TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" በትግራይ ክልል ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ ነው " - የሰላም እና የስምምነት ኮሚቴ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም እና ስምምነት ኮሚቴ ፤ በትግራይ ክልል ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ ዛሬ አሳውቋል።
ኮሚቴው ፤ " በክልል ትግራይ የሚገኙ ብፁዓን አባቶቻችን ለሃይማኖታቸው አንድነትና መስፋፋት እንዲሁም ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት መሠረት በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናቸው አንድነትና ሉዓላዊነት በጽናት በመቆም ተፈጠሩ የሚባሉ ችግሮችን ሁሉ በዝርዝር ለማቅረብ ለውይይት ዝግጁ እንድትሆኑ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
የሚያቀርቧቸውን የውይይት ነጥቦችን መሠረት በማድረግ ችግሮቹን በስምምነት ለመፍታት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናን ዝግጁ መሆኗን ኮሚቴው #አረጋግጧል።
በዚህም የውይይትና የሰላም መልእክት ቤተ ክርስቲያኗ ያስተላለፈችውን ጥሪ በመቀበል በትግራይ ያሉ ብፁአን አባቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውይይትና ለስምምነት ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ የቀረበ ሲሆን #በቅርብ ቀናት ውስጥ የሰላም ልዑክ ለውይይት ወደ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ እንደሚጓዝ ኣሳውቋል።
በዚህም በጋራ በሚደረገው ቦታና ጊዜ የውይይትና የስምምነት ጉባኤ የሚደረግ ይሆናል ብሏል።
የፌዴራል መንግሥትና የክልል ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርም ችግሩ በሰላማዊ መንገድና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ በመደገፍና ለውይይቱ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር አስፈላጊውን ትብብር ጥሪ ቀርቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

👍1.55K👎326❤162🕊129🙏37😢16😱14🥰5