TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዳማ ASTU! እጅግ በጣም ጥብቅ ማሳሰቢያ!

ሁላችሁም ከግቢው የወጣችሁ ተማሪዎች ግቢው ፍፁም ሰላማዊ እና ለመማር ማስተማር ሂደቱ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች ያለመኖራቸው ተገንዝባችሁ እስከ እሁድ ታህሳስ 1 ድረስ ወደ ግቢ እንድትመለሱ ጥሪ ቀርቧል። ሰኞ ታህሳስ 2 መደበኛ ትምህርት በተገኙት ተማሪዎች ይጀምራል።

የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ!

@tikvahethiopia @tsegabwolde
መቱ! አዲስ ማስታወቂያ!

ከሰኞ ታህሳስ 2 ጀምሮ መደበኛው የመማር ማስተማር ስራው ስለሚቀጥል መማር የሚፈልግ ተማሪ በግቢው እንዲገኝ ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ ያሳስባል።

ምንጭ፦ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ አስቸኳይ! Urgent!

ለሐረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ የትምህርት ሚኒስቴር ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ወደ ግቢ እየተመለሱ ላሉ ተማሪዎች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ስላዘጋጀ ቅዳሜና እሁድ ማለትም 30-03-2010ና 01-4-2010 ጠዋት በአዳማ አዲሱ መናሀርያና በአዲስ አበባ ነባሩ አውቶብስ ተራ በመገኘት
የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ይጋብዛል፡፡

0255530035 / 0910253360
#Urgent

Barattoota Yuunivarsiitii Haramayaa Hundaaf Ministeerri barnootaa Yuunivarsiitii Haramayaa waliin ta'uun barattoota gara yuunivarsiitiitti deebi'a jiraniif tajaajila
geejjiba tolaa waan qopheesseef sanbataa fi dilbata ganama 1. Finfinnee buufata konkolaataa biyyaalessaatti.
2. Adaamaa buufata konkolaataa haaraatti argamuun akka
fayyadamtan isin affeera.

ምንጭ፦ ቢኒ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1🕊1
የኢትዮጵያዊነት ቀን
(በላይ በቀለ ወያ)
:
ቀን ሁሉ በቀን ላይ፣ ተከብሮ እየዋለ
የኢትዮጵያዊነት ቀን፣ ለምን ተዘለለ ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሀገርን የሚያህል ፣ አንድነት በትኖ
ከእኛነት በላይ፣ እኔነት ጀግኖ
ቀን አይከበርም፣ ጨለማ ላይ ሆኖ።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ሊቢያ የባሪያ ንግድ! በሊቢያ በህገ-ወጥ ስደተኞች ላይ የሚፈፀመው የባሪያ ንግድ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከጉዳት ለመታደግ በቅርብ እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ በሊቢያ ያለው የባሪያ ንግድ ድርጊትን የሊቢያ መንግስት እንዲያስቆም
የኢፌዲሪ መንግስት ጠይቋል፡፡

ምንጭ፦ኢዜአ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
እየሩሳሌም! የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ እየሩሳሌምን በእስራኤል ዋና ከተማነት ዕውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ ፍልስጤማውያን “የቁጣ ቀን” ብለው በጠሩት ዓመፁ ጋዛ ላይ የእስራኤል ወታደሮች አንድ ፍልስጥጤማዊ ገድለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ቻናል ለማስታወቂያ ክፍት ነው። በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ የዚህ ቻናል ተከታይ ኢትዮጵያዊያን ምርቶቻችሁን እና አገልግሎቶቻችሁን በተመጣጠነ ክፍያ ማስተዋወቅ ትችላላችሁ።

ቻናሎቻችሁን ማስተዋውቅ የምትፈልጉም ልታናግሩን ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዩን እና የክፍያ ሁኔታውን በ @tsegabwolde መልዕክት አስቀምጡ!

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
እየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ውስጥ ግጭት እንዳይፈጠር የሰጋችው እስራኤል የፀጥታ ኃይሏን አጠናክራለች። በተለይ እስራኤል በኃይል በያዘችው ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻና ምስራቅ እየሩሳሌም ውስጥ ከፍልስጤማውያን ጋር ግጭት እንዳይፈጠር ነው የሰጋችው።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ30 ደቂቃ ውስጥ እነዚህ መረጃዎችን አቀርብላችኃለሁ...

👉የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች..

👉ትላንት አክሱም ዩኒቨርሲቲ

..... @tikvahethiopia
መቀሌ! ከተለያየ ከተማ ሄደው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየደረሰብን ነው አሉ። ብሄር እና ቋንቋ መርጠው ካልታወቀ ቦታ ድንጋይ የሚወረውሩ አካላት እንዳሉ እዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ብሄርን የተመለከቱ የማስፈራሪያ ፅሁፎችን የሚፅፉ ተማሪዎችም እንዳሉ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ መሆን የጀመረው ከወልዲያው ግጭት በኃላ ነው።

ዩኒቨርሲቲው ይህን ጉዳይ ተከታትሎ የግቢውን ስም የሚያጠፉ ተማሪዎች ላይ ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ተማሪዎች ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች(በተለይ አሪድ ካምፓስ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰመራ! ትላንት በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ ከተማ ሰመራ ላይ በተከበረው አሥራ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ለተከሰቱት ግጭቶች የጥፋት ኃይሎችና ኮንትሮባዲስቶች ያሏቸውን ከሰዋል፡፡

ምንጭ፦ VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም! ትላንት በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል አዘጋጅነት በተከበረው 12ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል ላይ አላስፈላጊና ኢትዮጵያዊነትን የማያንፀባርቁ ድርጊቶች መፈፀቸውን የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ።

በአከባበር ስርዐቱ ላይ የተገኙት ተማሪዎች በዘር ተከፋፍለው እርስ በእርሳቸው የጥላቻ ንግግሮችን ሲለዋወጡ እንደነበር ከዛም አልፎ ተርፎ እርስ በእርሳቸው ሲደባደቡ እና ድንጋይም ሲወራወሩ እንደነበር በቦታው የተገኘ የቲክቫህ ኢትዮ. ተከታይ የሆነ የአይን እማኝ ተናግሯል። በተፈጣረው ክስተትም የተጎዱ ተማሪዎች ነበሩ። አሁንም ስጋት በውስጣቸው እንዳለ የሚናገሩት የግቢው ተማሪዎች ግቢው አስፈላጊውን የደህንነት ማስጠበቅ ስራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የትላንቱን ሁኔታ ወደ ሌላ ችግር ከማምራቱ በፊት መቆጣጠር መቻሉን አልሸሸጉም።

በተጨማሪ....

ዘንድሮ ከወትሮው በተለየ ሁናቴ በአንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ 12ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሳይከበር ቀርቷል። ተማሪዎች ለቀኑ እንዲዘጋጁ ጥሪ ከተደረገላቸው በኃላ ሊከበር የነበረው በዓል በድንገት የተሰረዘባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

# ሰውነት ይበልጣል ከዘር ቆጠራ! መማራችን ማወቃችን ፍቅር እና መከባበር ካልታከለበት ባዶ ነው።

ፈጣሪ! ተምሮ እንዳልተማር ሰው ከማሰብ ይሰውረን።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!

ምንጭ፦ G(አክሱም)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
8050~የመቄዶንያ አረጋውያንን እየረዱ በ3ብር እስከ መኪኖች የሚሸለሙበት! ዛሬ A ብለው ይላኩ!ይሸለሙ!አሁኑኑ ይላኩ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም አስከባሪዎቹ ተገደሉ! ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ሀሙስ ዕለት 14 የተመድ ሰላም አስከባሪዎች ሲገደሉ ከ 40
በላይ መቁሰላቸውን አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለስልጣን ዛሬ በትዊተር አስታወቁ። ለባልደረቦቻቸውም የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ተ.መ.ድ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎጃም ያረሰውን፣ለጎንደር ካልሸጠ
ጎንደር ያረሰውን፣ለጎጃም ካልሸጠ
የሀረር ነጋዴ ፣ ሸዋላይ ከልሸጠ
የትግሬ አባት ልጅን ፣ለወለጋ ካልሰጠ
ፈቅር ወዴት ወዴት፣ ወዴት ዘመም ዘመም
ሀገርስ አለቺኝ፣ሀገር የኔ ህመም
ስሩ እዳይበጠስ ፣ መቋጠሪያ ደሙ
አረጓዴ ቢጫ ቀይነው ቀለሙ

@tikavhethiopia
ከይቅርታ ጋር! ማስታወቂያዎችን በቻናሉ ላይ ለማስነገር ፍላጎት እንደነበራችሁ የገለፃችሁ በድጋሚ መልዕክታቹን በ @tsegabwolde ላይ በመላክ የክፍያ ሁኔታውን ማወቅ ትችላላችሁ።

እዲተዋወቅ የምትፈልጉት ..
.ድርጅት ከሆነ ድ/D
.ቻናል ከሆነ ቻ/C
.የጉዞ ወኪሎች ጉ/T
.በግላችሁ እቃ የምታስመጡ እ/E

ብላችሁ በድጋሚ እድትልኩልኝ በአክብሮት ጠይቃለሁ! ከቁጥራችሁ ብዛት ለሁላችሁም መልዕክት መላኩ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው ይህን የለጠፍኩት።

@tikvahethiopia
🔘ሰበር ዜና~ጦርነቱ አበቃ🔘

ኢራቅ ከአሸባሪው ኢስላሚክ ስቴት (አይ ኤስ) ጋር ስታካሂድ የነበረው ጦርነት መጠናቀቁን አውጃለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይደር አል አባዲ ዛሬ በባግዳድ በተካሄደ ጉባዔ ላይ አንደገለፁት፥ የኢራቅ ጦር እስከ ሶሪያ ድንበር ድረስ ያለውን የሀገሪቱን ክፍል ሙሉ በሙሉ ከአሸባሪው አይ ኤስ ነፃ
በማውጣት ተቆጣጥሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “የኛ ጦር የኢራቅ ሶሪያ ድንበር አካባቢን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል፤ ስለዚህ ከአሸባሪው አይ ኤስ ጋር ሲደረግ የነበረው ጦርነት መጠናቀቁን አውጃለው” ብለዋል።
“ጠላታችን የጥንት ስልጣኔያችንን
ሙሉ በሙሉ መግደል ይፈልግ ነበር፤ በአንድነታችን እና ተግተን በመዋጋታችን ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ልናሸንፈው ችለናል” ሲሉም ተናግረዋል።

የኢራቅ ጦር በበኩሉ ባወጣው
መግለጫ፥ “ኢራቅ ሙሉ በሙሉ
ከአሸባሪው ኢስላሚክ ስቴት
(አይ.ኤስ) ነፃ ወጥታለች” ብሏል።

ምንጭ፦ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረር! አስቸኳይ ማስታወቂያ ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ☝️

ምንጭ፦ L
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢህአዴግ! ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ የሚጠበቀው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከፀጥታ አካላት በደረሰን የስልክ መልዕክት መሠረት ዛሬ እና ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ስታድየም ሊደረጉ የነበሩ ውድድሮች መሰረዛቸውን እየገለፅን የተስተካከለውን ፕሮግራም ወደፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን"

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia