የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር ከፋዮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ።
ሚኒስቴሩ ፤ ማንነታቸው በውል ያልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች የተለያዩ የማደናገሪያ እና የማጭበሪያ መንገዶችን እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስም እና ሀሰተኛ ማንነት በመጠቀም ግብር ከፋዮችን #እያጭበረበሩ ይገኛሉ ብሏል።
ይህ የማጭበርበር ተግባር እየተሰራ ያለው የግብር ከፋዩን የስልክ አድራሻ በመጠቀም እንደሆነም ገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል።
የማጭበርበር ተግባሩ የሚፈፀመው እንዴት ነው ?
የግብር ከፋዮችን አድራሻ በመጠቀም ፦
1. ለታማኝ ግብር ከፋይ የሚሰጠውን ሽልማት እንድትሸለሙ እናስመርጣችኋለን፣
2. የኦዲት ውሳኔ #እናስቀንስላችኋለን፣
3. ድርጅታችሁ #ወንጀል_መስራቱ ስለተደረሰበት በህግ እንዳትጠየቁ እናደርጋለን የሚሉና የመሳሰሉ #የማስፈራራት እና #የማግባባት ሙከራዎች እና ዘዴዎችን በመጠቀም ነው።
ገቢዎች ሚኒስቴር ይህ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑ በክትትል ለማወቅ እንደቻለ ገልጾ ግብር ከፋዮች የነዚህ መሰል የማጭበርበር ሙከራዎች ሰለባ እንዳይሆኑ አስጠንቅቋል።
ማንኛውም ግብር ከፋይ ይህ መሰል ሁኔታዎች ሲያጋጥሙትም በአቅራቢያው ለሚገኝ የግብር ሰብሳቢ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአፋጣኝ ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስቧል።
@tikvahethiopia

👍512👎75❤64🙏15🥰11😱6🕊5😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል ! ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች። ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ…
#Update
አሜሪካ ዩጋንዳ ላይ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠነቀቀች።
የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ፤ ኡጋንዳ ትላንት ያፀደቀችውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን #ወንጀል የሚያደርገውን ህግ " አሳፋሪ እና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት " በማለት ተቃወሙ።
ባይደን ፤ " ይህ አሳፋሪ ድርጊት / ሕጉ መፅደቁን / በዩጋንዳ ውስጥ ያለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ሙስና የቅርብ ጊዜ እድገት አመላካች ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዜዳንት ባይደን ፤ የአሜሪካ ብሄራዊ ደኅንነት ም/ ቤት የዩጋንዳው ሕግ አሜሪካ ከአገሪቱ ጋር ባሏት ግንኙነቶች ላይ ምን አንድምታ እንዳለው አጥንቶ እንዲያቀርብ አዘዋል ተብሏል።
ከህጉ ጋር በተያያዘ ፤ አሜሪካ ለኡጋንዳ የምትሰጠውን እርዳታና ኢንቨስትመንት ልታቆም እንደምትችል ባይደን አስጠንቅቀዋል።
የሕጉን ተፅኖ ከግምት በማስገባትም የዩጋንዳ የአጎዋ (AGOA) ተጠቃሚነት እንደሚገመገም አሳውቀዋል።
ፕሬዜዳንቱ በከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወይም ሙስና ውስጥ በተሳተፈ ማንኛውም ሰው ላይ #ማዕቀብ እና ወደ አሜሪካ የመግባት #እገዳን ጨምሮ ተጨማሪ እርምጃዎችን እያጤኑ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ከባይደን በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ፤ ህጉን ተቃውመዋል ፤ መስሪያ ቤታቸውም የአሜሪካ ዜጎች ወደ ዩጋንዳ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ መመሪያ እንዲያወጣ አዘዋል።
የባይደን አስተዳደር የዩጋንዳ ፓርላማ አፈ ጉባኤ " አኒታ አሞንግ " አሁን ያላቸውን የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ መሰረዙ ሮይተርስ ፣ እንዲሁም ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግበዋል።
ከዚህ ቀደም የዩጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።
ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።
ምንም እንኳን ምዕራባውያን ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት (ተመድን ጨምሮ) ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በዩጋንዳ ምድር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል በሚያደርገው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን እንዳያኖሩና እንዳያፀድቁ ማስጠንቀቂያዎችን ቢሰጡም ፕሬዜዳንቱ ትላንት መጠነኛ ማሻሻያ የተደረገበትን ሕግ በፊርማቸው በማኖር #አቅፅድቀውታል።

👎7.16K👍1.79K❤387😢134😱102🙏88🕊62🥰33