TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቀሌ! ዛሬ ምሽት ከ3 ሰዓት ጀምሮ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ካምፓስ አለመረጋጋቶች ነበሩ። በተለይ በገዳም እና ከንዓን መንደር የተፈጠረው ግጭት ለአንዳንድ ተማሪዎች ጉዳት ምክንያት ሆኗል። በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ፖሊስ ወደ ግቢው በመግባት ሁኔታዎችን ተቆጣጥሯል። ተማሪዎችም በየዶርማቸው ናቸው። ዩኒቨርሲቲው ተረጋግቷል። በተማሪዎች ዘንድ ግን ፍርሀቱ እንዳለ ነው።

ዛሬ ቀኑን ሙሉ በግቢው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ሲካሄድ ነበር።

ምንጭ፦ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነገው ዕለት የሚቀርቡ መረጃዎች...

.ጨለንቆ
.ወልዲያ
.ወለጋ
.ባህርዳር
.ደብረታቦር

@tikvahethiopia
ዘረኛ ከሆንክ የአለማችን እርካሹ ሰው አንተ ነህ።

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ! ሻምቡ ውስጥ ሁለት ከትግራይ ክልል የሄዱ ተማሪዎች ሕይወት አልፏል።

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሻምቡ ግቢ ውስጥ በተማሪዎች መካከል በተነሣ ግጭትና ሁከት ሁለት ከትግራይ ክልል የሄዱ ተማሪዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

የትግራይና የኦሮምያ ክልሎች የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮዎች ኃላፊዎች በየፌስቡክ ገፆቻቸው ላይ ዛሬ ባወጧቸው መልዕክቶች በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሻምቡ ግቢ ውስጥ ሌሊቱን በተፈጠረ ሁከት የግቢው ተማሪዎች የነበሩ ሁለት የትግራይ ተወላጆች ሌሊቱን ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቀዋል።

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ማዕከል የሆነችው ሻምቡ ከተማ አንድ ነዋሪና ሌላ በግቢው የዩኒቨርሲቲው ባልደረባ የሆኑ ባለሙያ ለዝግጅት ክፍላችን ስለ ሁኔታው ሲገልፁ ግጭቱ የተከሰተው አዲግራት ውስጥ
ተገድሏል በተባለ ሌላ ተማሪ አጋጣሚ ምክንያት የተነሣሣ መሆኑን ጠቁመዋል።

ምንም እንኳ ከትምህርት ሥርዓቱ ጋር በተያያዘ ሰሞኑንም ውጥረት የነበረ ቢሆንም እንዲህ አንድ ጎሣ ላይ ነጥሎ ያነጣጠረ ችግር ግን እንዳልነበረ ቪኦኤ ያነጋገራቸው እማኞች ተናግረዋል።

የሻምቡ ግቢ የትምህርት ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ ቱሊ አብዲሣ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ነቀምቴ የሚገኘው ዋና ግቢ ተማሪዎች ባለፈው ሣምንት ትምህርት አቁመው እንደነበረና ቅዳሜ ይመለሳሉ ተብሎ ሲጠበቅ እንዳልተመለሱ፤ የሻምቡ ግቢ ተማሪዎችም ተመሣሣይ ጥያቄ ትናንት (ሰኞ) አንስተው በሰላም መለያየታቸውን ገልፀዋል።

በተማሪዎቹ መካከል ግጭቱ እኩለ ሌሊት ላይ መነሳቱንና ከተንቤን የመጡ ናቸው ከተባሉት ተማሪዎች አንደኛው በድብደባ ሲሞት የሁለተኛው ግን እየተጣራ መሆኑን ዲኑ አመልክተው እርሣቸው በግቢው ውስጥ በኃላፊነት ባገለገሉባቸው ሦስት ዓመታት ውስጥ እንዲህ ጎሣ የለየ ጥቃት ሲፈፀም ሲያዩ የትናንት ሌሊቱ የመጀመሪያቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ VOA አማርኛ(ሰለሞን አባተ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🚫🚫ዘረኝነት ይቁም🚫🚫

ያንዲት እናት ልጆች መሆናችን አውቀን
ጎሳና ኃይማኖት ሳይነጣጥለን
ምን ይሳነን ነበር ብንተባበር
አናሳዝንም ወይ ??

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀሌ! አሪድ ካምፓስ የምትማሩ የሀዳሴ መንደር ብሎክ 6,7 እና 8 ተማሪዎች ችግር ቢፈጠር ከላይ ባሉት ስልኮች ተጠቅችሁ ጥቆማ አድርሱ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህርዳር! ከጥዋቱ 1:30 ይባብ ግቢ የተማሪዎች ካፌ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል። ተማሪዎች የለም ግቢውም ጭር ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀሌ! ሰላማዊ እና የተረጋጋ የመማር ማስተማር ሂደቱ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

ትላንት ምሽት በገቢው ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ጥቂት ተማሪዎች ለሊት ከግቢ ወጥተዋል። በአሁኑ ሰዓት ከግቢው ተማሪዎች መውጣት እንዳይችሉ ተደርጓል። ከትላንቱ ክስተት ጋር በተያያዘም ከነዓን የሚገኙ ተማሪዎች በፖሊስ ተይዘው በአንድ ክፍል ውስጥ አድረዋል። ተማሪዎቹ እስካሁንም እንዳልተለቀቁ ነው የተሰማው።

ፖሊስ ሁኔታዎችን ተቆጣጥሮ በግቢው ሰላም እንዲሰፈን እና ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ነው።

ከ2 ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍላቸው ሲሄዱም ተስተውሏል። አንዳንድ ተማሪዎች ፈርተው ከዶርም እንዳልወጡም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ! ከላፉት 3 ቀናት በተሻለ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየታየ ነው። ይህም ቢሆን ተማሪዎች ወደ ውጪ እንዲወጡ አልተፈቀደላቸውም። ዩኒቨርሲቲው የተፈጠሩ ችግሮችን በንግግር ፈቶ ተማሪዎችን ወደ መደበኛ ትምህርታቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ ነው። በግቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ አካላት በተጨማሪ የሀይማኖት አባቶች አስተዋፆኦ ከፍተኛ እንደሆነ በግቢው ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ተግረዋል።

ምንጭ፦ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ(ሀረር ካምፓስ)! ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ተማሪዎች በየመማሪያ ክፍላቸው እየገቡ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው።

በተመሳሳይ...

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ ቀጥሏል። ከህግ ክፍል የተገኘው ማረጃም እንደሚጦቅመው ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው። ዛሬም ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ግቢ ያልተመለሱ ተማሪዎች ቢኖሩም በመጭዎቹ ቀናት ወደ ትምህርት ተቋማቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

(ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎችን ይመለከታል) ሀረማያ!

ምንጭ፦ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም! ከቀደሙት ቀናት በተሻለ መልኩ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መረጋጋት እና ሰላም ሰፍኖበታል። የዩኒቨርሲቲው በር እንዳልተከፈተም ተማሪዎች ተግረዋል።

በርካታ ተማሪዎች ዛሬም በስጋት ላይ እንዳሉ ቢገልፁም የፀጥታ አካላት ለግቢው ሰላም እና መረጋጋት እያደረጉ ያሉት ነገር ምስጋና የሚቸረው ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለተፈጠረው ችግር ፈጣን እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥም ተማሪዎች ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegavwolde @tikvahethiopia
መቀሌ! ዩኒቨርሲቲው(አሪድ ካምፓስ) ተማሪዎች ወደ ክፍል እንዲገቡ ጥሪ ቢያቀርብም አብዛኛው ተማሪ ወደ ክፍል ሳይገባ ቀርቷል። በአንዳንድ ዲፓርትመብቶች ፈተና ተሰርዟል። ግቢው ሰላማዊ እና የተረጋጋ ቢሆብም ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ ተከልክለዋል።

ምንጭ፦ የመ.ዩ.ተማ.
@tsegabwolde
ችግሮችን ለማባባስ እየራችሁ ላላችሁ ዘረኞች እና ብሄርተኞች! ጠንካራ መልዕክት እንሆ....

❗️ዛሬ እንጂ የዛኔ ምርጫ የላችሁም❗️

☞ እናንተ ግጭትን ለማብረድ ከመሞከር ይልቅ በተነሳው እሳት ላይ ቤንዚን እየጨመራችሁ ያላችሁ ግብዞች ሆይ!!

☞ ይህ እውነት የተፃፈው ለእናንተ ነው፡፡ በዚህ ርኩሰት ተግባር ከቀጠላችሁ

☞ እንዲመጣ እየወተወታችሁት ያላችሁት ክፉ ቀን ቢመጣ እንዲህ እንዳሁኑ ፌስቡክ ላይ ተጥዳችሁ
መዘብዘብ አይታሰብም። ያኔ ምኞታችሁ ዛሬን በህይወት መክረም ብቻ ይሆናል።

☞ ያኔ አይደለም እንደልባችሁ ወጥታችሁ መግባት ይቅርና ሱቅ ደርሶ መመለስ ቅንጦት ሊሆንባችሁ ይችላል፡፡ ምክንያቱም እንዲነድ ያቀጣጠላችሁት እሳት ወላፈን. .. ከቤታችሁ ወጣ እንዳላችሁ ሊበላችሁ ይችላል። ለነገሩ እያቀጣጠላችሁት ያለው እሳት.....ከቤታችሁም ሆናችሁ ከሰል አድርጎ ሊያስቀራችሁ ይችላል።

☞ ያኔ ሀገሪቱ በትናንሽ ባለጠመንጃ መንግስታት የምትመራ ስለምትሆን እንደልብ የምትተቹት መንግስት አይኖራችሁም። ይህ ነገር አሁን አይገባችሁም።


☞ እናንተን ምናልባት የሚገባችሁ

☞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት በመድሃኒትና በምግብ እጦት ሲያልቁ ያዩ እናቶች... ልጆቻቸውን ለማትረፍ ወደ ስደት በሚያደርጉት ጉዞ የአውሬና የሽፍታ ሲሳይ ሆነው ሲቀሩ ያኔ ይገባችኋል።

☞ አስፓልቶች በታንክ ታርሰው..... ከተማይቱ በህንፃ ፍርስራሽ ተሞልታ በዘሩ ምክንያት በየቀኑ በየጎዳናው የሞተው ቀባሪ ያጣ አስከሬን ሽታው አገሩን ሲሞላው ያኔ ይገባችሁ ይሆናል።

☞ እመኑኝ ...... ዛሬ ላይ ለተፋችኋት እያንዳንዷ ብጥብጥ ቀስቃሽ መልእክታችሁ መፈጠራችሁን እስክትረግሙ ዋጋ ትከፍልባታላችሁ። ለኃጥዓን የወረደው ለፃድቃን ይተርፋል እንደሚለው ቅዱስ መፅሃፉ ዳፋችሁ ለሁሉም ሲሆን ያኔ ይገባችሁ ይሆናል ።

☞ ያ እንዲመጣ የምትፈልጉት ቀን ሲመጣ. .. ክልላችሁ አያድናችሁም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የላካቸው ሰላም አስከባሪ ወታደሮችም ከመጣባችሁ መዓት ፈፅሞ ሊያስጥሏችሁ አይችሉም ።

☞ ምናለፋችሁ ዛሬ እንደዋዛ እያቀጣጠላችሁት ያላችሁት እሳት ለጎረቤት ሃገራትም ይተርፋልና ክልሌ መሸሸጊያዬ ብላችሁ እንዳታስቡ።

ዛሬ በሀገር ሰላም በድንገት በህዝቦች መካከል የተፈጠሩ ግጭቶችን ላጋጋላችሁበት አንድ ቀን በቁጭት እና ፀፀት የደም እንባ እያነባችሁ በህይወታችሁ ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ፡፡

☞ አሁን እንጂ የዛኔ ምርጫ የላችሁም፡፡ ስለዚህ ያች እንድትመጣ እየጠራችኋት ያለችው ቀን ሳትመጣ፣ በዚች በመልካሟ በዛሬዋ ቀን ላይ ሳላችሁ ምርጫ አላችሁና አስቡበት።

ልቦና ይስጠን!

ምንጭ፦ ቂርቆስ

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ጠብቅልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህርዳር! በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ካምፓሶች ዛሬ ጥዋት ሰላማዊ ሰልፍ ሲድረግ እንደነበር በድምፅ እና በምስል ተደግፈው የተላኩት መረጃዎች ይጠቀማሉ። በተለይ ይባብ በተባለው ግቢ በርካታ ተማሪዎች በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ አሰምተዋል። አንዳንድ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ ግን የግቢው በር ተዘግቷል። ተማሪዎች በአጥር በኩል ግቢውን ለቀው እየወጡ እንደሆነም ተሰምቷል።

በአሁኑ ሰዓት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ካምፓሶች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ያለ ሲሆን ፖሊስ ለተማሪዎች ጥበቃ እያደረገ ይገኛል።

ምንጭ፦ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስኳር! የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በመተሃራ ተበላሽቷል ተብሎ ስለተቀበረው ስኳር ማስረጃ አላገኘሁም አለ።

ስኳር ኮርፖሬሽን በውጭ ምንዛሬ ገዝቶ ወደ ሐገር ካስገበው 2 መርከብ ስኳር 3 ሺህ 777 ኩንታሉን ተበላሽቷል ብሎ ቀብሮታል ተብሏል፡፡ የዓይን እማኞች ጭምር አሉኝ ቢልም ስለመቅበሩ ግን ማስረጃ አላቀረበም፡፡

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርበው የተጠየቁት የሥራ ሃላፊዎቹ በጊዜው ስኳሩን የቀበርነው ውጭ ሐገር ድረስ ልከን መበላሸቱን እና ለምግብነት እንደማይውል ካረጋገጥን በኋላ ነው ብለዋል፡፡ ስኳሩ ብልሽት ያጋጠመው ከአቅራቢው ሳይሆን ከመርከቡ ነው ያሉት የሥራ ሃላፊዎቹ ካሳ ያልጠየቅንበትም ምክንያት ይሄው ነው ብለዋል፡፡

የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ ግን ተበላሽቷል ተብሎ የተቀበረው ስኳር በመጠን እጅግ ብዙ በመሆኑ ካሳም ስላልተጠየቀበት ማስረጃም ስላላገኘን መላ ሊባል ይገባዋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1 (ትዕግስት ዘሪሁን)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጨለንቆ! ከጨለንቆ ወጣ ብላ በምትገኝ የሶማሌ ክልል አዋሳኝ መንደር ውስጥ አንድ ሰው በልዩ ፖሊስ ተገድሏል መባሉ ከተሰማ በኋላ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በተነሳ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ ተስምቷል።

ምሥራቅ ሐርርጌ ጨለንቆ ውስጥ ከትናንት ወዲያ በተቀሰቀሰ ግጭት የሞቱ ሰዎች የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት መፈፀሙን የከተማዋ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። ትላንት የአስራ አንድ ሰዎች ቀብር በተፈፀመበት ቦታ ላይ መገኘታቸውን ለዶቼቬለ የተናገሩ አንድ የከተማዋ ነዋሪ እንዳሉት ከሟቾቹ መካከል ተማሪዎች ይገኙበታል። እንደ አይን ምስክሩ ሰዎቹ የተገደሉት፣ ከጨለንቆ ወጣ ብላ በምትገኝ የሶማሌ ክልል አዋሳኝ መንደር ውስጥ አንድ ሰው በልዩ ፖሊስ ተገድሏል መባሉ ከተሰማ በኋላ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በተነሳ ግጭት ነው።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በግጭቱ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን እና 14
መቁሰላቸውን በፌስ ቡክ ማሳወቃቸው ተዘግቧል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቬለ(ኂሩት መለሰ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ! ትላንት ምሽት የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጨለንቆ ላይ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያዊያን ወገኖችን ሻማ በማብራት አስበዋል። ተማሪዎቹ በወገኖች ሞትም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀሌ! አሪድ ግቢ ትላንት ምሽት ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በፖሊስ የተያዙት ተማሪዎች 8:15 ላይ ተለቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስብሰባ! የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የክፍል ተወካዮች ዛሬ ከምሳ ሰዓት በፊት በፖሊ ግቢ ከከተማው ከንቲባ ጋር ስብሰባ ነበራቸው። በስብሰባውም የከተማው ከንቲባ በግቢ ውስጥ ያሉት የፀጥታ አስከባሪዎች(ፖሊስ) በቅርቡ እንደሚወጡ ገልፀው የተማሪ ተወካዮችም ተማሪዎችን አረጋግተው ከተቻለ ዛሬ ካልሆነም ነገ መደበኛው ትምህርት እንዲቀጥል ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ቢ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተዘግተዋል! በኢትዮጵያ ከትላንት ጀምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን የተዘጉ ሲሆን ተጠቃሚዎች የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀንን VPN በተባለ አፕሊኬሽን እየተጠቀሙና መረጃ እየተለዋወጡ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia