TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነዳጅ #Update

ወደ ትግራይ ክልል #ነዳጅ መግባት መጀመሩን የክልሉ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ፤ ወደ መቐለ 10 ቦቴ ነዳጅ መግባቱን ያመለከተ ሲሆን ወደ ኩዊኃ እና ዓጉላም ነዳጅ መግባት መጀመሩን ጠቁሟል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር ጥሩ ትብብር እየተደረገ ነው ያለው ቢሮ " እናተ ጋር ካለው ችግር አንፃር ቅድሚያ እንሰጣለን " ተብለናል ሲል ገልጿል።

ጦርነት ለመፈጠሩ በፊት በወር 12 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ይገባ እንደነበር የገለፀው ቢሮው አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ ከሚፈለገው አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው ብሏል።

መቐለ ውስጥ ካሉት 15 ማደያዎች ነዳጅ የገባው በ4ቱ ላይ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ነዳጅ ለማግኘት እነማን ቅድሚያ አላቸው ?

አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ በተወሰነ መልኩ ስለሆነ ፦

- አምቡላንስ
- እሳት አደጋ
- ውሃ አቅራቢ ቦቴዎች
- የመንግስት ተሽከርካሪዎች
- የእርዳታ አከፋፋይ አካላት
- ባንክ፣ ቴሌ፣ መብራት ኃይል
- በትራንስፖርት ቢሮ ታሪፍ የወጣላቸው ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ቅድሚያ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።

የፋይናንስ እጥረት በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን ያሳወቀው ቢሮው ችግሩን ለማፍታት ከባንክ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ቤንዚን እና ናፍጣ ስንት እየተሸጠ ነው ?

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከፌዴራል መንግስት ለክልሉ እንደተላከ ለመረዳት ተችሏል።

በመቐለ #ቤንዚን በሊትር 60 ብር ከ57 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን #ናፍጣ 66 ብር ከ58 ሳንቲም እየተሸጠ መሆኑን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit : Tigrai Television

@tikvahethiopia
👍1.04K🕊164👎7256🙏22🥰18🤔18😢16😱2