TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል። የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው። ሌቪት ፥ ትራምፕ…
#ዴሞክራሲ #አሜሪካ

" ሕዝቡ የሚመርጠውን እንቀበላለን " - ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን

ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የ2024 የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫን ዶናልድ ትራምፕ ካሸነፉ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር አድርገዋል።

በዚህም ፥ ለተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ስልክ ደውለው " የእንኳ ደስ ያለዎት !" መልዕክት ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል።

ባይደን ከዲሞክራቷ ዕጩ ካማላ ሀሪስ ጋር እንደተናጋገሩ አስታውቀው " መልካም አጋር እና የሕዝብ አገልጋይ ናት " ብለዋል።

የካማላ የምርጫ ዘመቻን " አነቃቂ " ሲሉ ያሞገሱት ባይደን ምክትል ፕሬዝደንቷ በሥራቸው እንዲኮሩ መክረዋል።

" አንዲት ሀገር ምርጫዋ አንድ ነው። ሕዝቡ የሚመርጠውን እንቀበላለን " ሲሉም ተናግረዋል።

ባይደን " ስናሸንፍ ብቻ አይደለም ሀገራችንን የምንወደው፤ ስንስማማ ብቻ አይደለም ጎረቤታችንን የምንወደው " የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንደሚኖርም አስታውቀዋል።

የምርጫ አስተባባሪዎችም " ምስጋና ይገባቸዋል " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥር 12/2017 በኦፊሴላዊ መንገድ መንበረ-ሥልጣኑን ይረከባሉ።

የ2024 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ " ታሪካዊ ነው " ያሉት ባይደን በሚቀጥሉት 74 ቀናት ያልተቋጩ ሥራዎችን ጨርሰው ሥልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ አሳውቀዋል።

" መሸነፍ ያለ ነው። ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ ይቅር የማንለው ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ የሆነው ለፕሬዝዳንትነት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፎካከሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለተመራጩ ፕሬዝዳንት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ሃሪስ፥ ለትራምፕ ስልክ ደውለው " እንኳን ደስ አለዎ " ማለታቸው ተዘግቧል።

ሃሪስ ለትራምፕ ስልክ ደውለው የ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን በማሸነፋቸው ውጤቱን መቀበላቸውን የሚያመለክት መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
773👏202🕊47🙏39😡38😢17😭14🤔12😱11🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #China ቻይና በአሜሪካ ላይ አፀፋዊ የሆነ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች። ቻይና ከዚህ በፊት ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ84% ታሪፍ ጥላ የነበረ ሲሆን ዛሬ ሌላ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች። የቻይና የፋይናንስ ሚኒስትር ከአሜሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ84% ወደ 125% ከፍ መደረጉን አስታውቀዋል። የትራምፕ አስተዳደር  በቻይና ላይ የተጣለው አጠቃላይ ታሪፍ 145% መሆኑን የገለፀ…
#USA #CHINA

የአሜሪካ እና የቻይና የታሪፍ ጦርነት !

ወደ አሜሪካ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከጣሏቸው የአፀፋ ታሪፎች ነፃ መሆናቸውን የአሜሪካ የጉምሩክ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

➡️ ስማርት ስልኮች፣
➡️ ኮምፒዩተሮች
➡️ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ክፍሎች ትራምፕ ከጣሉት ታሪፍ ነፃ መደረጋቸውም ተዘግቧል።

ውሳኔው የመጣው የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር በቻይና ላይ የ145% አጠቃላይ ታሪፍ መጣሉን ካስታወቀ በኋላ ሲሆን የታሪፉ መጣል እንደ አፕል ላሉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክ ምርት አምራቾች ስጋትን ፈጥሮም ነበር።

አፕል 90% የሚሆነውን የአይፎን ስልክ የሚያመርተው እና የሚገጣጥመው በቻይና ሲሆን ካውንተር ፖይንት የተሰኘው የጥናት ተቋም አፕል በአሜሪካ ያለው ክምችት ለ6 ሳምንታት ብቻ የሚሆን እንደሆነና እሱ ካለቀ የምርቱ ዋጋ መጨመር እንደሚጀምር ገልጾ ነበር።

አፕል ከአይፎን በተጨማሪ 80% የሚሆነውን አይፓድ እና ከ50% በላይ የሚሆነውን የማክ ኮምፒዩተር ምርቶቹን በቻይና እንደሚያመርት ተገልጿል።

አፕል ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነውን የአይፎን ምርት የሚሸጠው በአሜሪካ እንደሆነ ሲነገር በቻይና ላይ ታሪፍ መጣሉን ተከትሎ አብዛኛውን ምርቱን በህንድ ማምረት ለመጀመር ማሰቡም ተነግሮ ነበር።

አፕል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፀፋ ታሪፍ በሃገራት ላይ መጣል ከጀመሩ በኋላ የገበያ ዋጋው በ640 ቢሊየን ዶላር መቀነሱ የተዘገበ ሲሆን ከ600 ቶን በላይ ክብደት ያላቸው 1.5 ሚሊየን የአይፎን ስልኮችንም ከህንድ ወደ አሜሪካ በአውሮፕላን አጓጉዞ ማስገባቱ መዘገቡ ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንትና አንዳንድ ምርቶች በሚታወቁ ምክንያቶች እሳቸው ከጣሉት ታሪፍ ነፃ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረው ነበር።

ትራምፕ በጣሉት ታሪፍ የተነሳ የአይፎን ስልክ ዋጋ በሶስት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ስጋቶች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶቹ ከአፀፋዊ ታሪፉ ነፃ መሆን ትልቅ ዕድል እንደሚሆን ተዘግቧል።

በውሳኔው መሰረትም #ሳምሰንግን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራቾች ወደ አሜሪካ ምርታቸውን ሲልኩ ይጠብቃቸው ከነበረው የ10% መሰረታዊ ታሪፍም ነፃ መሆናቸው ተነግሯል።

ከታሪፉ ነፃ የሆኑ 20 የምርት ዘርፎች የተቀመጡ ሲሆን ለሴሚ ኮንዳክተር መሳሪያነት የሚያገለግሉ ማሽኖችም ከታሪፉ ነፃ መሆናቸው ታውቋል።

ኋይት ሃውስ፣ የአሜሪካ የአለም አቀፍ ንግዶች ኮሚሽን እና የአሜሪካ የንግድ ቢሮ በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።

#ዓለምአቀፍ #የታሪፍጦርነት #ቻይና #አሜሪካ

@tikvahethiopia
304🤔76🙏24👏21💔16🕊14😭13🥰10😡10😢4😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #CHINA ቻይና አንዳንድ የአሜሪካ ምርቶችን ከጣለችው የ125% ታክስ ነፃ አደረገች። ቻይና ከአሜሪካ ወደ ሃገሯ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶች ከጣለችው የ125% ታሪፍ ነፃ ማድረጓ እና ድርጅቶች ከታክስ ነፃ መሆን አለባቸው ብለው የሚያስቧቸውን ወሳኝ ዕቃዎች ለይተው እንዲለዩ መጠየቋን ሮይተርስ ከምንጮች አረጋግጦ ዘግቧል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለታይም መፅሄት በሰጡት ቃለ መጠይቅ…
#ቻይና #አሜሪካ #ታሪፍ

አሜሪካ እና ቻይና በምርቶቻቸው ላይ ጥለውት የነበረውን ታሪፍ ለመቀነስ ተስማሙ።

ሁለቱ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች በተደጋጋሚ የአፀፋ ታሪፎችን እርስ በራሳቸው ሲጣጣሉ የነበረ ሲሆን በጄኔቫ ከተደረገ ውይይት በኋላ የአፀፋ ታሪፎቹን በ115% ለመቀነስ ተስማምተዋል።

አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ ጥላ የነበረውን የ145% ታሪፍ በመቀነስ ወደ 30% ያወረደች ሲሆን ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ ጥላ የነበረውን የ125% ታሪፍ ወደ 10% ቀንሳለች።

አዲሱ የታሪፍ ቅነሳም ለሚቀጥሉት 90 ቀናት በስራ ላይ ይቆያል ተብሏል።

የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሃላፊው ስኮት ቤሰንት የታሪፍ አፀፋዎቹ ሁለቱም ሃገራት የማይፈልጉት ነው በማለት ሃገራቱ አብረው መነገድ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ቤሰንት አዲሱ ስምምነት አንዳንድ ሴክተሮች ላይ የተጣሉ ታሪፎችን እንደማይመለከት የገለፁ ሲሆን
አሜሪካ በመድሃኒት፣ ሴሚ ኮንዳክተር እና ብረት ላይ አሁንም ስትራቴጂካዊ የንግድ ሚዛንን ማስጠበቋን ትቀጥላለች ብለዋል።

በተጨማሪ ቻይና ከታሪፍ በተጨማሪ ውድ ማዕድናት ወደ
አሜሪካ እንዳይላኩ ያስቀመጠችውን እገዳ ጨምሮ ሌሎች ከታሪፍ ውጪ የሆኑ የንግድ እገዳዎችን ታነሳለች ተብሏል።

የጄኔቫው ውይይት በሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ከትራምፕ ወደ ስልጣን መመለስ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያ ውይይት ሲሆን በጊዜያዊነት ቢሆንም ሃገራቱ ከገቡበት የንግድ ጦርነት ፋታ እንዲወስዱ አድርጓል።

ሁለቱ ሃገራት ወደ ንግድ ጦርነቱ ከገቡ በኋላ የ600 ቢሊየን ዶላር የንግድ እንቅስቃሴ መቆሙ ከመነገሩ በተጨማሪ የሁለቱንም ሃገራት ኢኮኖሚ በክፉኛ ተጎድቷል።

ቻይናና
አሜሪካ ይህ የመጀመሪያው ንግግር መሆኑን ያስታወቁ ሲሆን በንግድ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ በቀጣይ በቻይና አሊያም በአሜሪካ ወይም በአማራጭነት በሶስተኛ ሃገር ውይይቶች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የመረጃው ምንጮች ሲኤንኤን እና ሮይተርስ ናቸው።

@tikvahethiopia
👏479106🤔42🕊37🥰26🙏12😡10😭9😢4💔4😱1