TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሁን! ጨለንቆ ላይ ቆመው የነበሩት የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፌደራል ታጅበው መንገዳቸውን ጀምረዋል። የፀጥታ አካላት መንገድ የሚዘጉ እና ሰላምን የሚያደፈርሱ አካላትን በቁጥጥር ስር እያዋሉ ነው።

በጉዞ ላይ ያላችሁ ተማሪዎች ሰላም እንድትገቡ እመኛለሁ።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮ. ተከታዮች በተማሪዎቹ ጉዞ ወቅት የሚፈጠር
አዲስ ነገር ካለ አሳውቃችኃለሁ።

ምንጭ፦N.(ጨለንቆ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲግራት! በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ የክልሉ ተማሪዎች የታሰሩ ተማሪዎች ይፈቱ በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቢሞክሩም በፀጥታ ሀይላት ሰልፉ ተበትኗል። ሰልፈኛ ተማሪዎቹም እየሮጡ በግቢው የጀርባ በር አምልጠዋል።

በግቢው የሚማሩ የሌላ ክልል ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ለመውጣት ቢፈልጉም ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለማረጋጋት እየጣረ ነው። ዛሬም ማንኛውም ተማሪ ከግቢ መውጣት አልተፈቀደለትም።

ምንጭ፦ዳ(አዲግራት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ቡና! ኢትዮጵያ ቡና ከቅ.ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እንዲራዘምለት በደብዳቤ ጠይቋል☝️

አ.አ ላይ ሊደረግ የነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በፀጥታ ስጋት ምክንያት መሰረዙ አይዘነጋም።

ምንጭ፦ @bUNA_GEBEYA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ! በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የሀይማኖት አባቶች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር እየተነጋገሩ ይገኛሉ።

ግቢው መረጋጋት ይታይበታል። የግቢውን ሰላም የሚያስጠብቁ በርካታ የፀጥታ አካላት ወደ ግቢው ገብተዋል።

ምንጭ፦ B(ወልዲያ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ! ቴዲ አፍሮ በአዳማ "እኔም ለወገኔ እዘፍናለሁ" በሚል ፕሮግራም ገቢው ከሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ኮንሰርት ለማዘጋጀት ፍቃድ ጠይቋል መባሉን ማናጀሩ ጌታቸው ማንጉዳይ ሀሰት ነው ሲሉ አስተባበሉ። "ስለ ወሬው እኛ የምናውቀው ነገር የለም" ብለዋል አቶ ጌታቸው።

ምንጭ፦ ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቻይና! በቻይና ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት ዕድል እንድታገኙ እናደርጋለን በሚል ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎችን እየላኩ ያሉ ህገ ወጥ ደላሎች ዜጎችን ለዕንግልት እየዳረጉ ነው ተባለ፡፡

በዚህ ጉዳይ ኢቢሲ የሰራውን ዘገባ ዛሬ ምሽት አቀርብላችኃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሂርና! ወደ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ይዞ ይጓዝ የነበረው መኪና አንድ ግለሰብ ላይ አደጋ በማድረሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። ተማሪዎችን በሌላ መኪና ለመላክ የተደረገው ጥረት አልተሳካም። ባለንብረቶች ሀላፊነት አንወስድም በማለታቸው ተማሪዎቹ የዛሬ አዳራቸውን ሂርና ላይ ለማድረግ ተገደዋል።

ተማሪዎቹ የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦M(ሂርና)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዘረኝነት እይታን የሚጋርድ፣ ጆሮን የሚያደነቁር በሽታ ነው።

ዘረኝነት እና ኤች አይቪ ኤድስን በጋራ እንከላከል! - አብርሀ ደስታ

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ገብተዋል ሀረማያ! ጨለንቆ ላይ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ለረጅም ሰዓት ቆመው የነበሩት እና በፌደራል ፖሊስ ታጅበው አካባቢውን የለቀቁት ተማሪዎች በሰላም ወደ ግቢ ገብተዋል። ተማሪዎቹ ከአዲስ አበባ የተነሱ ናቸው።

የዛሬን የጨለንቆ ውሎና የነበረውን ክስተት ከተለያዩ ታማኝ እና አለምአቀፍ ምንጮች መረጃውን እዳገኘው አቀርብላችኃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም! ዛሬ ቀኑን ሙሉ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ሲካሄድ ቢቆይም አመሻሹን ግቢው ውስጥ አለመረጋጋት ታይቷል። ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው ድንጋይ ሲወራወሩ ነበር። መታወቶችም ተሰባብረዋል።

በአሁኑ ሰዓት ግቢው መረጋጋት ይታይበታል ፌደራል ፖሊስ ሆኔታዎችን ለመቆጣጠር እና ሰላም ለማስፈን ጥረት እያደረገ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከግቢውስጥ መውጣትም ሆነ መግባትም በጥብቅ ተከልክሏል።

ምንጭ፦ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፊ የተባለው የእንግሊዝ ማዕድን አውጪ ኩባንያ በኢትዮጵያ 18ዐ ሚሊየን ዶላር መዋዕለንዋይ በማፍሰስ በወርቅ ማውጣት ለመሰማራት ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የኩባንያውን ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ አምባሳደሮችን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እየሩሳሌም! የአውሮፓ ሃገሮች ኢምባሲዎቻቸውን ወደእየሩሳሌም
እንደሚያዛውሩ እና ለእየሩሳሌም መዲናነቱዋ ዕውቅና እንደሚሰጡ እምነቴ ነው ሲሉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተናገሩ።

ምንጭ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረታቦር! በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ምሽቱን አለመረጋጋት የነበረ ቢሆንም የክልሉ ልዩ ሀይል ወደ ግቢው በመዝለቅ ሁኔታውን ሊቆጣጠር ችሏል። ከግቢው የቶክስ ድምፅ ይሰማ ነበር። እንዳንድ ተማሪዎች ሁኔታውን በመፍራት ተሸሽገዋል።

ምንጭ፦ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዘሬም ዜግነቴም በአንድነት አንድ ነው
ዘሬን አትጠይቁኝ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው።

አንተስ ? አንቺስ ? እናተስ ?

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ! በጣም በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የነበረ ጥያቄ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ያለው ሁኔታ ነው። እኔም በርካታ ሰዎች ስለጠየቁኝ እና በርካታ ተማሪዎችም መረጃ ስላደረሱኝ ይኸው ያለ ሰዓቴ ተገኝቻለሁ።

በወልዲያ ያለው ውጥረት አሁንም እንዳለ ሲሆን ዛሬ ምሽት በግቢው ብሎክ 37 የተባለው ህንፃ የእሳት አደጋ ደርሶበታል። ተማሪዎችም አምልጠው ወጥተዋል። ፖሊስ እና የግቢው ሰራተኞች ችግሮች እንዳይባባሱ እየሰሩ ነው። ከደቂቃዎች በፊት ግቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች እንዳሉም ሰምቻለሁ። አሁን ግን ከግቢ መውጣት ለማንም አካል የተከለከለ ነው።

ምንጭ፦ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳፋሪ መረጃ! ይህን መሰሉ ምንም አይነት ተጨባጭ ነገር ሳይዙ ለህዝብ የሚሰራጩ መረጃዎች ህዝብን እርስ በእርስ ከማጋጨት እና ሰላምን ከማደፍረስ ውጭ ምንም አይነት አላማ የላቸውም። ውጭ ተቀምጦ ይህን ማለት ቀላል ሊሆን ይችላል ለቤተሰብ ግን ከባድ ነው።

ደብረታቦር ላይብረሪ አልጋየም!
@tsegabwolde
አምቦ! በአምቦ ዩኒቨርሲቲ አዋሮ ካምፓስ ተማሪዎች ሰልፍ መውጣታቸው ተሰምቷል። የዛሬ ጥዋት ትምህርትም ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። አንዳንድ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው። ግቢው ተማሪዎችን ለማረጋጋት እየሞከረ ነው።

ምንጭ፦ የአዋሮ ካምፓስ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሶሪያ! ፕሬዝደንት ፑቲን ትናንት ሶርያ ሲደርሱ የሀገራቸው ጀት አብራሪዎች ተዋጊ አውሮፕላናቸውን መሪያቸው ወደተቀመጡበት የአውሮፕላን አቅጣጫ አስጠግተው በማብረር አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፑቲን በሶሪያ ጉብኝታቸው የሀገራቸው ወታደሮች
ሶሪያን ለቀው እዲወጡ አዘዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም! የመማር ማስተማር ስራው ቀጥሏል። ትላንት ምሽት ጥቂት አለመረጋጋት የነበር ቢሆንም ዛሬ ግን ተማሪዎች በየመማሪያ ክፍላቸው ተገኝተው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው። ፌደራል ፖሊስ በግቢው ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገ ይገኛል። ትላንት ምሽትም ፖሊስ በየዶርሙ እየዞረ ፍተሻ አድርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ...

ያናገርኳቸው አንዳንድ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣት እንደሚፈልጉ ገልፀውልኛል። ጥዋት ማታ እየሰጉ መማር እንደሰለቻቸው ለዚህ ጉዳይ ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝለት ትምህርታቸውን ማቋረጥ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia