TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሶማሌ

በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ።

ዛሬ ከሰዓት በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ፤ ሸበሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።

አደጋው የደረሰው ከጅግጅጋ መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ " ሚኒባስ " ተሽከርካሪ እና ከሸበሌ አቅጣጫ ሲመጣ በነበረ " ሲኖ ትራክ " እየተባለ በሚጠራው ተሽከርካሪ መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው።

ፖሊስ የአደጋውን ምክንያት እያጣራ ሲሆን የሚደርስበትን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ በትራፊክ አደጋው ምክንያት በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው ለቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከክልሉ ቴሌቪዥን (ኤስአርቲቪ ሶማልኛ) ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
😭1.83K😢149129🕊94🙏55😱34🥰28😡17
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Somali #Iftar ዛሬ የአፋር እና ሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች የኢፍጣር መርሐ ግብር በጅግጅጋ እየተካሄደ ይገኛል። በመርሃ ግብሩ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሃጂ አወል አርባ፣ የሰላም ሚንስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል። #SomaliRegionGovCommunication …
#አፋር 🕊 #ሶማሌ

" እኛ እና ሶማሌዎች ከሚያለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች በትልቁ ይበዛሉ " - ሀጂ አወል አርባ

ዛሬ በአፋር ክልል መዲና ሠመራ የአፋር እና ሶማሌ ወንድማማች ሕዝቦች የኢፍጧር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች፣ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ  ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር።

የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ሀጂ አወል አርባ " እኛና ሶማሌዎች ከሚያለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ  የሚያደርጉን ነገሮች በትልቁ ይበዛሉ " ሲሉ ገልፀዋል።

ስነ ስርዓቱ የሁለቱን ክልል ወንድማማቾች የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እና የፍቅር ተምሳሌት ለማድረግ መካሄዱን ጠቁመዋል።

" ትላንት በሠው ሠራሽ ችግሮች የተፈጠሩትን ግጭቶችን ዛሬ የማስቆም ታሪካዊ ሀላፊነት የኛ ነው " ያሉ ሲሆን "  በኛ ትውልድ ከዚህ ቀደም ያለውን ጥላቻና መራራቅን የምንቀይርበትና የምናሻሽልበት ዘመን ነው " ብለዋል።

" ክፋትን ወደ ፍቅር እንቀይራለን ለዚህ ማሳያው ደግሞ የጅጅጋው እና የዛሬው የኢፍጣር ፕሮግራም ማሳያ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ፤ " ሁለታችንም ክልሎች በቀድሞው ስርዓት የተገፋን እና ከልማት የተገለልን ነበርን " ሲሉ ተደምጠዋል።

" በለውጡ ዘመን ያገኘነውን መሻሻል ተጠቅመን ከግጭት እና ከጥላቻ ወጥተን በአብሮነት ወደ ልማት እና ወደ ብልፅግና ተያይዘን እና ተደጋግፈን ያለንን የሠው ሀይል በጋራ በማድረግ ክልላችንን ማልማት አለብን " ሲሉ መግለጻቸውን የአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

#AfarMassMediaAgency

@tikvahethiopia
759🕊111😡45🙏40👏18🤔17😭12😢9🥰5😱2