TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲግራት! በአድግራት የነበረው የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ያለምንም የፀጥታ ችግር ነው የተጠናቀቀው።

ስለ ቡና ስትጨነቁ ለነበራችሁ ሁሉ እኛ ሰላም ነን ይሏችኃል የክለቡ ደጋፊዎች።

ምንጭ ፦ @buna_gebeya

@tsegabwolde
አሁን ጅማ JiT! ተማሪዎች መብራት በመጥፋቱ ምክንያት በመጮኻቸው በዚህ ምሽት በግቢው ውስጥ ከ2ኛ አመት በላይ የሆኑ ተማሪዎች ላይ ፖሊስ ድብደባ እየፈፀመ መሆኑን ተማሪዎች ተናገሩ።

የሚሰማ አካል ካለ ጩኸታችንን አሰማልን ሲሉ የግቢው ተማሪዎች ምልዕክታቸውን ልከዋል።

ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ይዤ እመለሳለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ JiT ተማሪዎች መልዕክት ..

"ሰላም ወንድሜ! ከጅማ ነው ምፅፍል በአውን ሰዓት(5:15) jit ግቢ ውስጥ ፈደራሎቹ ሁሉን ተማሪዎች ይዞ እየመቱ እና እስፖርት እያሰሩ ይገኛሉ፡፡ አንድም ተማሪ ዶርም የለም ከሴቶች በስተቀር፡፡ወገን ይድረስልን፡፡"

ዋ ~ ከጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT! በጥቂት ተማሪዎች ምክንያት በርካቶቻችን እንዲህ ልንደረግ አይገባም በገዛ ሀገራችንም ይህን አይነቱ እርምጃ ሊወሰድብን በመቻሉ ልባችን ተሰብሯል አሉ የJiT ተማሪዎች። በግቢው ያለውን ሁኔታ በመፍራትም በአጥር ዘለው ከግቢ የወጡ ተማሪዎችም እንዳሉ ተሰምቷል።

ጥቂት ጉዳት ከደረሰባቸው ተማሪዎች ውጭ ሁሉም ተማሪ ሰላም ነው። ግቢውም የተረጋጋ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ተችሏል።

በግቢው የተፈጠረውን ክስተት እና ምክንያቱን እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን አስተያየት እንደደረሰኝ አቀርብላችኃለሁ።

የJiT ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ከወጡ ከቀናት በኃላ መመለሳቸው ይታወቃል። በነገ በኃላ ባሉት ቀናትም መደበኛ ትምህርት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ የJiT ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀሌ! በመቀሌ ስላለው ሁኔታ የተረጋገጠ መረጃ ከታማኝ ምንጭ አልያም ከመንግስት ሚዲያዎች ካገኘው በ20 ደቂቃ ውስጥ አቀርብላችኃለሁ። ካልሆነም በነገው የመረጃ ዳሰሳ የተፈጠረውን ጉዳይ ወደ እናተ አደርሳለሁ።

መቀሌ የምትገኙ በተለይ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የምትገኙ መልዕክት ልታስቀምጡልኝ ትችላላችሁ።
@tsegabwolde
መቀሌ! በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ካምፓስ ችግር አለ ተብሎ ሲወራ የቆየው ፍፁም ስህተት መሆኑን የግቢው ተማሪዎች አረጋግጠዋል። ግቢው ሰላማዊ ነው።

በወልዲያ በተፈጠረው ሁኔታ በከተማው ውጥረት የነበረ ቢሆንም በውጭ ሚዲያዎች እጅግ በተጋነነ መልኩ እና ሰላም እንደሌለ ተደርጎ የሚወራው ግን የተሳሳተና ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚደረግ ነው።

ምንጭ፦ B

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ፣አስቸኳይ ማስታወቂያ ለሁሉም የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር እና አልሙናይ ዳይሮክተሬት! አዲስ ማስወቂያ!
@tikavhethiopia
መዳ ወላቡ! በዩኒቨርሲቲው ትምህርት ከተቋረጠ ሁለት ሳምንት ማለፉ ይታወሳል ሆኖም እስካሁን ግቢ ግቡና ወደ ትምህርት ገበታችሁ ተመለሱ ብትባሉም አሻፈረኝ ስትሉ ቋይታቹሃል። የግቢው ሴኔት ባለፈው ሐሙስ ዝግ ስብሰባ ከግቢው ፕሬዝዳንት ጋር አድርጎ ነበር። ነገ ማለትም ሰኞ 25/03/2010 እስከ 11 ሰዓት ዳግም ምዝገባ አለ በዚህ ዳግም ምዝገባ ያልተመዘገበ ተማሪ አዲስ የሚሰጠውንም መታወቂያ ያልወሰደ ተማሪ የትምህርት ቤቱ ተማሪ እንዳልሆነና ወደ ግቢ ከማክሰኞ ጀምሮ የማናስገባ መሆናችንን እያስታወቅን ለሚደርስባችሁ መጉላላት ሃላፊነቱን ትወስዳላችሁ !

መደወላቡ ዩኒቨርስቲ አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት

ምንጭ፦Ou

@tikavhethiopia @tsegabwolde
👍1
ዘሬም ዜግነቴም በአንድነት አንድ ነው
ዘሬን አትጠይቁኝ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው።

አንተስ ? አንቺስ ? እናተስ ?

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ! በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አንማርም አድማ ዛሬም መቀጠሉ ተሰምቷል። ተማሪዎች ቅሬታቸውን ይዘው ሰልፍ ሊወጡ ቢሞክሩም ሰልፉ በፌደራል ፖሊስ እና በክልሉ ልዩ ሀይል ጫና ምክንያት ሳይደረግ መቅረቱን ተማሪዎች ተናግረዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን አቋም በቀጣይ አደርሳችኃለሁ።

ምንጭ ፦የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ ASTU! ዛሬ ጥዋት የMID EXAM ይጀመራል ቢባልም ለፈተናው አንድም ተማሪ ሳይገኝ ቀርቷል። ዩኒቨርሲቲው ግን ስለ ፈተናው መራዘም ወይም ስለ ማቅረቱ ያለው ነገር የለም። በከሰዓቱ የፈተና መርሀ ግብር ምን እንደሚፈጠር አብረን የምናይ ይሆናል።

ከቀናት በፊት በርካታ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸው ይታወቃል።

ምንጭ ፦ የአ.ሳ.ቴ.ዩ ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ! የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የትምህርት ሚንስቴር ከፍተኛ አመራሮች በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ስለተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ከተማሪዎች ጋር እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ዛሬ ህዳር 25 ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልፆ ነበር።

ለመሆኑ ውይይቱ ተደረገ?? ከተደረገስ ምንም ጉዳዮች ተነሱ??

ግቢ ውስጥ ያላችሁ ተማሪዎች መረጃዎችን አካፍሉን።

ውይይት ስለመኖሩ የተሰማው ከግቢው FM 91.5 ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
መደ ወላቡ! የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን መረጃዎች ደርሰውኛል አንዳንድ ተማሪችም በግድ እንዲመዘገቡ ፖሊስ ጫና ሲያደርግባቸው እንደነበረ ተናገርዋል።

ግቢው ዛሬ ምዝገባውን ተመዝግበው አዲስ መታወቂያ የማያገኙ ተማሪዎችን ከነገ ጀምሮ ወደ ቅጥር ግቢው እንደማያስገባ በማስታወቂያ ገልፆ ነበር።

ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲም በርካታ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣቸው አይዘነጋም።

ምንጭ ፦ ቦን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT! ትላንት ምሽት ጥቂት ተማሪዎች በ(GC)ተመራቂ ተማሪዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ መሞከራቸው ተማሪዎች ገልፀዋል። በዚህም ምክንያት ፖሊስ የተማሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲል ሀይል ተጠቅሟል። በዚህ መሀል በርካታ ተማሪዎች ያለምንም ጥፋት ሲደበደቡ አምሽተዋል።

ዛሬ ግቢው ወደ ቀደመው ሰላሙ የተመለሰ ሲሆን GC ተማሪዎችም መደበኛ ትምህርታቸውምን መከታተል ቀጥለዋል። ወደ ቤታቸው ሄደው የነበሩ ተማሪዎች በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

ዛሬም ግቢው ተማሪዎች እንዳይወጡ ክልከላ እያደረገ መሆኑም ተሰምቷል።

ምንጭ ፦ ሞግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🥰1
ሀረማያ! በሀረርና ድሬዳዋ ከተሞች ውስጥ የምትገኙ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደዋናው ግቢ ለመመለስ የትራንስፖርት አገልግሎት ዩኒቨርሲቲያችን ያቀረበ በመሆኑ ከሀረር ስላሴ ቤተክርስቲያን አካባቢ፤ ድሬዳዋ ለምትገኙ ደግሞ በለገሀር ባቡር ጣቢያ አደባባይ ሄዳችሁ በተዘጋጁት መኪኖች እንድትሳፈሩ እናሳውቃለን።

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ~ ህዳር 25 ቀን 2010 ዓ.ም

ምንጭ ፦ HU FM 91.5
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀሌ! የመቀሌ ከተማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ትላንት ምሽት ከ3 ሰዓት ጀምሮ እስከ ለሊቱ 8 ሰዓት ድረስ በፌደራል ፖሊስ ታጅበው በሰላም መቀሌ ከተማ መግባታቸው ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ኪ.ኢዛ.(የመቀሌ ከተማ ደጋፊ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል በተቀሰቀሰው የድንበር ግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች በአዲስ አበባ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ተጠልለዋል። ተፈናቃዮቹ የአዲስ አበባ አስተዳደር መጠለያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ምኝጭ ፦ ዶይቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረር! ስላሴ ቤተክርስቲያን የቆመውን የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ መኪና በፎቶው ተመልከቱ መኪናው ከቆመ ረጅም ሰዓት ቢሆነውም ውስጥ ያሉት ተማሪዎች ከ10 የማይበልጡ ናቸው።

ምንጭ ፦ ካሂ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ ASTU! የMID EXAM ከዛሬ ጀምሮ እንደሚሰጥ አ.ሳ.ቴ.ዩ. ቢያሳውቅም ተማሪዎች ግን ግቢውን ለቀው ወደቤታቸው ለመሄድ በአዳማ መናኸሪያ መኪና ለመሳፈር ሰልፍ ይዘዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረር! አዲስ ማስታወቂያ!

የሀረር ጤናና ሳይንስ ኮሌጅ ዛሬ ህዳር 25 ከቀኑ 8:30 ጀምሮ አስቸኳይ ስብሰባ ስለሚኖር ተማሪዎች ተገኙልኝ ብሏል። የስብሰባው ቦታ LTH!

የሚነሳውን አብየት ጉዳይ ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ አደርሳችኃለሁ።

ምንጭ ፦ ሳንዲያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia