት" ብለዋል።

የፖለቲካ አመራሩም አብሮ የወርቅ ንግድ ውስጥ መሰማራቱን ጠቁመዋል።

ሰዎቹ ማሽን ሲያዝባቸው የፌዴራል ሰዎች ጋር እየተደዋወሉ "እናተን የመሰለ ሰው የለም" እያሉ እየተለማመጡ ማሽን ለማስለቀቅ እንደሚሞክሩ ገልጸዋል።

በጥናት " እገለ እግሌ 300 ሚሊዮን ወስዷል በቁጥጥር ስር ይዋል፣ እገሌ ይሄን ያህል ማሽነሪ ወስዷል በቁጥጥር ስር ይዋል እርምጃ ይወሰድ " ከተባለ 2 ዓመት እንደሆነው አመልክተዋል።

የቀረበውን የጥናት ዶክመት እነ ደብረጽዮን (ዶ/ር) እንደሚያውቁት ጠቁመዋል።

ትግሉ ውስጥ ትልልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ሰዎች ስም ሌሎችን ይዞ እንዳይጠፋና የውሸት አንድነት ለማስቀጠል ሲባል እምርጃ መውሰድ አልተቻለም ብለዋል።

"የመረረኝ ሰዓት እርምጃ እንዲወሰድ ዶክመንት አቅርቤም ተግባራዊ አልተደረግም" ብለዋል።

እነ ምግበን፣ እነ ኃይለስላሰን በስም ጠቅሰን መጠየቅ ስላልቻልን "ሁሉም የሰራዊት አመራሮች ዘርፈዋል" የሚል የጅምላ መልዕክት እያስተላለፍን ነው የመጣነው ይህ ውሸት ነው ብለዋል።

ተጠያቂነት እንዳይሰፍን የፖለቲካ መሪዎቹ እንቅፋት እንደሆኑ ይህን የሚያደርጉትም እነሱም ተጠያቂ ስለሆኑ እንደሆነ አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አድርገዋል።

አብዛኛው የሰራዊት አመራር ግን ሰላም ፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
🤔1.8K628😡200😭109😱106🕊86👏77🙏58💔34🥰29😢28