TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ፈተናውን ብዙዎቹ ሊያልፉ ይችላል የሚል ግምት ነው የተያዘው " - የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች መካከል #ተመሳሳይ የብሔር ማንነት ያላቸው አመራሮች ብዛት ከ40 በመቶ እንዳይበልጥ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል። በቅርቡ ለሚተገብረው #የሠራተኞች_ድልድል ሲባል…
#Update
" ፈተናው በ3 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ይሰጣል " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
ከ16 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ነገ አርብ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ.ም. ለፈተና ይቀመጣሉ።
ይህን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከ11ዱ ክፍል ከተማ ከተውጣጡ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ ከስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ከተመረጡ 16 ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ኦረንቴሽን እና ውይይት አካሂዷል።
በዚህ ወቅት ምን ተባለ ?
- በቅርቡ በሚተገብረው የሠራተኞች ድልድል መነሻ ከ16 ሺህ በላይ የከተማ አስተደደሩ ሠራተኞች ነገ አርብ ፈተና ይቀመጣሉ።
- ፈተናውም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በከተማው በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በቀን 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ 7 ስዓት ጀምሮ እንደሚሰጥ ይሰጠል።
ተፈታኞች በፈተናው ወቅት ማሟላት የሚገባቸው እና የተከለከቱ ተግባራት ምንድናቸው ?
* በሰዓቱ በፈተናው ስፍራ መገኘት፤
* የግል መታወቂያ (ID CARD) መያዝ፤
* ምንም አይነት ፅሁፎችን እና ወረቀት፣ የእጅ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እንዲሁም መሰል ቁሳቁሶችን ይዞ ወደ ፈተና መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው፤
* በተሰጠው ሰዓት ፈተናውን አጠናቆ መውጣት ይገባል።
- በፈተናው ወቅትም ምንም አይነት የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር ቢሮው ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እንዲሁም ከፀጥታ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ ነው።
- ለተፈታኞች በቂ የትራንስፖርት ስምሪት ስራ የከናወናል ተብሏል።
- ለፈተና በተለያየ ምክንያት መገኘት ያልቻለ ተፈታኝ ምክንያቱ ታይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ለፈተና የሚቀርብበት መንገድ ይመቻቻል ተብሏል።
- ፈተናውም በ3 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ይሰጣል።
ተጨማሪ ፦
☑️ ፈተናው የባህሪ እና የቴክኒክ ምዘናዎችን የያዘ ነው። የሚሰጠው የቴክኒክ ምዘና ሠራተኞቹ ከሚሠሩት ሥራ ጋር ግንኙነት ያለው ነው። የባህሪው ፈተና ደግሞ አገልግሎት አሰጣጡን የሚፈታተኑ የባህሪ ችግሮች ስላሉ ያንን ክፍተት ለመሙላት አመላካች እንዲሆን ተስቦ የተዘጋጀ ነው።
☑️ የምዘና ፈተናው የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በጋራ ትብብር ነው።
☑️ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርስቲ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ነው።
☑️ የከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎች ፈተናውን ለማለፍ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
☑️ ከዚህ የማለፊያ ውጤት በታች የሆነ ነጥብ ያገኘ ባለሙያ ከደረጃው ዝቅ ብሎ ባሉት የአስተዳደር እርከኖች ላይ ይመደባል።
☑️ ለዳይሬክተሮችና ለቡድን መሪዎች የፈተና ማለፊያ ነጥብ 60 በመቶ ነው። ይህን ነጥብ የማያመጡ አመራሮች ለዳይሬክተርነት / ለቡድን መሪነት ኃላፊነት #መወዳደር_አልችሉም።
☑️ በመ/ቤት ካሉ የሥራ መደቦች መካከል በተመሳሳይ ማንነት / ብሔር የተያዙት ከ40 በመቶ እንዳይበልጡ ይደረጌ። ድልድሉን ሲያከናውኑ ይህንን #የብሔር ስብጥሩን ለመጠበቅ እንዲችሉ " ብቃት ያላቸውን ሠራተኞች ከሌሎች መ/ ቤቶች በመለየት በዝውውር እንዲሟሉ " ይደረጋል።
☑ ከ40% መብለጥ የለበትም በሚል የተቀመጠው አሠራር፤ የሚተገበረው የቡድን መሪዎች እንዲሁም የዳይሬክተሮች ድልድል ላይ ብቻ ነው። በዚህ ድልድል ወደ #ሠራተኛው የወረደ እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም። የድልድል ደንቡ ውስጥም የለም።
@tikvahethiopia

😡1.59K❤473👏318😭87🙏82🕊45😢44😱38🥰37