TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት ዛሬ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው ፦
👉 የአማራ ክልል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን
👉 የአፋር ክልል የትራንስፖርት እና መንገድ ቢቶ
👉 የፌዴራል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

የአማራ ክልል የትራንፖርት እና የሎጀስቲክስ ባለስልጣን ምን አለ ?

- በአማራ ክልል አቅጣጫ ዛሬ 4ኛ ቀኑን የያዘ የሕዝብ ትራንስፓርት የሙከራ ጉዞ  ወደ አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ሶስት (3) የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአማራ ክልል በኩል ጉዞ አድርገዋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ ጉዞ ጀምሯል።

- የአማራ ክልል መንግሥት ለማንኛውም የትራንፓርት እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርጋል።

- የክልሉ ሕዝብ ለሰላማዊ እንቅስቃሴ በጎ አመለካከት ያለው በመኾኑ ጉዞው ላይ ችግር አያጋጥምም።

የአፋር ክልል የትራንፖርት እና መንገድ ቢሮ ምን አለ ?

- በአፋር ክልል በኩል በመጀመሪያው ቀን ብቻ ሁለት የሙከራ ጉዞዎች የተደረጉ ሲሆን ትራንስፖርት ከተጀመረ ዛሬ 6 ቀናት ተቆጥረዋል።

-  ክልሉ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲኾን ያግዛል።  መንግሥት ብቻ ሳይኾን ሕዝቡም ሰላማዊ አንቅስቃሴውን ይደግፋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ የየብስ ትራንፖርት ጀምሯል።

የትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- ተቋርጦ የነበረው የየብስ ትራንፖርትን ለማስጀመር ሁለት የጥናት ቡድን በአማራ ክልል በኩል እና በአፋር ክልል በኩል በመላክ ጥናት ተደርጓል።

- በሁለቱም ክልሎች በኩል 19 የሙከራ ጉዞዎች ከአዲሰ አበባ ትግራይ ክልል እና ከትግራይ ክልል አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ከዛሬ ጀምሮ  ይፋዊ የየብስ ትራንስፖርት ተጀምሯል።

የትግራይ ክልል የትራንፖርት ቢሮ ኀላፊዎች በአየር ትራንፖርት #መዘግየት ምክንያት በአዲስ አበባ በተሰጠው የጋራ መግለጫ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

#አሚኮ

@tikvahethiopia
👍69577👎74🕊38🥰5😱1😢1🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . . ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ? ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት…
ስለ ሕገ መንግሥት ማሻሻል . . .

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ምን አሉ ?

" ሕገ መንግሥቱ #ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ክርክር እየተነሳ ይገኛል።

በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ መፈናቀሎች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች ሕገ መንግሥቱ  መሰረታዊ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡

በሌላ በኩል የማንነት መሰረት ነው የሚሉም አሉ፡፡  በዚህ ምክንያት ጥናት መሥራት አስፈልጓል።

ሕገ መንግሥቱ የሊህቃኑ ብቻ ሳይኾን የሕዝብም በመኾኑ ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ መጓዝ ይገባል። "

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን ምን አሉ ?

" ሁሉም የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች በተለያየ መንገድ የሚሻሻሉበት ሁኔታ አለ።

በመደበኛም ይሁን በኢመደበኛ መንገድ ሕገ መንግሥቱ ይሻሻላል።

391 አንቀጽን የያዘው የሕንድ ሕገ መንግሥት 105 ጊዜ ተሻሽሏል። በመሆኑም ሕገ መንግሥቱ ሙሉ ሊሆን አይችልም።

ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾቹ  በአዋጅ እና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል።

የፌዴሬሽን ምክርቤት ለእነዚህ ሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ዕውቅና ያልነፈገ በመሆኑ እንዲሻሻል እንደፈቀደ ይቆጠራል።

ለምሳሌ ፤ የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ተሻሽሏል። በተመሳሳይ የፌዴራል እና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት ማሥተዳደርን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች ተሻሽለዋል

ሕገ መንግሥትን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 3 ምልከታዎች አሉ።

አንደኛው ሕገ መንግሥቱ ረብ የለውም የሚል ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ በፍፁም መነካት የለበትም የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚል ይገኝበታል።

ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚለው ነው።

ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ ነው። ሕገ መንግሥቱ የማይሻሻል ከሆነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሕገ መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ ይችላሉ።

በሀገሪቱ ያሉ የግጭት እና የአለመግባባት ጉዳዮችን በቀላሉ ለመፍታትም እንዲያስችል ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ ቢሻሻል መልካም ነው። "

#አሚኮ

@tikvahethiopia
👍1.35K👎219135🙏32🕊24😢17🥰14😱8
#አብና🕯

" የ4ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል ፤ የ6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም ! "

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 10 ሰዎች ሞተዋል።

የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ምን አሉ ?

" የ4 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ፤ የቀሪ 6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም።

በጉዳቱ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል።

በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቀበሌው ማዕከል ወደሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት በጊዜያዊ እንዲጠለሉ ተደርጓል።

በቀጣይም የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ የኖላ፣ ላጌ፣ ውፋ፣ ኩዳድ እና ጅብ ዋሻ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። " #አሚኮ

@tikvahethiopia
😭2K160😢84🕊67🙏46😱42😡25🥰24👏22🤔14