TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Adigrat

🚨 " በር ሰብረው ነው የገቡት " - አቶ ኪዱ ገብረ ፃድቅ (የትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የፀጥታ ኃላፊ)

➡️ " እኛ በር ሰብረን አልገባንም ህዝቡ ግቡ ብሎ በሰልፍ ስለመጣ ነው " - አቶ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔር


ከዚህ ቀደም የዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባዎች (አንድ በጊዜያዊ አስተዳደሩ አንድም እነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት) እንደተሾሙባት ይታወቃል።

ማክሰኞ በደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ቡድን የተሾሙት ከንቲባ በሰራዊት ኃይል በመታገዝ በኃይል በር በመስበር ፅ/ቤቱን እንደያዙት የምስራቃዊ ዞን የፀጥታ ኃላፊ አቶ ኪዱ ገብረ ፃድቅ አሳውቀዋል።

አቶ ኪዱ ገብረ ፃድቅ ምን አሉ ?

" የሰራዊቱ አመራሮች ' በምክር ቤት ለተመረጠው ከንቲባ አስረክቡ ' በማለት ወደ ከተማዋ ሰራዊት አስገብተዋል። ወደ ከንቲባ ፅ/ቤትም በኃይል ገብተዋል። ቁልፍ የላቸውም ሰብረው ነው የገቡት " ብለዋል።

አቶ ኪዱ ሰኞ ዕለት በዓዲግራት መግቢያ ቤተ ሓርያት በተባለ አካባቢው " ወጣቶች እያደራጃቹ ነው " በሚል በፀጥታ ኃይሎች ለ 4 ሰዓታት ታግተው ነው የተለቀቁት።

ማክሰኞ ቁልፍ ሳይኖራቸው በሩን ሰብረው ገብተዋል የተባሉት አቶ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔር ፤ " ሰብረን አልንገባንም " ብለዋል።

አቶ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔር ምን አሉ ?

" በህዝብ ሳይመረጥ በራስ ፍላጎት ብቻ በስልጣን ላይ የመቆየት ፍላጎት ስለነበረ ህዝቡ አገልግሎት አጥቶ ለሶስት ወራት ቆይቷል።

እኔ በምክር ቤት ተሹሜ ለሶስት ወራት ፅ/ቤት ሳልገባ መንገድ ዳር ነበርኩኝ። ችግሮች እንዳይፈጠሩ ስላሰብን ነው እስካሁን የቆየነው። አሁን ሰብረን አይደለም የገባነው የከተማው ህዝብ ከየአቅጣጫው ወጥቶ ' በሩ ይከፈት ' ብሎ ጠየቀ መልስ በማጣቱ ገፍቶ ነው የገባው በዚህም ወደ ፅ/ቤት ገብተናል " ብለዋል።

የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ራቅ ብለው ይከታተሉ ነበር እንጂ ወደ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ አልገቡም ሲሉ አክለዋል።

#VOATIGRIGNA

@tikvahethiopia
😁420🕊114102😭39🤔33😡16👏11🙏11😢9🥰3