TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ቶቶት የተሰኘ የወጣቶች ማህበር መስቃንና ማረቆ አካባቢ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ 400 ተማሪዎች የሚሆን የመማሪያ ቁሳቁስ ቡታጅራ ሴራና አዳራስ ድረስ በመገኘት አበርክቷል። ጳጉሜ 3/2011 ዓም።እንዲሁም ወልቂጤ ከሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ 50 ተማሪዎች የሚሆን የመማሪያ ቁሳቁስ አበርክቷል። መስራቹቹ የጉራጌ ተወላጆች በአዲስ አበባ ናቸው። የተሰበሰበውም አዲስ አበባ ከሚገኙ ባለሀብቶና በጎ አድራጊዎች ነው።" ሜራ/TIKVAH-ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከ190 ሺህ በላይ ዶላር ፣ 2,100 ዩሮና ከ729 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር "የውጪ ሃገራት ገንዘቦችን ይመነዝራሉ በተባሉ ግለሰቦች ላይ በተደረገ ክትትል" በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ ቀይ መስቀል አካባቢ ከነተጠርጣሪዎቹ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

Via #ESHETEBEKELE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ ና አክባሪ መሆኑን አይተናል"—የኮቲዲቫር ንጉስ
.
.
“የኢትዮጵ ህዝብ ሰው አክባሪ፣ እንግዳ ተቀባይ እና አኩሪ ባህል ያለው መሆኑን አይተናል“ ሲሉ የኮቲዲቫር ንጉስ ተናገሩ። ንጉሱ ከነቤተሰባቸው ጋር በመሆን ለኃይማኖታዊ ስነስርዓት ዛሬ አክሱም ከተማ ገብተዋል።

ንጉሱ ቺፌዝ ጆን ጋርቭየስ አክሱም ሲደርሱ በኃይማኖት መሪዎችና በአካባቢው ማህበረሰብ በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል መደሰታቸውን ገልጸዋል። “የኢትዮጵያ ስልጣኔ በአክሱም እንደተጀመረና ብዙ ነግስታት ንግሳቸውን  እዚህ እንደሚቀበሉ በታሪክ አውቃለሁ“ ብለዋል።

የኮንጎ፣ ቱኒዝያ፣ ናይጀሪያ፣ ኡጋንዳና ግብጽ ነገስታት ጨምሮ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎች አብሮዋቸው እንደመጡ ያመለከቱት ንጉሱ የመጡበት ፕሮግራምም አህጉራዊ ትስስር ለማጠናከር እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ የተባረከች ሀገር ናት፣በኢትዮጵያ መገኘታችን ትልቅ ጸጋ ነው“ ያሉት ንጉሱ ከዚህ በኋላ አክሱምን እንደራሳቸው አካባቢ እንደሚያዩት ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-10

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሆሳዕና⬆️"በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ለ2000 አቅመ ደካማ ህፃናት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ። ድጋፉን የዞኑ አስተዳደር አስተባብሯል።" የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ታረቀኝ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🥰1
የማዕከላዊ እስር ቤት የመጨረሻዎቹ ፎቶዎች⬆️

ከሰሞኑን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ማዕከላዊ እስር ቤትን በመጎብኘት ላይ እንደነበሩና ፎቶዎችንም ሲያጋሩን እንደነበረ ይታወሳል። የመጨረሻውን የፎቶ ስብስብ ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲያልፍ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጀት ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለይ በሐይማኖታዊ ቦታዎች፣ ባዛር በሚደረጉባቸው አካባቢዎች፣ በገበያ ስፍራዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ኮሚሽኑ ከሚመለከታው አካላትጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

ወንጀልን መከላከል የሚቻለው ሁሉም የህሕረተሰብ ክፍል ባለበት አካባቢ ከህግ አስከባሪዎች ጋር ሲተባበር መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ህብረተሰቡ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ እንደነበረው ከፖሊስ ጎን በመሆን ራሱም ሆነ አከባቢውን ከወንጀል መጠበቅ ይኖርበታል ብለዋል። ህብረተሰቡ ችግር ሲገጥመውም ሆነ ማንኛውንም እንግዳ ነገር ሲመለከት በ991 ነፃ የጥሪ መዕከል ማሳወቅ እንደሚቻል ኃላፊው ጠቁመዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የወላይታ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት ለ2012 በጀት ዓመት ከ 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ፡፡ ምክር ቤቱ የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረፅዮን!

የተጠናቀቀው ዓመት 2011 ዓ.ም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከርን ጨምሮ የተለያዩ ክስተቶች የተስተናገዱበት ነበረ ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ የአዲስ አመት መልካም ምኞታቸውን ዛሬ ባስተላለፉበት ወቅት እንዳትስታወቁት በተጠናቀቀው አመት በሃገሪቱ በርካታ በጎና በጎ ያልሆኑ ክስተቶች ተስተናግደዋል። ለሀያ አመታት ተራርቀው በነበሩ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች መካከል ታሪካዊ ምእራፍ የተሰራበት አመት ሆኖ መጠናቀቁን ዶክተር ደብረጽዮን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-10-2
አዲሱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በከተማዋ ቀጣይ የትኩረት አቅጫዎች ዙሪያ ለጋዜጠኞች የሰጡት መግለጫ👇
https://telegra.ph/ETH-09-10-3
ለሚመለከተው⬆️

"ይሄን ፎቶ ያነሳሁት ከ3 ቀን በፊት ነው የዛን እለት ሰው በሚሄድበት ወቅት እንጨቱ ከፋቁ ላይ ወደቀ እደእድል ሁኖ ማንም አልተጎዳም። ይሄ እስከዛሬ ይወድቃል እና ምንም መፍትሄ አልተሰጠውም። ቦታው 22 ሆሊውድ ሆቴል አከባቢ ነው።" ናቲ/TIKVAH-ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የEBC የሳተላይት ስርጭት መቋረጡን ለማወቅ ተችሏል። ድርጅቱ በምን ምክንያት ስርጭቱ እንደተቋረጠ ባይገልፅም ችግር እንደገጠመውና ለማስተካከል እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፤ ተመልካቾቹንም ይቅርታ ጥይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia