TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ታጋቹ ከ3 ወር መሰወር በኃላ የማስለቀቂያ ክፍያ ተጠየቀባቸው።  "አጋቾች ነን" ባዮች የጠየቁት ገንዘብ በ1 ሳምንት ጊዜ ካልተከፈላቸው ታጋቹን እንደሚገድሉት እንደዛቱ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እገታው እንዴት እና መቼ ተፈፀመ ?  የሰዎች እገታ ከህፃናት አልፎ እድሜያቸው በገፉት ላይም በመቀጠል በህብረተሰቡ ውስጥ ቀውስን ማቀጣጠል መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል። ታጋቹ…
#Update

ታግታ ከተወሰደች በኃላ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታጋዲዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች 20 ቀናት ሆኗታል።

ቤተሰቦቿ " ልጃችንን አፋልጉን " ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል። መላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና የፀጥታ ኃይል ልጃቸውን እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ቤተሰቦች ከትግራይ ዓድዋ ከተማ ያስተላለፉት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ ምን ይላል ?

የማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦች ፦

" ታዳጊ ልጃችን ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ከ 11:00 ሰዓት በኃላ ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት በመሄድ ሳለች በትግራይ ዓድዋ ከተማ ዓዲ ማሕለኻ ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍና ተወስዳለች።

አጋቾቹ በወሰዱዋት ቀን በራስዋ ሞባይል ስልክ ወደኛ በመወደወል ለማስለቀቅያ 3 ሚሊዮን ብር እንድንከፍላቸው ጠይቀውናል።  ከዛ በኃላ ግን በደውሉበት የልጃችን የሞባይል ቁጥር ብንደውልም አናገኛቸውም፤ በሌላ የሞባይል ቁጥር ደውለውም ያሉን ነገር የለም።

ስለሆነም እኛ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ወላጆች በከፍተኛ ጭንቅና ሃዘን ውስጥ እንገኛለን። ስለዚህ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና የፀጥታ አካላት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ እናቀርባለን። "

ማህሌት ተኽላይ የሚመለከት ማንኛውም አይነት መረጃ ለመስጠት ፦
+251938819844 ሙሴ ተኽላይ
+251992733943 ደጀን ተኽላይ 
+251935036100/
+251962529287 ሚልዮን ተኽላይ
በሚሉ የሞባይል ቁጥሮች እንድትጠቀሙ በትህትና እንጠይቃለን። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁኔታውን እንዲያብራሩ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦችን ጠይቆ ፥ " የዓድዋ ፓሊስ እኛን መልሶ ምን አዲስ ነገር አለ ብሎ ይጠይቀናል ? " ሲሉ መልሰዋል።

የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ #ዓድዋ እና #አክሱም ያደረገው ጉዞ በፓሊስ አመራሮች ስብሰባ ምክንያት አልተሳካም።

#TikvahFamilyMekelle
                                            
@tikvahethiopia            
😢1.05K😭235161🙏68😱29😡27🕊25👏10🤔10🥰3
#አክሱም

🧕" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች

➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

👉 " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም " - የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በትግራይ ፣ አክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት 2 ሳምንታት የራስ መሸፈኛ ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት እንደተከለከሉና በዚህም ከትምህርት ገበታ መውጣታቸውን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ከሂጃብ መልበስ ጋር በተያያዘ በአክሱም በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውዝግቡ የጀመረው ጥቅምት ወር ነው።

ተቋሙ ለክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቆ አውንታዊ ምላሽ ቢሰጠውም በተግባር የተቀየረ ነገር ግን የለም።

የምክር ቤቱ ፀሀፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ ምን አሉ ?

" ፀጉራቸውን ሸፍነው ትምህር ቤት እንዲሄዱ ማየት ያልተፈቀደበት መታየት የለበትም ፀጉሯ የአንድ ሴት ይሄ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው።

ሃይማኖት ውስጥ ፖለቲካ አይገባም፣ ፖለቲካ በሃይማኖት አይገባም እየተባለ በአንቀጽ ተቀምጦ እያለ አሁን ፖለቲካ በሃይማኖት እየገባ ነው።

ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል የፀጉር መሸፈኛ ሂጃብ መጠቀም እንደሚችሉ በ2000 ዓ/ም የወጣ ሀገር አቀፍ መመሪያ አለ።

ስለዚህ ዝም ብለን የምናየው ነገር አይሆንም።

በአሁኑ ጊዜ በአራት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ወጥተዋል።

ዋናው ደግሞ 3 ወር ሲማሩ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና የኦንላይ ምዝገባ የሚደረግበት ወቅት ነው በዚህ ሳምንት ያልቃል የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች እስካሁን አልተመዘገቡም።

የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል፤ አልገቡም እስካሁን።

ችግሩ እንዲፈታ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ትምህርይ ፅ/ቤት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው " ብለዋል።


ተማሪዎች ምን ይላሉ ?

" በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመታት ከሌሎች  ተማሪዎች ወደኃላ ቀርተናል አሁን ደግሞ በሂጃብ ምክንያት ፈተና ሊያመልጠን ነው።

ፎርሙ እያመለጠን ነው። ሌሎች ተማሪዎች በሂጀብ ፎርም እንደሞሉ ነው የምናውቀው። እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው።

ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም ፤ መፍትሄው ደግሞ በጣም አስቸኳይ እና ዘላቂ መሆን አለበት። እስካሁን መብታችን እየተከበረ አይደለም " ብለዋል።

NB. የክልል ትምህርት ቢሮ እና የአክሱም ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን አለ ?

ምክትል ርዕሰ መምህር ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር ፦

" ' ትምህርት ቤቶች ከሃይማኖት እና ከፖለቲካ ነጻ መሆን አለባቸው ' ይላል የትግራይ ክልል የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም።

ክርስቲያኑ መስቀል ወይም መጠምጠሚያ ፤ ሙስሊሙም ሂጀብ ወይም ኮፍያ ማድረግ አይፈቀድም። የትምህርት ቤቱ መለያ ዩኒፎርም ብቻ ነው መልበስ የሚገባው።

የተወሰኑ ተማሪዎች ሂጃባቸውን አናውልቅም ብለው ነበር አሁን ግን ተማሪዎች የትምህት ቤቱን መመሪያ ተከትለው እየገቡ ናቸው።

አሰራሩ ለዓመታት የቆየ ነው " ብለዋል።


አንድ በጉዳዩ ላይ ቃላቸው የሰጡ የክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኛ ፤ " በክልሉ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እየሆነ ያለው በ1995 የወጣ መመሪያ ነው በዚያ መመሪያ ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን መተዳደሪያ ማውጣት እንደሚችሉ ይደነግጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ትግርኛ አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
😡2.87K614😭234👏187🙏109🕊88🤔70🥰53😢47😱15
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሂጃብሂጃብ #አክሱም

" ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ #እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ ታዟል " - ፍርድ ቤት

በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎችን ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ክልከላ አድርገዋል በተባሉት አካላት ላይ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ህጋዊ ክስ መስርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ከምክር ቤቱ ጠበቃ አረጋግጧል።

በተመሰረተው ክስ መሰረት ተከሳሾች ለጥር 16/2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸው እንዲሰጡ የመጥሪያ ትእዛዝ ተፅፎላቸዋል።

የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ለተከሳሾች የፃፈው የመጥሪያ ትእዛዝ ሙሉ ይዘት ምን ይላል ?

ከሳሽ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሲሆን ተከሳሾች ደግሞ :- 
የአክሱም ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 
አብራሃ ወ አፅብሃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ወርዒ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ክንደያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ናቸው።

በዚሁ ደብዳቤ ላይ ተከሳሾች በወሰኑት አስተዳደራዊ ውሳኔ መሰረት የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን በቀረበቅ ማመልከቻ መረዳት እንደተቻለ ተገልጿል።

ፍርድ ቤቱ ፤ የተሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔ እግድ ካለተጣለበት በሴት ተማሪዎቹ ላይ የማይመለስ የመብት ጥሰት ሊያጋጥም ስለሚችል ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ አዟል።

ተከሳሾችም በቀረበው የእግድ ማመልከቻ መሰረት ቀርበው ቃል እንዲሰጡ በፍርድ ቤቱ ለቀን 16/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ተቀጥረዋል።

NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠበቃ ማረጋገጥ ችሏል።

159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከሂጃብ ክልከላ በተያያዘ ትናንት የተጠናቀቀውን 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የሚያስችላቸውን ፎርም ሳይሞሉ መቀረታቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መግለጹ ይታወሳል።

ጉዳዩን እስከመጨረሻውን የምንከታተለው ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
8😡547👏517159🙏55😭49🕊43🤔18😢17😱9🥰6