TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Seaport ሶማሊያ በኢትዮጵያ ያሉትን አምባሳደሯን ጠራች። ሶማሊያ እንደ ራሷ ግዛት በምታያት ሱማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል ትላንት በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ እንዳስቆጣት መነገሩ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ከኢትዮጵያ አምባሳደሯን ለምክክር በሚል ጠርታለች። የሀገሪቱ ካቢኔ ዛሬ ማክሰኞ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ፦ - የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት) - አፍሪካ ህብረት …
#Update

ሶማሊያ በኢትዮጵያ ያሉትን አምባሳደሯን መጥራቷን ተከትሎ አምባሳደር አብዱላሂ ዋርፋ ወደ #ሞቃዲሾ ማቅናታቸው ተሰምቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ የሶማሊያ ሁለቱ የፌደራል ፓርላማ ምክር ቤቶች በአሁን ሰዓት አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ላይ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።

ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ የወደብ እና የባህር በር ተጠቃሚ ለመሆን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰላማዊ የሆነና በሰጥቶ መቀበል መርህ የተቃኘ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሙከራ ስታደርግ ቆይታለች።

በዚህ ሙከራም ከሶማሊላንድ ጋር በሊዝ የባህር በር ለማግኘት መንገድ የሚጠርግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርማለች።

ስምምነቱ ግን በሶማሊያ መንግስት ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። ሶማሊያ ራስ ገዟን ሶማሊላንድ እንደ ራሷ አንድ ግዛት ነው የምታያት በመሆኑም መሰል የወደብም ሆነ ማንኛውም ስምምነት በክልል አስተዳደር በኩል ሊፈፀም አይችልም ፤ ይህ ልዓላዊነቴን የሚጥስ ነው እያለች ነው።

@tikvahethiopia
👏517106😡87😱41😭29🕊21😢12🙏9🥰5
#CPPI #WorldBank

የዓለም ባንክ ከኤስ ኤንድ ፒ ግሎባል ማርኬት ኢንተለጀንስ ጋር የሚያዘጋጀው የኮንቴይነር ወደብ የአፈጻጸም መለኪያ (Container Port Performance Index - CPPI) የ2023 ደረጃ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል።

ይህ መለኪያ ወደቦች የመረከብ አቀባበላቸውንና እንዴት እንደሚያስተናግዱ በአጠቃላይ ያላቸውን የስራ ቅልጥፍና እና አፈጻጸም የሚለካ ነው።

በዚህም ከ409 ወደቦች የራስ ገዟ #ሶማሌላንድ " #በርበራ " ወደብ 106ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሶማሊያ ፤ " #ሞቃዲሾ " ወደብ ደግሞ 166ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የ " #ጅቡቲ " ወደብ ከመጨረሻ ተርታ 379ኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጠው።

በዚህ የዓለም ባንክ የአፈጻጸም መለኪያ የበርበራ ወደብ ከሞቃዲሾ እና ጅቡቲ ወደቦች የተሻለ ደረጃ ተሰጥቶታል።

በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰጣቸው ከ405 ወደቦች በመጨረሻ ተርታ ማለትም 379 ላይ የተቀመጠው የጅቡቲ ወደብ በሀገሪቱ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።

የጅቡቲ ወደብ በ2022 ከዓለም የተሰጠው ደረጃ 26ኛ ሲሆን በ2023 መለኪያ 379ኛ ላይ መቀመጡ ጅቡቲን አላስደሰተም።

ሀገሪቱ " የ2023 ደረጃ አሰጣጥ ምክንያታዊነት የጎደለው በመሆኑ ያሳስበናል " ያለች ሲሆን " ምን አይነት ሳይንስ ነው የሚያብራራው በዓለም ደረጃ ከ350 በላይ ነጥብ መጣል ? " ስትል ጠይቃለች።

በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲህ ያለው ደረጃ መሰጠቱ በመለኪያው ላይ የተዓማኒነት ጥያቄ እንደሚያስነሳ ገልጻለች።

ጅቡቲ ፥ " ደረጃ አሰጣጡ ነጻ እና ከተእጽኖ የጸዳ ነው ወይ ? " ስትል ጠይቃ " ለማንኛውም አድሏዊም ሆነ አልሆነ ጅቡቲ ከሰሃራ በታች እና ምስራቅ አፍሪካ ትልቁ እና ቀልጣፋ ማዕከል ናት " ብላለች።

ሙሉ ዶክመንቱን በዚህ ያግኙ ➡️ CPPI 2023

#WorldBank

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
292👏49😱33🤔32😡28🕊23😭22🙏17🥰16😢16