ጥብቅ ማስታወቂያ! ለአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ የመጀመሪያ አጋማሽ የMid Exam ከህዳር 25 ጀምሮ የሚሰጥ በመሆኑ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ በጥብቅ አሳስቧል።
ምንጭ ፦ የግቢው ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ ፦ የግቢው ተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአትሌቷ ገዳይ እጁን ለፖሊስ መስጠቱ ተሰማ!
ፈረንሳይ ትኖር የነበረችዉን ኢትዮጵያዊት አትሌት ዝናሽ ገዝሙ ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረዉ እትሌት እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል። የፈረንሳይ ፖሊስ በስም ያልተጠቀሰዉ የ28 ዓመቱ ወጣት አትሌት፤ ዝናሽን በትራስ አፍኖ እና በዋንጫ ደብድቦ ሳይገዳላት አልቀረም ብሏል።
ምንጭ ፦ ዶቼ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈረንሳይ ትኖር የነበረችዉን ኢትዮጵያዊት አትሌት ዝናሽ ገዝሙ ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረዉ እትሌት እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል። የፈረንሳይ ፖሊስ በስም ያልተጠቀሰዉ የ28 ዓመቱ ወጣት አትሌት፤ ዝናሽን በትራስ አፍኖ እና በዋንጫ ደብድቦ ሳይገዳላት አልቀረም ብሏል።
ምንጭ ፦ ዶቼ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር ስዩም ተሾመ ስለ ጅማ ዩኒቨርሲቲ(JiT) ተማሪዎች እና ስለ ግቢው ተከታዩን ፅሁፍ ፅፏል።
"ፕረዜዳንቱ ወደ ውጪ፣ ተማሪዎቹ ወደ ግቢ!!"
የተማሪዎችን ጥያቄ ተቀብሎ ተገቢ ምላሽ መስጠት የዩኒቨርሲቲው ፕረዜዳንት ሥራና ሃላፊነት ነው፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ በመምህራንና ተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ ተግባራዊ እንዲደረግ አመራር መስጠት የፕረዜዳንቱ ድርሻና ሃላፊነት ነው፡፡ በዚህ መሠረት፣በአንድ በኩል ተማሪዎቹ ስለ መመሪያው ዓላማና ግብ በማሳወቅ ማሳመን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጥያቄያቸውን ለትምህርት ሚኒስቴር በማቅረብ መመሪያው ያለበትን ክፍተት መጠቆምና የተሻለ የማሻሻያ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
ተማሪዎች ወደ አመፅና ተቃውሞ የሚሄዱት ፕረዜዳንቱ ይህን ማድረግ ስለተሳነው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ግቢውን ለቅቆ መውጣት ያለበት የዩኒቨርሲቲው ፕረዜዳንት እንጂ ተማሪዎቹ አይደሉም፡፡ ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎቹ የመማሪያ ተቋም እንጂ የፕረዜዳንቱ የግል ንብረቱ አይደለም፡፡
ተማሪዎቹ Cost_Sharing ከፍለው ነው የሚማሩት፣ ፕረዜዳንቱ ደሞወዝ ተከፍሎት ነው የሚሰራው፡፡ ተማሪዎቹ አገልግሎት የማግኘት መብት አላቸው፣ ፕረዜዳንቱ አገልግሎት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
የተማሪዎቹ የወደፊት እድላቸውን በሚወስን ማንኛውም ጉዳይ ላይ የመጠየቅ፥ የመቃወምና አቤቱታ የማሰማት መብት አላቸው፡፡ ፕረዜዳንቱ የተማሪዎቹን ጥያቄ ተቀብሎ ምላሽ መስጠት አለበት፡፡ ለተማሪዎቹ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ በመስጠት መብታቸውን ማክበርና ማስከበር የተሳነው ፕረዜዳንት ግዴታውን መወጣት ተስኖታል፡፡ የሥራ ድርሻውን መወጣት ያቃተው ፕረዜዳንት ያለው አማራጭ ራሱን ከሃላፊነት በማንሳት ዩኒቨርሲቲውን ለቅቆ መውጣት ነው፡፡
ተማሪዎቹ በአግባቡ ያቀረቡትን ጥያቄ
መመለስ የተሳነው ፕረዜዳንት የዩኒቨርሲቲውን ቅጥር ግቢ ለቅቃችሁ ወጡ ማለት አይችልም፡፡ ከዚያ ይልቅ፣ እሱ ራሱ ቅጥር ግቢውን ለቅቆ መውጣት አለበት፡፡
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ እንዲለቁ የተደረጉ ተማሪዎች ከከተማው ነዋሪዎች ምግብ ለምነው እየበሉ (ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ምስል) በአጠቃላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲው ባለቤቶች ናቸው፣ ፕረዜዳንቱ ተቀጣሪ ደሞወዝኛ ነው፡፡ ሥራውን መስራት ካቃተው ግቢውን ለቅቆ መውጣት አለበት፡፡ ነገር ግን፣ እንዲህ እንደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕረዜዳንት ተማሪዎችን ከግቢ አስወጥቶ በየሰው ቤት ምግብ ለምነው እንዲበሉ ካደረገ ግን ሥራ ከመልቀቅ በተጨማሪ በወንጀል መጠየቅ አለበት፡፡ "
ስዩም ተሾመ ~ አምቦ~ኢትዮጵያ

🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
በ1 ወር ውስጥ 15,000 ሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ወደሀገራቸው መመለስ እንደሚፈልግ የተመድ ትላንት አስታወቀ። ወጪውን የአውሮጳ ኅብረት ይሸፍናል። የአፍሪቃና የአውሮጳ ኅብረት በዚህ ሳምንት በጋራ ስደተኞችን ከሊቢያ በአስቸኳይ ለማስወጣት ተስማምተዋል።
ምንጭ ፦ ተ.መ.ድ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ ፦ ተ.መ.ድ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረር! በሀረር መናኸሪያ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ (ሀረር ግቢ) ተማሪዎች ከተማውን ለቀው እንዳይወጡ መደረጋቸው ተሰምቷል። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት እዛው መናኸሪያ ይገኛሉ።
ምንጭ ፦ ዳን,ጆ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ ፦ ዳን,ጆ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኘው ሰው ቁጥር ከ718 ሺህ በላይ መሆኑንና ከእነዚህም መካከል ሕክምና እየተከታተሉ ያሉት 69 ከመቶ
የሚሆኑት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል። በትላንትናው ዕለት የአለም ኤድስ ቀን ለ30ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል።
ምንጭ ፦ የአሜሪካ ድምፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚሆኑት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል። በትላንትናው ዕለት የአለም ኤድስ ቀን ለ30ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል።
ምንጭ ፦ የአሜሪካ ድምፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
20 ሺ ምርጥ አባላት ! ከመላው ኢትዮጵያ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሁሉም ክልሎች፣ ከሀገር ውጭም ከበርካታ ሀገራት! እጅግ በጣም አመሰግናለሁ! መረጃዎችን እየላካችሁ ህዝብ ጋር እንዲደርስ እያደረጋችሁ ያላቹ ወጣቶች በጠቅላላው ምስጋና ይገባችኃል እና መረጃውን በሚከታተሉት ተከታዮች ስም አመሰግናለሁ! አሁንም አብረን እንጓዛለን።
ትንሽ ተብሎ የሚታለፍ ጉዳይ የለም በሀገሪቱ ውስጥ እየተፈፀሙ ያሉ ጉዳዮች በየደቂቃው ይለጠፋሉ።
ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነው!
@tikvahethiopia @tsegabwolde

ጅማ JiT! የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለሴት ተማሪዎች ያደረገውን ጥሪ ከላይ በተለጠፈው ማስታወቂያ ይመልከቱ።
:
በርካታ ሴት ተማሪዎች ከግቢ ውጭ ሲሆኑ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉትም ወደቤታቸው መመለሳቸው ይነገራል።
ምንጭ ፦ NeH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
:
በርካታ ሴት ተማሪዎች ከግቢ ውጭ ሲሆኑ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉትም ወደቤታቸው መመለሳቸው ይነገራል።
ምንጭ ፦ NeH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድንቁ ሰው አረፈ ! አሳዛኝ ዜና!
ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ፀሐፌ-ተውኔት፣
ገጣሚ፣ ድምፃዊ፣ ተዋናይ፣ ዲያቆንና የሌሎችም በርካታ ክህሎቶች፣ አስተዋፅዖ፣ ክብርና ሽልማቶች ባለቤቱ ሣሙዔል ፈረንጅ አረፈ።
ሣሙዔል ፈረንጅ በ81 ዓመት ዕድሜው ለረዥም ዓመታት በኖረባት ቶሮንቶ ካናዳ ከትናንት በስተያ ኅዳር 20/2010 ዓ.ም. ያረፈው ላለፉት 15 ዓመታት በሕክምና ሲረዳ ከቆየ በኋላ ነው ህይወቱ ያለፈው።
ነገ፣ ቅዳሜ ኅዳር 23/2010 ዓ.ም. ለአቶ ሣሙዔል ፈረንጅ በቶሮንቶ ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ከተከናወነ በኋላ አስከሬኑ በዲችዉድ መካነ-መቃብር እንደሚያርፍ ቤተሰቦቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ከቀኝአዝማች ፈረንጅ ቦቶ እና ከወይዘሮ አበበች ገመዳ በመጋቢት 1929 ዓ.ም. ወለጋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የተወለደው አቶ ሣሙዔል ቀደም ሲልም በአማርኛና በእንግሊዝኛ ዜና አንባቢነትና በጋዜጠኝነት ሲሠራበት የነበረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዋና ዳይሬክተር ሆኖ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከተሾመበት ጊዜ አንስቶ በማስታወቂያ ሚኒስቴር እና በሌሎችም የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በባለሙያነትና በኃላፊነት አገልግሏል።
ሣሙዔል ለአጭር ጊዜም የቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት ባልደረባም ሆኖ ሠርቷል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በ1966 ዓ.ም. ተከስቶ ለነበረው ድርቅና ረሃብ ተጎጂዎች ድጋፍ በማሰባሰብ፣ የአክሱም ሃውልት እንዲመለስ በተደረገው ጥረት ውስጥ በመሣተፍና በሌሎችም ጉልህ መድረኮች ውስጥ ተሣትፏል አቶ ሣሙዔል።
ሣሙዔል ፈረንጅ ሁለት መፅሐፎችን የደረሰና ተውኔቶችንም የፃፈ ከመሆኑም በተጨማሪ ስለ ልዕልት ዳያና ሕልፈት በእንግሊዝኛ የፃፈው ግጥም የተለያዩ ዓለምአቀፍ ሽልማቶችን አስገኝቶለታል።
እአአ በጥር 1994 ዓ.ም. ታትሞ የወጣው ታይም መፅሔት የሣሙዔልን መጣጥፎች “የምርጦች ምርጥ” በሚል አምዱ ሥር አስፍሯል።
ሣሙዔል ከኦክላሆማ ገዥ የኦክላሆማ ግዛት፣ እንዲሁም ከጣልያን ፕሬዚዳንት ጁዜፔ ሣራጋት የኢጣልያ የክብር ዜግነት ተሰጥቶታል።
ሣሙዔል ፈረንጅ የስምንት ልጆች አባት፣ የሰባት ልጆች አያት፣ የአንድ ልጅ ቅድም አያት ለመሆን ታድሏል።

ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ዛሬ ጥዋት በሀረር መናኸሪያ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ተማሪዎች ወደቤታቸው እንዳሄዱ ሲከለከሉ እና ከመኪና እንዲወርዱ ሲደረግ የሚያሳይ ነው። @tikvahethiopia
ሀረር! በሀረር ግቢ የሚማሩ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደቤታቸው እንዳይሄዱ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል። መኪና ውስጥ የገቡ ተማሪዎችም ተለይተው እንዲወርዱ ተደርገዋል። ኬላ ላይም ተማሪዎች ተለይተው ወደ መጡበት እንዲመለሱ ሲደረግ ነበረ። ተማሪዎች ግን በተለያየ መንገድ ከከተማው ለመውጣት እና ወደቤታቸው ለመሄድ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ እዛው የሚገኙ ተማሪዎች መረጃ አድርሰዋል።
ግቢው ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማሳሰቢያ እንደሰጠ አይዘነጋም።
ምጭ፦ ዴቭ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግቢው ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማሳሰቢያ እንደሰጠ አይዘነጋም።
ምጭ፦ ዴቭ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒ.! አዲስ ማስታወቂያ ከተማሪዎች ህብረት!
ትምህርት መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ተጨማሪ ደህንነታቸውን ሊያስጠብቁ የሚችሉ አካላት ገብተዋል አለ የተማሪዎች ህብረት።
ተማሪዎችን የምታሸብሩ ደግሞ ለሚደርስባቹ ችግር ሀላፊነት አንወስድም ሲል በማስታወቂያው ገልጿል። ሙሉውን ከ
ምንጭ ፦ ደሬ
@tsegabwolde

በራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናችሁ ህዳር 27-28 መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅታችሁ እንድታጠናቅቁ።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት - ማይጨው
ምንጭ፦ ቢኒ አፍሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የራያ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት - ማይጨው
ምንጭ፦ ቢኒ አፍሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጌዲዮ ዞን ተከስቶ የነበረው ግጭት ዋነኛ ምክንያቱ በዞኑ የሚታየው ድህነት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡ ችግሩን በየደረጃው የሚገኘው አመራር ከመፍታት ይልቅ በዞኑ የሚገኘው ሌላው ብሔረሰብ የችግሩ ምንጭ እንደሆነ አስመስለው በማቅረብ እንዲባበስ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
በዞኑ ከ12ሺ 4ዐዐ በላይ ነዋሪዎች መሬት አልባዎች መሆናቸው ግጭቶች እንዲፈጠሩና እንዲባባሱ የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከቱም ተገልጿል፡፡
በዲላ ከተማ የሰላምና የልማት ኮንፍረንስ ተካሂዷል፡፡
ምንጭ ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዞኑ ከ12ሺ 4ዐዐ በላይ ነዋሪዎች መሬት አልባዎች መሆናቸው ግጭቶች እንዲፈጠሩና እንዲባባሱ የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከቱም ተገልጿል፡፡
በዲላ ከተማ የሰላምና የልማት ኮንፍረንስ ተካሂዷል፡፡
ምንጭ ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ! የጅማ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል በየካምፓሱ ስላለው የመማር ማስተማር ሂደት በተመለከተ ትላንት ባድረገው የምክክር መድረክ ከላይ በምትመለከቷቸው ነጥቦች ላይ ከስምምነት ደርሷል።
ምንጭ ፦ ፍሬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ ፦ ፍሬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተሰሩት የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት የተማሪ አውቶቡሶችና የአምበሳ
የከተማ አውቶቡስ ተደራራቢ አውቶቡሶች ርክክብ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ መካከል ዛሬ ተፈጸመ፡፡
ምንጭ ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከተማ አውቶቡስ ተደራራቢ አውቶቡሶች ርክክብ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ መካከል ዛሬ ተፈጸመ፡፡
ምንጭ ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ ASTU! ከላይ የምትመለከቱት ዛሬ ማምሻውን የተላከልኝ ፎቶ ነው👇
የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኞሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሰኞ ህዳር 25 የMID EXAM ስለሚኖር ተዘጋጁ ብሎ ጥብቅ ማሳስቢያ ቢሰጥም አንድም ተማሪ ላይብረሪ ውስጥ ሊያነብ አልተገኘም።
ምንጭ ፦ ኤፍ

በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ባለፈው ጥቅምት 4 ቀን በተከሰተው ከባድ የፈንጂ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት 512 መሆኑን የሟቾቹን ማንነት ለማጣራት የተቋቋመ ግብረ ኃይል አስታወቀ።
ምንጭ ፦ ዶይቸ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ ፦ ዶይቸ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia