TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሊደረጉ የነበሩት ጨዋታዎች ሰኞ ፣ የሸገር ደርቢ ደግሞ ማክሰኞ እንዲደረጉ ተወስኗል፡፡

ሰኞ ታህሳስ 2 ቀን 2010
09፡00 መከላከያ ከ ሀዋሳ ከተማ
11፡30 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ጅማ አባ ጅፋር

ማክሰኞ ታህሳስ 3 ቀን 2010
11፡00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ምንጭ፦ ኢ.እ.ፌ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መደወላቡ! አሁን በመደወላቡ ዩንቨርሲቲ ምክንያቱ ምን ይሁን ምን በማይታወቅ ነገር ሰልፍ የተነሳ ሲሆን ፖሊሶች በቀላሉ ተቆጣጥረውታል የተያዙም ተማሪዎች አሉ። አንዳንድ ተማሪዎች በፖሊስ ስለመደብደቸውም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲግራት! በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው መጋጨታቸው ተሰምቷል። ከትላንት ህዳር 29 ጀምሮ በግቢው ከፍተኛ ውጥረት እንደነበር ተማሪዎች ገልፀዋል። አንዳንድ ተማሪዎች ከሌላ ከተማ የመጡ ተማሪዎችን እያስፈራሩ እና እየደበደቡ እንደሆነ ተማሪዎች ገልፀዋል። አንዳንዶች በአንድ ዶርም ውስጥ 10 ሆነው ለመቀመጥም ተገደዋል። ዛሬ አመሻሹን በግቢው ውስጥ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር። የአስተዳደር ሰዎችም በመኪና እየዞሩ ተማሪዎች ወደ ማደሪያቸው እንዲገቡ ሲያደርጉ እንደናበር የግቢው ተማሪዎች ገልፀዋል።

ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱኝ አቀርባለሁ።

ምንጭ፦ የአዲግራት ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኔ አካባቢዬን አፀዳለሁ...እናንተስ ?" በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳትና አረንጓዴ ልማት ወርሃዊ የንቅናቄ መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde
አዳማ ASTU! ተማሪዎች መመለስ ጀምረዋል። ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እንዲመለሱ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱ አይዘነጋም። ዛሬ አመሻሹን ግቢውን ለቀው ከወጡ ተማሪዎች መካከል ጥቂቶቹ መመለሳቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። በነገው ዕለትም በርካታ ተማሪዎች ወደ ግቢው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በርካታ ተማሪዎች ከሳምንት በፊት የአንደኛ ሴሚስተር የMiD EXAM ፈተናን ጥለው መውጣታቸው ይታወቃል።

የአ.ሳ.ቴ.ዩ ግቢው ሰላማዊ እና ለመማር ማስተማር ስራው እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች እንደሌሉ መግለፁ አይዘነጋም።

ከሰኞ ጀምሮ መደበኛው የመማር ማስተማር ስራ ይቀጥል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦B(እዛው ግቢ ውስጥ የቆየ ተማሪ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የቻናሉ ተከታዮች በኔትዎርክ መቋረጥ ምክንያት ትላንት ምሽት በቂ መረጃ ስላላደረስኳቹ ይቅርታ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
# ለተጨነቃችሁ ቤተሰቦች በሙሉ #

አክሱም! የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ትላንት በሰላም ውሏል ግቢ ውስጥ ምንም ችግር የለም። አንዳንድ ተማረዎች ግን አሁም ስጋት ውስጥ መሆናቸውን አልሸሸጉም። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ በሙሉ አቅሙ እየሰራ ይገኛል።

በተጨማሪ...

የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ትላንት ምሽት አንዳንድ የክልሉ ተማሪዎች ከሌላ ቦታ በመጡ ተማሪዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሞክረው ነበር። በየተማሪዎች ማደሪያም እየዞሩ ተማሪዎችን ለመደብደብ እና ለማስፈራራት ሞክረዋል። በተመሳሳይ በዚህም ግቢ የሚማሩ ተማሪዎች በፍርሀት ውስጥ ናቸው። አንዳንዶች ግቢውን ለቀው መሄድ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ሁኔታዎች ለመቆጣጠር እና ጥፋት ያጠፉትንም ለመቅጣት የማጣራት ስራ እየሰራ ነው።

ምንጭ፦ የአክሱም እና የአዲግራት ዩኒቨር ሲቲ ተማሪዎች

እንደ ዘረኝነት ቆሻሻ አስተሳሰብ የለም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እየሩሳሌም! የግብፁ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ታዋድሮስ ሁለተኛ አሜሪካ ኤምባሲዋን ወደ እየሩሳሌም ለማዞር መወሰኗን ተከትሎ ከአሜሪካን ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ውይይት ሰረዙ።

ምንጭ፦ አል አህራም, ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መደወላቡ! ዩኒቨርሲቲው ከግቢ መውጣት የሚፈልጉ ተማሪዎች ከላይ ያሉትን መስፈልቶች ማሟላት አለባቸው ይላል።☝️

ተማሪዎች ትምህርቸውን በአግባቡ እየተከታተሉ ቢሆንም ከግቢ እንዳይወጡ መከልከላቸው ችግር ውስጥ እንዲገቡ እያደረጋቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

@tsegabwolde
አሁን! የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ግቢያቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

💚💛❤️ሰላም ግቡ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዘረኝነት ትልቅ በሽታ ነው። በዘረኝነት የታወረ ሰው ስለእውነት፣ ስለአብሮ መኖር አይጨነቅም፤ ምክንያቱም ብሩህ የሆነ መጪ ጊዜ አይታየውም፤ የለውምም። ለሁሉም ነገር መፍትሄውን ሳይሆን ጨለማውን ነው የሚታየው። ጠቡ ከህዝብ ጋር ነውና ለበሽታው በቀላሉ መፍትሄ የሚገኝለት አይደለም።

እውቀት፣ ሚዛናዊነት እና ሰብኣዊነት በእርሱ ህሊና ላይ ወንበር አይኖራቸውም። ሰውን ያህል ክቡር ፍጡር በጅምላ ይፈርጃል፤ በጅምላ ያወግዛል፤ በጅምላ ይመርቃል፤ በጅምላ ይረግማል። ከዚያ በኋላ በመጨረሻ መፍትሄ ሆኖ ወደ አንጎሉ ሊመጣለት የሚችለው ነገር ሜንጫ ወይም ገጀራ ነው የሚሆነው። በዚያ ገጀራ ደግሞ አንገት ለመቅላት ወደ አደባባይ ይወጣል፤ ሄዶ ሄዶም ይሄ የጥላቻ አዝመራ ፍሬ ማፍራቱ አይቀርምና እልቂት፣ በዘር ተለያይቶ መጨፋጨፍ ይሆናል ውጤቱ።

እንደዚህ ዓይነቱን በሽታ ወደ ሌሎች እንዳይጋባ ማድረግ የሚቻለው አንድም በተቻለ መጠን የመረጃ ክፍተቱን በመሙላት፣ እውነት የሆነውንና እውነት ያልሆነውን በበቂ እውነት አስደግፎ ለይቶ በማሳየት ነው። አንድም ደግሞ እንደዚህ ያለውን አስተሳሰብ የበላይነት አግኝቶ የትውልድ እልቂት ከማድረሱ በፊት በሀሳብ፣ በፖለቲካና በማነኛውም አውድ መታገልና ማጋለጥ ሲቻል መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። ምክንያቱም ከህዝብ እና ከሀገር የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ! እንዲሁም ለእውነት መቆም በሚያስፈልግ ስዓት ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆን እንኳ ለእውነት መቆም የህሊና ጥያቄ ስለሚሆን ነው። በመሰረቱ አንድን ህዝብ ለይቶ በጅምላ የሚጠላ እና የሚያወግዝ የማንም ወዳጅ ሊሆን አይችልም።

እስካሁን ከዓለም ታሪክ እንደምንማረው ስለፍትህ፣ ስለእኩልነትና አብሮ በሰላም ስለመኖር የታገሉት እንጂ በዘረኝነት መንገድ ቁልቁለት የተጓዙ ሲያሸንፉም ሆነ ክብር ሲያገኙ አላየንም። በዓለም ላይ ሁሉ ሰብአዊነት እና የሰውን ክቡርነት እየገነነ በሚሄድበት ጊዜ አንዳንዱ ደግሞ በባለፈው ዘመኑ ተኝቶ ይኖራል፤ ያ ዘመኑ ‘ሃንጎበር’ ሆኖ ስለሚጫጫነው ቶሎ መንቃት ይከብደዋል፤ ስለዚህ ገፋ ቢል ያቃዠው እንደሆነ እንጂ እውነተኛ ትንሳኤ አይኖረውም።
.
.
.
.
.
አስራት አብረሀም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲግራት! የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ይገኛሉ። ከትላንት በሲቲያ ምሽት ጀምሮ ዘር እና አካባቢ መርጦ ትንኮሳ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ እንዲሁም ድብደባም እየተፈፀመ እንዳለ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ተጓዥ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ! የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ግቢ እየተመለሱ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት በአዳማ የሚገኙት ተማሪዎች ወደ ግቢያቸው ለመመለስ የግቢውን መኪና በመጠበቅ ላይ ናቸው።

ሰላም ግቡ!

ምንጭ፦S
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎጠኛ እና ዘረኛ ከሆንክ ታመሃል እንድንግባባ እና እኩል እንድናወራ
መዳን ይኖርብሃል።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ! የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በአዳማ የመደበው መኪና በቂ ባለመሆኑ መቸገራቸውን ተማሪዎች ተናግረዋል። ለሊት 10:00 ሰዓት የወጡ ተማሪዎች እስከ ቀኑ 8 ሰዓት ድረስ መኪና አግኝተው መሄድ አልቻሉም። ዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ መኪናዎችን እንዲልክላቸው ተማሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ከአዲስ አበባ 19 መኪናዎች የግቢውን ተማሪ አሳፍረው ወደ ሀረማያ እያቀኑ ነው።

ምንጭ፦ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲግራት! ግቢውን ለቀን እንዳንወጣ ተደርገናል አሉ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች።

ግቢው ተማሪዎችን ለማረጋጋት እየሞከረ ነው። ስብሰባ ተብሎ ተማሪዎች በአንድ አዳራሽ ቢቀጠሩም እንስካሁን ሊያናግራቸው የመጣ ሰው የለም።

ምንጭ፦ Da
@tsegabwolde
አሁን! አዳማ ASTU! ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር ስብሰባ እያደረጉ ይገኛሉ። በስብሰባው ላይ ዩኒቨርሲቲው ለአንድ አመት አግዷቸው የነበሩትን ተማሪዎች ትምህርቸውን እንዲቀጥሉ ወስኗል።

የተቀጡት(ለአንድ አመት የታገዱት) ተማሪዎች ማክሰኞ ወደ ግቢው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስብሰባው ሲጠናቀቅ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን አደርሳችኃለሁ።

ምንጭ፦ .(በስብሰባው ላይ የሚገኝ ተማሪ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር! በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ስላለው የመማር ማስተማር ስራ ወቅታዊ መረጃ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ለኢቢሲ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከላይ ያድምጡ☝️

ለድምፅ ጥራቱ ይቅርታ ጠይቃለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
😭1
አዲግራት! ተጨማሪ የፀጥታ አስከባሪ ሀይሎች ወደ ግቢው በመግባት ላይ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁጥሩ በርከት ያለ የፀጥታ ሀይሎችን አሰማርቷል።አሁንም ተማሪዎች ወደ ውጭ እንዳይወጡ በሩ እንደተዘጋ ነው።

የዩኒቨርሲቲውን ሁናቴ እየተከታተልኩ አደርሳችኃለሁ።
ምንጭ፦Uh.
@tsegabwolde
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቃችን
ይነሳል አንድ ቀን አይዞሽ ኢትዮጵያችን
:
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቃችን
ይነሳል አንድ ቀን አይዞሽ ሀገራችን

💚አምላክ ኢትዮጵያን አደራ💚

#ቴዲአፍሮ @tikvahethiopia