TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa #ማሳሰቢያ ‌‎የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላለፈ። ‎ ‎ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ቅዳሜ ይከበራል። በዓሉን አስታኮ ግን አንዳንድ አገልግሎት ሰጪዎች ከፍ ያለ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ እንደሆነ በግልጽ ታይተዋል። ‎ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያም  " ጥቂት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዓሉን አስታከው በአንዳንድ…
#ሐምሌ19 #ቅዱስ_ገብርኤል

የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግስ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ጀምሮ በከተማይቱ የተወሰኑ መንገዶች ይዘጋሉ።

ሞተር ሳይክሎችና ባጃጆች ከዛሬ ጀምሮ በዓሉ ተከብሮ እስኪያልፍ ከምሽት 3 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይፈቀድላቸውም።

በየዓመቱ ሐምሌ 19 በሀዋሳ በታላቅ ድምቀት ለሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ እጅግ በርካታ ምዕመናን ወደ ከተማው ገብተዋል። በነገው እለት እንዲሁም በዕለቱም በርካቶች ወደ ከተማዋ ይገባሉ።

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በተለይም በዓሉ ከትራፊክ አደጋ ነጻ ሆኖ እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን ጠቁሟል።

ከሐምሌ 18/2017 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶችንም እንዳሉ አመልክቷል።

ለተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ ዝግ የሚሆኑት መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?

- ከቅዱስ ገብርኤል /ሱሙዳ/ እስከ  ሎጊታ 
- ከቅዱስ ገብርኤል /ሱሙዳ/ እስከ  ዳሽን ባንክ ፒያሳ
- ከቅዱስ ገብርኤል /ሱሙዳ/ እስከ  ማርሲል ቸርች
- ከቅዱስ ገብርኤል /ሱሙዳ/ እስከ  ሳዉዝስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል
- ከታቦር መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ ኢንጆሪ ላውንጅ
- ከታቦር ትራፊክ መብራት እስከ ኬራውድ ኢንተርናሽናል ሆቴል
- ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፊት ለፊት እስከ ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ ያሉ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች እንደሁልጊዜው ሁሉ በሀዋሳ ከተማ በሁሉም ክ/ከተሞች ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም አመልክቷል።

ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ በዓሉ ተከብሮ እስኪያለፍ  ማንኛዉም ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎችና ባጃጆች ከምሽቱ  3 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይፈቀድላቸው የክልሉ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

እንግዶች ለክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መረጃና ጥቆማ ማድረስ ሲፈልጉ  8295 ነፃ የስልክ መስመር አልያም ለከተማ ፖሊስ 7614 መደወል ይችላሉ ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
2.65K🙏229😡77🕊71👏63🥰27🤔18💔17😭8😱4