TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቅጣት! በሰባት ዓመት ሕጻን ላይ ግብረ ሰዶም የፈጸመው በ18 ዓመት እሥራት ተቀጣ።

በአዲስአበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 ክልል ልዩ ቦታው ታቦት ማደሪያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሐምሌ 25 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ሲሆን የወንጀል ህግ አንቀጽ 631/ለ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የግብረ ሰዶም ጥቃት በማድረሱ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የጉለሌ ምድብ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶበታል፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ገረመው ቦጋለ ከእርሱ ጋር አንድ አይነት ፆታ ባለውና ለአካለ መጠን ባልደረሰው ልጁ ላይ የግብረ ሰዶም ጥቃት ለመፈፀም በማሰብ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 ክልል ልዩ ቦታው ታቦት ማደሪያ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ እድሜው 7 ዓመት የሆነውን የግል ተበዳይ ህፃን ላይ የግብረ ሰዶም ጥቃት ማድረስ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከዐቃቤ ህግ ጋር በመተባባር ባጣሩት ምርመራ መሰረት የግል ተበዳይ ላይ ወንጀሉ የተፈፀመ መሆኑን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

ተከሳሽ ማንነቱ በችሎት ተረጋግጦ ክሱ ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን አልፈፀምኩም፣ ጥፈተኛም አይደለሁም በማለት ክዶ ተከራክሯል፡፡ አቃቤ ህግም
ባቀረበው ክስ መሰረት ምስክሮችን አቅረቦ በመሰማቱ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ተከሳሹን በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ብሎታል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 7ኛ ምድብ ወንጀል ችሎት አቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ እና የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበል ጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያርማል ሌሎችን ያስጠነቅቃል በማለት በአስራ ስምንት አመት ፅኑ እስራት
እንዲቀጣ እና ከማንኛውም ህዝባዊ መብቱም ለ5 ዓመት እንዲታገድ መወሰኑን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የላከልን ዜና ያስረዳል።

ምንጭ፦ ድሬትዮብ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ እንዴት ዋለች ?? ዩኒቨርሲሪዎቿ እንዴት ዋሉ ?? ከዚህ በታች በሚገኙ የኒቨርሲቲዎች የምትማሩ ውድ ኢትዮጵያዊያን የግቢያችሁን ውሎ አካፍሉን...

ደብረታቦር
መቀሌ
አዲግራት
አምቦ
አክሱም
ደብረማቆስ
ሀረማያ
ባህርዳር
ወልዲያ
መቱ
ወለጋ
ጎንደር

እንዲሁን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የምትገኙ የቲክቫህ ተከታዮች ቀኑ እንዴት ነበር የሚለውን ላኩልኝ።

መረጃዎቹ...
1. ከግል እይታ አንፃር ሳይሆን አብዛኛውን የሚወክል
2. ግነት የሌለበት
3. በአካል ያያችሁትን
4. አሉባታ እንዳትልኩ
5. ከፌስቡክ ላይ የተገኘ ማረጃ እንዳትልኩ
5. በፍፁም ብሄርተኝነት እና ዘረኝነት እንዳይንፀባረቅበት
6. ብሄር እና ዘርን ወክሎ መረጃ ማድረስ አይቻልም

ሁላችንም የአንድ እናት ልጆች ነን!

በተለይ ታማኝ አባላቶቻችን መረጃዎችን እድታደርሱ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

@tsegabwolde
ይቅርታ! ኔትዎርክ በበርካታ ከተሞች እየተቆራረጠ ይገኛል። እኔ ባለሁበት ከተማ የዳታ አገልግሎት ተቋርጣል በዚህም ምክንያት ልዘገይ ችያለሁ። ከዚህ በኃላ ወደየ ግቢው እየዞርን ውሎ እንዳስሳለን...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀሌ! አሪድ ካምፓስ ! ዛሬ ውሎው ሰላማዊ ነበር። ምንም እንኳን ተማሪዎች ስጋት ላይ ቢሆኑም በግቢው ውስጥ ሰላምን የሚያደፈርስ እንቅስቃሴ አልነበረም። በግቢው ረብሻም ይሁን ሁካታ አልነበረም። ጥዋት ተማሪዎች ወደ ክፍል እንዲገቡ መልዕክት ሲተላለፍ ነበር ተማሪዎች ግን ዛሬ ወደ ክፍል አልገቡም። ግቢው ተማሪዎች እንዳይወጡ በሩን እደዘጋው ነው አሁንም። ሰላምን የሚያስከብሩ የፀጥታ ሀይላት በግቢው ውስጥ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች ጉዳት እንዳይደርስቸው ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ።

አዲሀቂ..

በዚህም ግቢ ሰላማዊ ውሎ ነበር። ለሰዓታት ተማሪዎች ከግቢ እዳይወጡ በር ተዛግቶ የነበር ቢሆንም የኃላ ኃላ በሩ ተከፍቶ ተማሪዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል። ምሽቱን ደግሞ ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት መሪዎች ወደ ግቢው በመዝለቅ ተማሪዎች እንዲረጋጉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ለከፍተኛ ጥበቃ ካለባቸው ግቢዎች አንዱ ይህው ግቢ ነው።

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለሊቱም ሰላማዊ ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ገልፀዋል።

ምንጭ፦ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች(አሪድ እና አዲሀቂ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወለጋ! የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ተማሪዎች ወደ ግቢ እየተመለሱም እንደሆነ ተስምቷል። ነገር ግን በሻምቡ የተፈጠረው ክስተት የተመላሽ ተማሪ ቁጥሩን ቀንሶታል።

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ መንግስት የተማሪዎች ደህንነት ለማስጠበቅ በቂ ፖሊስ መድቧል። በወለጋ ይህ ነው የሚባል ችግር የለም። የተማሪዎች ስጋት ግን እንዳለ ነው።

ምንጭ፦ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረታቦር! የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ሰላም ውሏል። አሁንም ትምህርት ሙሉ በሙሉ እንደ ተቋረጠ ነው።

በርካታ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ ነው። በግቢው ውስጥ አንድ ኢትዮጵያዊ ህይወቱ እንዳለፈ አስክሬኑም ሲወጣ በአይናቸው ያዩ ተማሪዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ዩኒቨርሲቲው ስለትምህርት ጉዳይ ምንም አይነት መግለጫም ሆነ ማስታወቂያ አላወጣም።

ለዩኒቨርሲቲው የመከላከያ ሀይሎች ከፍተኛ ጥበቃ እደረጉ ነው። ረብሻም ሆነ ሁከት ዛሬ አልነበረም።

የደብረታቦር ከተማም ፍፁም ሰላም የሰፈነባት ናት።

ምንጭ፦ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ! ቅዳሜ እንደመደበኛ የትምህርት ቀን የተካተተበት አዲስ ፕሮግራም ውጥቷል። ተማሪዎች በወጣው ፕሮግራም መሰረትም ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል። አዲስ ፕሮግራም የወጣው የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተራዘመ! አንጋፋው ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ በሀገር ውስጥ ሊሰራ ያሰበውን ኮንሰርት ላልተወሰን ጊዜ አራዘሟል።

ምንጭ፦ ድሬትዩብ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረማርቆስ፣ መቱ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ወልዲያ፣ አምቦ፣ ጎንደር በዛሬው ዕለት በእዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ይህን ያህል የጎላ ችግር አልተፈጠረም። አንዳንዶቹ ወደ መደበኛው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ገብተዋል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ለሰዓታትም ቢሆን የተማሪዎች ተቃውሞ ነበር። ልክ እንደ አምቦ በአርሲ ዩኒቨርሲቲም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ነበር።
በባህርዳር ዩኒቨርሲታ ደግሞ ዛሬ ጥዋት ተማሪዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር። ከሰዓት በኃላ ግን የፖሊ ግቢ ፍፁም ሰላማዊ እና ብዙም እንቅስቃሴ የማይታይበት ነበር። በፔዳ ግቢ ይህን ያህል የጎላ ችግር ባይኖርም አልፎ አልፎ የተማሪዎች ጩኸት ይሰማል።

በአጠቃላይ በዛሬው የዩኒቨርሲቲዎች ውሎ ይህን ያህል የጎላ ችግር አልነበረም። በአንፃሩ ሰላም ወርዷል በየግቢው። ይህም ቢሆን ተማሪዎች ከፍተኛ ጭንቀት እና ስጋት ውስጥ እንደሆኑ ይናገራሉ።

አለመረጋጋት ተፈጥሮባቸው ከነበሩት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች እየወጡ ነው። አብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ አድርገዋል።

ተማሪዎች የሚማሩበት ግቢ እንዲለቃቸው እና ወደቤተሰቦቸው እንዲልካቸው በተደጋጋሚ እያጠየቁ ነው።

አለመረጋጋት በታየባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ የሆነ የፖሊስ ጥበቃ እየተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ዛሬ ምሽት ከፋና ጋር ባደረጉት ቆይታ ተማሪዎች ከ2 ሰዓት በኃላ እንዳያመሹ አሳስበዋል። ለጥቂት ቀናት ከተቻላቸው በጊዜ ወደ ዶርማቸው እንዲገቡም መክረዋል። የተማሪ ወላጆችም ልጆቻቸውን እንዲያረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል። መንግስት ለተማሪዎች ደህንነት አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀው ዩኒቨርሲቲዎችም ለተረከቧቸውን ተማሪዎች አስፈላጊውን ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ታህሳስ 4
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ የሚታየው ግጭት አሳስቦኛል አለ። በጨለንቆና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተከሰቱ ግጭቶች የተሳተፉትን መንግሥት ተጠያቂ እንዲያደርግና የዜጎቹን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ኤምባሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
❗️ይህ ቻናል በማንኛውም ሰዓት መረጃ ማድረስ ሊያቆም ይችላል ❗️

በሀገሪቱ በርካታ ቦታዎች የማህበራዊ ሚደያዎችን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት እየተዘጋ ነው። የቻናሉ ተመልካች ቁጥርም እጅግ በጣም አሽቆልቁሏል። ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ መረጃዎችም ተቋርጠዋል።

የዚህ ቻናል መረጃዎችን እያገኙ ያሉት ጥቂት የሀገር ውስጥ አባላት ሲሆኑ የተቀረው ግን በውጭ ሀገር የሚገኙ ተከታዮች ናቸው።

እኔ ባለሁበት ቦታ በየትኛውም ሰዓት ኔትዎርክ ሊቋረጥ ይችላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሳር ቅጠሉ ውሀው ኢትዮጵያን ሲመስል
ዘር እንቆጥራለን ገበሬ ይመስል
ገበሬ ዘር ቢመርጥ የእውቀት ስራ ነው
የኛ ዘር መምረጥ ግን የድንቁርና ነው
ከዚህ ድርንቁርና አምላክ ይርዳንና
በፍቅር እንመን ፍቅር ይበልጣልና።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
አዳማ ASTU! ትላንት ምሽት የአ.ሳ.ቴ.ዩ ተማሪዎች በጨለንቆ በተፈጠረው ግጭት ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች የመታሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅተው ነበር። ተማሪዎች በኢትዮጵያዊያኑ ሞት የተሰማቸን ጥልቅ ሀዘንም ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረማርቆስ! በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተርማር ስራው መሉ በሙሉ ተቋርጧል። ተማሪዎች ተማሪዎች ካፌ መመገብ እንዳቆሙም ተሰምቷል። በግቢው በተፈጠረው አለመረጋጋት የአንደኛ አመት ተማሪዎች የሚኖሩበት ህንፃ ላይ የሚገኙ ዶርሞች ውድመት ደርሶባቸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተላኩት መልዕክቶች እንደሚያስረዱት ባርካታ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደዋል።

ምንጭ፦ ንጉሴ ምትኩ(የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት) , አዲስ ስታንዳርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተራዘመ! የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድሬዳዋ ከተማ ታህሳስ 8/2010 ዓ. ም. ሊያካሂድ የነበረውን የ19ኛውን የሜ/ጄኔራል ኃይሎም አርአያ መታሰቢያ 15
ኪ.ሜ የጎዳና ሩጫ ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን አስታውቋል።

ምንጭ፦ ሥለሺ ብስራት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ጨለንቆ! የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ በጨለንቆ የተፈፀመውን ድርጊት አውግዘዋል። በሁኔታው ማዘናቸውን የገለፁት አቶ ለማ “ግድያውን የፈፀሙ ሰዎችን ለህግ እናቀርባለን” ሲሉም ተደምጠዋል።

ጨለንቆ ከተማ በነበረው ግጭት ከ16 በላይ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸው እንዳለፈ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ምንጭ፦OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀሌ! በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ትላንት ከተማሪዎች ጋር ተነጋግረዋል። ተማሪዎቹም ተረጋጋተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል። ግቢው ሰላማዊ ነው። የተማሪዎችን ደህንነት የሚያስጠብቀው ሰራዊትም ከግቢ አልወጣም።

ምንጭ፦አ(ከቢዝነስ ኮሌጅ)
@tsegabwolde
ተቋርጧል! በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። የኢትዮ-ቴሌኮም ደንበኞች ሶሻል ሚዲያን መጠቀም አልቻሉም። እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኙ ደንበኞች 2ጂና 3ጂ የዳታ ኢንተርኔትና ሶሻል ሚዲያ መጠቀም አልቻሉም።

ኢትዮ-ቴሌኮም በዚህ ጉዳይ ምንም ያለው ነገር የለም። እስከመቼ እንደሚቆይም አልታወቀም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረታቦር! መማር ብንፈልግም በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ያለው የጸጥታ ሀይል ቁጥር መብዛት ስጋት ፈጥሮብናል አሉ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች።

በዩኒቨርሲቲው በተከሰተው አለመረጋጋት ጉዳት ደርሶበት ህክምና ሲሰጠው የነበረ አንድ ሰው ህይወቱ ማለፉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዓለማየሁ ከበደ ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ላይ ተረጋግቷል፣ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ በቅርብ ቀናት ትምህርት ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አ.ብ.መ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ! በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱ አልተጀመረም፡፡ጸጥተው ካለፉት ቀናት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነው የጸጥተው ሁኔታ ግን ካለፉት ቀናት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነው፡፡ በዩኒቨረሲቲው ላይም መረጋጋት ሰፍኗል፡፡ተማሪዎችም በተፈጠረው ችግር መደናገጣቸውንና አሁን ዛሬ ላይ የተረጋጋ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡ ከተማሪዎች፣ አመራሮች እና ከመምህራን ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethioia