TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀምሯል። ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ ካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደተጀመረ ገልጿል። በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል። ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት ከተማ እየተሰጠ…
" ብሔራዊ መውጫ ፈተናውን ሁሉም በላቀ ውጤት አልፈዋል። ... 70% የማዕረግ ምሩቃን ናቸው " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነገው እለት የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ/ም 249 #የህክምና_ዶክተሮችን እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

ከነዚህ ተመራቂዎች መካከል 70 በመቶ የማዕረግ ምሩቃን ናቸው።

የብሔራዊ የመውጫ ፈተናውን ደግሞ ሁሉም ተመራቂዎች (100%) በላቀ ውጤት አልፈዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ነገ 22 ተማሪዎች በአንስቴዥያ የህክምና ዘርፍ የሚመረቁ ይሆናል።

@tikvahethiopia
👏3.61K467🙏154🥰106🕊52😡29😭26😱20😢17
#ደመወዝ

" ላለፉት ወራት በደሞዝ መዘግየትና መቆራረጥ ስንፈተን ቆይተናል " ያሉ የዎላይታ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች " ስራችንን በአግባቡ ለመስራት እንችል ዘንድ መንግሥት በአግባቡ ደሞዝ ሊከፍለን ይገባል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸው ከሰጡት የመንግስት ሰራተኞች ውስጥ በተለይም #መምህራን እና #የህክምና_ባለሙያዎች ይገኙበታል።

" ጉዳዩን በተዋረድ ለሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ለወረዳ አመራሮች ካሳወቅን ቆየን " የሚሉት እነዚህ ሰራተኞች " ማክሰኞ መጋቢት 17/2016 ዓ/ም ወደ ክልሉ መንግስት መቀመጫ ወደሆነችዉ ወላይታ ሶዶ ከተማ ብናቀናም ሰሚ አላገኘንም " ብለዋል።

በተለይ ይህ የደሞዝ አለመክፈል እና መቆራረጥ ችግር የተከሰተባቸው በዎላይታ ዞን ስር የሚገኙት የኪንዶ ኮይሻ ፣ የሆብቻ ፣ አባላ ፣ አባያ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞት ፑላሳ ፣ ዳሞት ወይዴ ፣ ኪንዶ ዲዳዬ እና አካባቢዉ ወረዳና ቀበሊያት እንደሆኑ ተገልጿል።

በሆብቻ ወረዳ የሚገኘው የሆብቻ ወረዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስራ ካቆመ መሰነባበቱንና ተማሪዎች ቤታቸዉ እየዋሉ መሆኑን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ መምህራን " መንግስት በአፋጣኝ እርምጃ ወስዶ ወደስራችን ይመልሰን " ብለዋል።

ከዚህዉ ጋር ተያይዞ የከልሉን መንግስት ሀሳብ በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ አዜብ ስለጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸዉ በመግለጽ ዝርዝር ሀሳብ ከመሰንዘር ተቆጥበዋል።

ይህን ጉዳይ እየተከታተልን እናሳውቃችኃለን።

መረጃዉን አዘጋጅቶ የላከዉ የሀዋሳው ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
😭21061😢18🤔17👏11😡8😱7🙏7🥰1