TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዳማ ASTU #Loading>>
የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድንገት በግቢው በተፈጠረው ሁኔታ በመደናገጥ በአጥር እየዘለሉ ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ተናገሩ። የተለያዩ ተማሪዎች በየዶርሙ እየገቡ ተማሪዎችም ለማጥቃት ሞክረዋል። መስታወቶች መሰበራቸውን የሚያሳዩ የፎቶ ማስረጃዎች ደርሰውኛል። ከዶርም ውጭ ኳስ በማየት ላይ የነበሩ ተማሪዎች በፖሊስ መያዣቸው ተሰምቷል።

ተጨማሪ ጉዳዮችን በተለይም የዩኒቨርሲቲውን አቋም መረጃው እንደደረሰኝ አቀርብላችኃለሁ።

ምንጭ ፦ የASTU ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ ASTU! ለሰዓታት ባለመረጋጋት ውስጥ የነበረው የአ.ሳ.ቴ.ዩ. አሁን መረጋጋቶች ታይተዋል። ተማሪዎች ላይ የደረሰ አደጋም የለም። ዩኒቨርሲቲው የተማሪው ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ቢገኝም ተማሪዎች ግን በፌደራል ፖሊስ እየደረሰብ ያለው ወከባ ከባድ ነው ብለዋል። ውጭ የተገኙ በርካታ ተማሪዎችም በፖሊስ ተይዘው ሜዳ ላይ ይገኛሉ። በርካታ ተማሪዎች በአጥር ዘለው ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። አዳራቸውንም በእምነት ተቋማት እና በየሰው ቤት ለማድረግ እንዳሰቡ ተናግረዋል። በግቢው ውስጥ ያሉ ቀሪ ተማሪዎች እንዳሉት ዛሬን በግቢው አድረው ነገ ጥዋት ግቢውን ለቀው እንደሚወጡ ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከሰኞ ህዳር 25 ጀምሮ የMid Exam እሰጣለሁ ቢልም ተማሪዎቹ በዚህ ሁኔታ ፈተና ላይ መቀመጥ እጅግ አዳጋች መሆኑን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ስለተከሰተው ክስተት የሚለውን በነገው ዕለት ለማድረስ ሞክራለሁ።

@tikvahethiopia
አዳማ! የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ በሙሉ ተረጋግቷል። ከዶርም ውጭ የነበሩ ተማሪዎችም ወደ ዶርማቸው እየተመለሱ ነው። ነገ የሚኖሩ ጉዳዮችን ተከታትይ አሰማችኃለሁ።

የተማሪዎች ጉዳይ የነገዋ ኢትዮጵያ ጉዳይ ነው። እኔም ይመለከተኛል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ምሽቱ በክስተቶች የተሞላ ነበር። @tikvahethiopia
እናስተውል! ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች እንጂ የፕሬዘዳንቱ ወይም የገለሰቦች አይደለም። ዩኒቨርሲቲ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች የሚሰባሰቡበት ትልቅ ተቋም ነው።

ሰው እንዴት የራሱን ንብረት ያወድማል? ይሰብራል ?

የትኛውም አይነት ጥያቄዎች ቢነሱ በተለያየ መንገድ ማቅረብ እየተቻለ ነገ የራሳችን ወንድሞች መጥተው የሚማሩበትን ንብረት እንዴት እናወድማለን? እንዴት እራሳችን የምናነብበትን እውቀት የምናገኝባትን ላይብረሪ እንዲህ እናደርጋለን ? በጣም ያሳዝናል!

ጥያቄ መጠየቅ የስልጣኔ ምልክት ነው። ነገር ግን ማንም በማይጎዳበት የራሳችንም ንብረት በማይጠፋበት መሆን አለበት።

ነገ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን መጥተው እንደሚማሩ አንዘንጋ።

መንግስት በመንግስት ይተካል ዛሬ ያለው ነገ ይቀየራል ሀገር እና ህዝብ በምንም የሚተኩ አይደሉም።

ለሁላችንም ፈጣሪ ልቦና ይስጠን !

ቸር ወሬ ያሰማን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በመውጣት በሀረማያ ፣ በሀረርና በድሬዳዋ ከተሞች ውሥጥ የተቀመጣችሁ ተማሪዎች ከሰኞ ህዳር 25 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት የሚጀመር ሥለሆነና በግቢው ውሥጥም ትምህርት ለመጀምር የሚያሥችል አስተማማኝ ፀጥታ በመኖሩ ከህዳር 24 ጀምሮ ወደ ግቢ እንድትመለሱ ጥሪ እያቀረብን ከተጠቀሱት ከተሞች እቃዎቻችሁን ለማምጣት ተሽከርካሪ ያዘጋጀን መሆኑን እንገልፃለን።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 23 ቀን 2010 ዓ.ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia

ምንጭ፦ HU FM 91.5
አዳማ! የአ.ሳ.ቴ.ዩ በግቢው ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን አውከዋል ክፍል እየገቡ ተማሪዎችንን እና መምህራንን ከክፍል እዲወጡ ሲያደርጉ ነበሩ ያላቸውን 7 ተማሪዎች ለአንድ አመት ከትምህርት ገበታቸውን እንዲታገዱ አደረገ።

ተጨማሪውን ከላይ ባለው ማስታወቂያ ያንብቡ☝️

@tsegabwolde
⚪️🔘ሰበር ዜና🔘⚪️

የወልዲያና መቀሌ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ዛሬ ሊካሄድ የነበረው የወልዲያና መቀሌ ከተማ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ልባሴ አሊጋዝ እንደገለፁት፥ ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመው፥ ዛሬ ከረፋዱ 3 ሰዓት ከ 30 አካባቢ በሁለቱ ክለቦች ደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው።

ጨዋታውን ለማድረግ የሚያበቃ የጸጥታ ሁኔታ ባለመኖሩ መራዘሙን አቶ ልባሴ ተናግረዋል።

ኃላፊው አሁን ላይ በደጋፊዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ፖሊስ የተቆጣጠረው ሲሆን፥ የተፈጠረው አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ሰላም እየተመለሰ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦የአማራ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ , ፋና ብሮድካስቲንግ

@tikvhaethiopia @tsegabwolde
ወልዲያ! በወልዲያ እና በመቀሌ ከተማ ደጋፊዎች መካከል ተነስቶ የነበረው ግጭት መብረዱ ተረጋግጧል። ይህም ቢሆን በርካታ የመቀሌ ደጋፊዎች በስጋት ውስጥ እንደሆኑ ተናግረዋል። ፖሊስ እንደገለፅው ከሆነም ዛሬ የነበረው ግጭት የጨዋታውን መረሀ-ግብር ለማስፈፀም እንደማያስችል ተናግሯል። ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙም ተሰምቷል።

በተለይ በዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ የውድድር ዘመን ይህን መሰሉ የደጋፊዎች ግጭት እዚህም እዚያም እየታየ መምጣቱ ኳስ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ከሜዳ ሊያርቃቸው እንደሚችል ይገመታል።

እዛው የምትገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታዮች ተጨማሪ መረጃ ካላችሁ በ @tsegabwolde ላይ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
አዳማ ASTU! ተማሪዎች እቃቸውን ይዘው በአጥር ሲዘሉ። @tikvahethiopia
አዳማ ASTU! ግቢው እቃችሁን ይዛችሁ መውጣት አትችሉም በማለቱ በአጥር ዘለን ለመውጣት ተገደናል አሉ የASTU ተማሪዎች።

ነገ የአመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ የMID EXAM ይሰጣል ብሎ ዩኒቨርሲቲው ቢያሳውቅም ተማሪዎች ግን ግቢውን ለቀው መውጣት አላቆሙም።

መልዕክታቸውን ለቲክ ቫህ ኢትዮ. የላኩ ተማሪዎች እንዳሉት ይህ ሁሉ በሚሆንበት ሁኔታ ፈተና ላይ ለመቀመጥ ዝግጁ ባለመሆናችን እንዲሁም ከፈተናው ህይወታችን ስለሚበልጥብን ግቢውን ጥለን ወጥተናል ብለዋል።

ትላንት ምሽት በዩኒቨርሲቲው ትንሽ አለመረጋጋት የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ሁኔታውን ተቆጣጥሮ ግቢውን ወደ ቀደመው ሰላሙ መመለስ ችሏል። ነገር ግን ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።

የASTU ተማሪዎችን እያንዳንዷን እንቅስቃሴ እና የዩኒቨርሲቲው ግብረ መልስ ምን እደሚመስል እየተከታተልኩ አደርሳችኃለሁ።

ምንጭ ፦ የASTU ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" እኔ በዕውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ ዐይናማዎቹ ሲያወሩ ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት ግን የሰዉ አስተሳሰብ ነው።

የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል።

ጃፓንና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን አልምተው ነው። ቤታችሁ ገብታችሁ እንድታጤኑት ነው። ኢትዮጵያ ውሥጥ ብዙ ሺ ሠዎች ፈርሠው መሠራት አለባቸው ከባለሥልጣን ጀምሮ እሥከ ተራ ወዛደርና ወታደር።"

💚💛❤️መጋቢ ሀዲሥ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተለጠፈ! በተለይ ግቢ ውስጥ ላሉ ተማሪዎች። ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ግቢው በተማሪዎች የሚለጠፉትን ማስታወቂያዎች ሊቆጣጠረው እና ሊያስቆመው አልቻለም። @tikvahethiopia
ሀረማያ! በተማሪዎች እና በአስተዳደሩ መካከል ያለው ፍጥጫ አሁንም ቀጥሏል።

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የግቢው ሰላም አስተማማኝ በመሆኑ በየአቅራቢያ ከተሞች ያላችሁ ተማሪዎች እስከ ነገ ህዳር 25 ድረስ ተመለሱ ብሎ ጥሪ ማቅረቡ አይዘነጋም። ለተማሪዎቹም እቃቸውን ለማምጣት መኪና ሊመድብ እንደሚችልም ገልጾ ነበር።

በሌላ በኩል...

የተማሪዎችን እንቅስቃሴ እናስተባብራልን ያሉ ተማሪዎች በለጠፉት ማስታወቂያ አሁንም በግቢው ውስጥ የሚገኙ ጥቂት ተማሪዎች ግቢውን እስከ ነገ ህዳር 25 ለቃችሁ እድትወጡ የሚል ቀጭን ትህዛዝ አስተላልፈዋል።

ይህ በእንዲ እንዳለ ዛሬ ከወደ ሀረማያና ሀረር የተገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ተማሪዎች ወደ ግቢው እየተመለሱ አይደለም።


ምንጭ ፦ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤታችን የጠፋው ፍቅር ነው! አንድ የሚያድርገን ሰው መሆናችን ነው። ሁላችንንም ያሰባሰበን ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊነት እኮ ረቂቅ ነው! ኢትዮጵያዊነት እኮ መታደል ነው። እባካችሁን በብሄር በዘር አናስብ። አንከፋፈል አንበታተን አንድ እንሁን። ዘረኝነት ክፉ በሽታ ነው። ሰው መሆን ከዛም ኢትዮጵያዊ ሆኖ መኖር ይበቃናል። ወደ ፈጣሪ እንመለስ። ፈጣሪን ይቅርታ እንጠይቅ! ፈጣሪ አንድ እንዲያደርገን ተግተን እንፀልይ። ፈጣሪ ሁሉን ይችላል!

አንድነት፤ሰላም፤ፍቅር !!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
⚪️🔘አሳዛኝ ሰበር ዜና⚪️🔘

በወልድያ ከተማ ከእግር ኳስ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ጠፍቷል ተባለ። በ5ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወልዲያ ላይ ሊደረግ የነበረው የወልድያና የመቀሌ ከተማ ጨወታ በረብሻ ምክንያት የተቋረጠ ሲሆን፣ አሁን የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንዳስታወቁት አንድ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል ሲረዳ የነበረ ሰው ህይወቱ አልፏል። የተለያዩ ሱቆች እና ተቋማት ዘረፋ ተካሂዶባቸዋል ብለዋል።

ምንጭ ፦ ንጉሱ ጥላሁን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ! የወልዲያ ከተማ እና የመቀሌ ከተማ የእግር ኳስ ቡድኖች ደጋፊዎች ወልዲያ ከተማ ውስጥ ዛሬ መጋጨታቸውን ዶቼ ቨለ ዘገበ።

በግጭቱ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ሕንፃ መቃጠሉን የዐይን እማኞች ተናግረዋል። ሁኔታውን በጣም አስጊ ነው ሲሉ የገለጹ የዐይን እማኝ እንደሚሉት ግጭቱ በደጋፊዎች መካከል ይፈጠር እንጂ የብሔር ግጭት መልክ ይዟል ብለዋል። ስድብ እና ግርግር በወልዲያ ከተማ እንደነበር የተናገሩ ሌላ የዐይን እማኝ የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸውን እና ውሃ መርጨታቸውን ተናግረዋል።

የደሴ ነዋሪ እንደሆኑ የገለጡ የዶቼ ቨለ አድማጫች እንደ ተናገሩት ወልድያ የተገኙት በአጋጣሚ ነበር ወዳጃቸውን ለመጠየቅ። ጠዋት ሦስት ሰአት አካባቢ «ግርግር አለ ሲባል ለማየት» መውጣታቸውን ገልጠዋል። «የሆነ ደስ የማይል ስድብ ነበር» ሲሉም በሁለቱ ደጋፊዎች መካከል ግጭት ያጫረውን ምክንያት አክለዋል። «ከአካባቢው ራቅ ለማለት ሞከርን» ያሉት የዐይን እማኝ «ተኩሶቹ እየጨመሩ ነው የመጡት» ብለዋል።

ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው፦ «ያየሁት ነገር፤ አስለቃሽ ጋዝ ይተኮስ ነበር፤ ከየት እንደሆነ ባላውቅም ጥይቶች ድምፅ ይሰሙ ነበር» ብለዋል።

የአማራ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ግጭቱ መከሰቱን አረጋግጦ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ሊደረግ የታቀደው ጨዋታ «ላልተወሰነ ጊዜ» መራዘሙን ዘግቧል። የአማራ መገናኛ ብዙኃን
ድርጅት ያነጋገራቸው የሰሜን ወሎ ዞን ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልባሴ አሊጋዝ «ጨዋታውን ለማድረግ የሚያበቃ የጸጥታ ቁመና ባለመኖሩ»
ምክንያት መራዘሙን ገልጠዋል።

ምንጭ ፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ - ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ ASTU! ነገ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የአንደኛ አጋማሽ የMID EXAM የመኖር እድሉ እጅግ በጣም ጠባብ መሆኑን ተማሪዎች ተናገሩ። ዩኒቨርሲቲው ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ሊያዘዋውረውም ይችላል ተብሏል።

ፕሬዘዳንቱ ፈተናው እንደማይቀር ለተማሪዎች ቢናገሩም በርካታ ተማሪዎች ዛሬ እና ትላንት የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ግቢ ለቀው ውጥተዋል። በርካታ ተማሪዎችም ወደ ቤታቸውን አቅንተዋል።

ምንጭ ፦ Y

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT! ከዩኒቨሲቲው ወጥተው የነበሩ ተማሪዎች ተምዝግበው እየተመለሱ ነው። ወደቤት የሄዱም ተማሪዎች በመጭዎቹ ቀናት ጅማ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ተማሪዎቹ እንዳሉት ግን ጥያቄያቸው ስላልተመለሰ አሁንም ተቃውሟቸው እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ወደ ግቢው ተመለስን ማለት ተስማምተናል ማለት አይደለም ዛሬ የመውጫ ፈተናን አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል።

ምንጭ ፦ ካስ,ኤ,ብሩ

@tsegabwolde @tikvahethiopia