#Update
ኢትዮጵያ #ድምፀ_ተአቅቦ ያደረገችበት የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባኤ ተካሄደ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዓርብ ምሽት በእስራኤል እና ሃማስ የጋዛ ጦርነት ጉዳይ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ አካሂዷል።
በዚህም ጉባኤ በ " ዮርዳኖስ " አቅርቢነት በጋዛ " አስቸኳይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም " እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ ነበር።
የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ የቀረበበት የውሳኔ ሀሳቡ ፦
- በ120 ድጋፍ፣
- በ14 ተቃውሞ
- በ45 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።
በዚህም መሰረት ተመድ በጋዛ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።
የውሳኔ ሃሳቡን ከተቃወሙት ውስጥ አሜሪካ ፣ እራሷ እስራኤል ፣ ሃንጋሪ ፣ ኦስትሪያ ይገኙበታል።
ድምፅ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ፣ ግሪክ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስውዲን፣ ኢራቅ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ሕንድ ፣ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን፣ ቱኒዝያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ ይገኙበታል።
የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ የተካሄደው በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ነው።
እስራኤልም በጋዛ የምድር ዘመቻ ማካሄድ ጀምራለች።
የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ አማካሪ ማርክ ሬጅቭ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን #ሃማስ በሰብአዊነት ላይ በርካታ የግፍ ወንጀሎችን መፈፀሙን ገልጸው ለዚህም ደግሞ ከዓርብ ምሽት (ትላንት) ጀምሮ ክፍያውን #እንደሚከፍል እና እስራኤልም መመለስ መጀመሯን ተናግረዋል።
ሀማስ እስራኤል ለምታካሂደው የምድር ላይ ዘመቻ አፀፋውን ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ገልጿል።
የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ከፍተኛው አመራር ኢዛት አል-ሪሻቅ " ኔታንያሁ ወደ ጋዛ ለመግባት ከወሰነ እኛም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን " የወታደሮቹ ሬሳ በጋዛ ምድር ይዋጣል " ብለዋል።
21ኛ ቀኑን በያዘው በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት በእስራኤል ጥቃት ጋዛ የተገደሉ ሰዎች ከ7300 መብለጣቸውን በሃማስ ስር ያለው የጤና ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በእስራኤል በኩል በሃማስ የተገደሉም ከ1400 በልጠዋል።
ℹ️ ተጨማሪ #የውጭ_ሀገር_መረጃዎችን በዚህ መከታተል ይችላሉ 👉https://tttttt.me/+LM-bJ8NzZMcxMjA8
@tikvahethiopia

😡820❤276👏267🕊242😭139😢80🙏44😱39🥰28
#Puntland #Somalia
ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች።
ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች።
የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና እንዳነሳች አሳውቋል።
ምክንያቱ ምንድነው ?
የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ ብዙ ባወዛገበ ሂደት በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።
የሕገ መንግሥት ማሻሻያው ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የማሰናበትን ሙሉ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን ‘ አንድ ሰው አንድ ድምጽ ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርግና ሌሎችም ማሻሻያዎች አሉበት።
NB. በሶማሊያ #ውስብስብ የሆነውን እና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ከ50 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ አሁን ' አንድ ሰው አንድ ድምፅ ' የሚለው ማሻሻያ በፑንትላንድ ባለልስጣናት ተቃውሞ ገጥሞታል።
በአጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት ያካሄደው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በፑንትላንድ አልተወደደም ውድቅም ተደርጓል።
ፑንትላንድ ፤ " በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም " ብላለች።
ሕዝበ ውሳኔ (#ሪፈረንደም) የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ የሆነ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራት አስታውቃለች፡፡
ከአሁን በኋላ ፍላጎቷን ለማስጠቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ አማካይነት #የውጭ_ግንኙነቶችን እንደምታደርግ ገልጻለች።
ይህ የፑንትላንድ ውሳኔ ከሶማሊያ ተነጥሎ ነጻ አገርነትን ከማወጅ ጋር ሊስተካከል እንደሚችል በመጥቀስ #ከሶማሊላንድ ቀጥሎ ለፌደራል መንግሥቱ ሌላ ራስ ምታት እንደሚሆን ተንታኞች እየገለጹ ነው።
ፑንትለንድ በተፈጥሮ ሃብቶችና #በቦሳሶ_ወደቧ በመተማመን እ.አ.አ 1998 ነው ከፊል ራስ ገዝ መሆኗን ያወጀችው። እራሷን እንደ ነጻና ሉኣላዊ ሀገር የምትቆጥረው የሶማሊላንድ ጎረቤትም ናት።
መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

❤845👏121🕊103🥰48😡44🤔39😭38😢34🙏34😱32