TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ ሶዶ! ትላንት ከለሊት ጀምሮ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች በግቢው ውስጥ በሚደርስባቸው በደል ምክንያት ሲጮኹ አድረዋል። ተማሪዎቹ እንደሚሉትም የትላንት ለሊቱን ዝርፊያ ጨምሮ በ2 ወር ውስጥ ለ6ጊዜ ዝርፊያ ተፈፅሟል። ሴት ተማሪዎቹ እንደገለፁት ሌሎች በርካታ ችግሮች እንዳሉባቸው ግቢው አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረገላቸው እንዳልሆነ እንዲሁም ለሊት እንኳን አንብበው ወደ ማደሪያቸው ለመሄድ ስለሚፈሩ በትምህርታቸው ላይ አሉታዊ ተፅኖ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት አስረድተዋል።

በአሁኑ ሰዓት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ከሴት ተማሪዎች ጋር አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ ፦ አብር
@tikvahethiopia
ቴክኖሎጂ ! ሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ በ12 ደቂቃ ውስጥ የሚሞላ የሞባይል ስልክ ባትሪ መስራቱን አስታወቀ። ባትሪው የስልካችን ሃይል ረጅም ጊዜ እንዲቆይ የማድረግ አቅም አለው ነው የተባለው። ሳምሰንግ አሁን የሰራቸው ባትሪዎች እንደየደረጃቸው የኤሌክትሪክ ሃይል ለሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችም ተመራጭ ናቸው ብሏል። ኩባንያው “የሳምሰንግ አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት” ተመራማሪዎች ግራፌን ቦል (graphene ball) የተባለ አዲስ ባትሪ መስራታቸውን ገልጿል። ከግራፌን ንጥረ ነገር የተሰራው የአሁኑ ባትሪ፥ ከመደበኛዎቹ የሊቲየም አዮን ባትሪዎች ሃይልን ለመሙላት ከሚጠይቀው ጊዜ አምስት እጥፍ በፈጠነ ጊዜ ውስጥ እንደሚሞላ ነው የተጠቆመው። ከዚህም ባሻገር የስልኩን የሃይል የመቆጠብ አቅም በ45 በመቶ እንደሚያሳድ ሳምሰንግ
በመግለጫው አመላክቷል።

ምንጭ፦ኢንዲፔንደንት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ ! በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥዋት የመማር ማስተማሩ ስርአት መቋረጡ ተሰምቷል። ተማሪዎችም ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።

በግቢው ስላለው ሁኔታ ትምህርት ስለተቋረጠበት ምክንያት ዩኒቨርሲቲውም ስለሚሰጠው ምላሽ እየተከታተልኩ ነግራችኃለሁ።

ምንጭ ፦ ሮብ,አም

@tsegabwolde @tikvahethiopka
Audio
የHU FM 91.5 የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ውሳኔን ከላይ እንደምትሰሙት አቅርቦታል።

ምንጭ ፦ Mm
@tikvahethiopia @tsegabwolde
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄዱት አካባቢያዊ፣ የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች ምርጫዎች ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ ቦርዱ ዝግጅቱን በአፋጣኝ
እንዲያጠናቅቅ አሳስቧል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ሀረር! አዲስ ማስታወቂያ! የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ (ሀረር ካምፓስ) ግቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች ከ7 ሰዓት ጀምሮ ወደ ግቢው ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አሳስቧል። በተጨማሪም የዋናው ግቢ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ እየተመለሱ እንደሆነ ገልጿል።

ምንጭ ፦ ኤክመ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ! በዛሬው እለት የቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ቦረና በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ይቁም በማለት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። የፌደራል ፖሊስም ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ እና ሐይል መጠቀሙንና ተማሪዎች ላይም ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መረጃ ገልፀዋል። በተጨማሪም ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንዳይወጡ ተከልክለዋል።

ምንጭ ፦ አቤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዳሸን ባንክ አንድ ቢሊየን ብር አተረፈ። በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ 303 ቅርንጫፎች ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ለሚልቁ ደንበኞቹ አገልግሎቶቹን ማቅረብ የቻለው ባንኩ በሂሳብ ዘመኑ መጨረሻ ጠቅላላ ሀብቱን ወደ ብር 34 ነጥብ 6 ቢሊየን አሳድጓል፡፡

ምንጭ ፦ ድሬትዩብ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! አዲስ ማስታወቂያ! የጅማ ቴክኖሎጂ ኢስቲትዩት ዛሬ አርብ ህዳር 22/2010 ዓ.ም. የመጨረሻ የድጋሚ የምዝገባ ቀን መሆኑን ጠቅሶ ምዝገባውን ያላከናወኑ ተማሪዎች በቀጣይ ለሚሆነው ነገር ሀላፊነቱን እራሳቸው እንደሚወስዱ ገልጿል።

ምንጭ ፦ ካስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ የሕገ ወጥ ስደት መከላከል ስራዎች 14 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ።

የአውሮፓ ሕብረት በአፍሪካ ሕገ ወጥ ስደትን ለመከላከል በዘረጋው የትረስት ፈንድ ለአፍሪካ የድጋፍ ፕሮግራሙ አማካኝነት ለኢትዮጵያ የ14 ሚሊዮን ዩሮ
ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በኢትዮጵያ የጣልያን ኢምባሲ ፕሮግራሙን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ! አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፍፁም ሰላማዊ እና የተረጋጋ ቢሆንም ተማሪዎች ግን ግቢውን ጥለው እየወጡ መሆኑ ተሰምቷል። ዩኒቨርሲቲው በዚህ ጉዳይ ያወጣው ማስታወቂያ የለም።

ምንጭ ፦ካሊ,ናት
@tikvahethiopia @tsegabwolde
በአለም አቀፍ ደረጃ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን ለ3ዐኛ ጊዜ እየተከበረ ነው፡፡ በኢትዮጵያም "አሁንም ትኩረት ለኤች አይ ቪ ኤድስ' በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ ያለው፡፡ ከግንዛቤ ማነስ ጋር ተያይዞ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስረጭት በኢትዮጵያ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ የዘንድሮ በአልም ቫይረሱን ለመከላከል ለግንዛቤ ማሳደግ ትኩረት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ምንጭ ፦ ኢቢሲ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በተማሪዎች የተለጠፈ። @tikvahethiopia
ጅማ ! የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማንን እንስማ ግራ ገብቶናል ተጨንቀናል አሉ።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም ካምፓሶች ማለት ይቻላል የትምህርት ስር ዓቱ ተቋርጧል። በተለይ በJiT ግቢ የመውጫ ፈተናን በመቃወም ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ከወጡ እንዲሁም ግቢውም አላስገባችሁም ካለ 5ቀን ሆኗል።

በዋናው ግቢ ደግሞ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ጠንከር ያሉ ማስታወቂያዎች የተለጠፉ ሲሆን በራሪ ወረቀቶችም ለሊት ተማሪዎች በተኙበት በየዶርሙ ሲበተኑ አድሯል።

ማስታወቂያዎቹ እንደሚሉት እስከ እሁድ ድረስ ግቢውን ለቆ የማይወጣ ተማሪ ሀላፊነቱ እንደሚወስድ ይገልጿሉ። ተማሪዎችም ይህን ሁኔታ በመፍራት ግቢውን ለቀው ለመውጣት ቢፈልጉም ግቢው አለቅም ብሏቸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ዩኒቨርሲቲው በሚያወጣው ማስታወቂያ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በትምህርት ገበታቸው ላይ ያልየተገኙ ተማሪዎች ለሚወሰድባቸው እርምጃ ተጠያቂ ይሆናሉ ብሏል።

አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ተማሪዎች እንደሚሉት ይህ ችግር ተፈቶ ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት መንገድ ቢመቻች መንግስትም ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ቢሰጥ መልካም እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩልም የመውጫ ፈተና ድጋሚ በማጤን ስለ ፈተናው ግንዛቤ መፍጠር ካልሆነም ፈተናው መቅረትም ካለበት እንዲቀር ተደርጎ ትምህርታቸውን ቢቀጥሉ እንደሚመርጡ ገልፀዋል።

ከዛው ከጅማ ሳንወጣ ፦

በJiT ግቢ የነበሩ ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታችን እንዲስተጓጎል አንፈልግም አንድ አመትም ላግ ማድረግ አንፈልግም በማለት ዛሬ ወደ ክላስ ተመልሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ በመቶ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ድጋሚ ተመዝግበዋል። ዛሬም በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች በአቋማቸው እንደፀኑ ከግቢ ውጭ ናቸው።

ትላንት ምሽት 12:00 ላይ ሁለት ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ቤተክርስቲያን እየሄዱ ለምን ተመዘገባቹ በሚል በ4 ልጆች ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።

ምንጭ ፦ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመውጫ ፈተና የሚቀር አይደልም - የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር

የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ምዘና በሚቀጥለው ዓመት መጀመሩ እርግጥ ነው ብሏል ሚኒስቴሩ።

በህክምናና በህግ ትምህርት ተሞክሮ ከፍተኛ ውጤት ያስገኘው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ምዘና /EXIT EXAM/ ከ2011 ጀምሮ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ከመጪው 2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የመውጫ ምዘና የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ተፈላጊውን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት እንዲላበሱ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

የመውጫ ምዘናው ተመራቂዎች ተፈላጊውን አነስተኛ የምሩቅ ፕሮፋይል ለማሟላታቸው ማረጋገጫ የሚሰጥ ተማሪዎች፤ ከመመረቃቸው በፊት ብቃታቸውን የሚያረጋግጡበት የምዘና አይነት መሆኑንም ነው ያስረዱት።

ምዘናው በብዙ አገራት የተለመደና ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት በገለልተኛ አካል የተዘጋጀን ምዘና ወስደው ብቃታቸውን የሚያረጋግጡበት አሠራር መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታው፥ በኢትዮጵያም ባለፉት ዓመታት በህግ እና በህክምና ትምህርት ተሞክሮ ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ተመራቂ ተማሪዎች በቂ ዝግጅት በማድረግ በራሳቸው እንዲተማመኑና ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚያስችል፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተማሪዎቻቸውን በጥሩ ውጤት ለማሳለፍና ያላቸውን ተፈላጊነት ለማሳደግ እንደሚያግዛቸው ዶክተር ሳሙኤል አመልክተዋል።

መምህራንም ተማሪዎቻቸው ብቃት ተላብሰው እንዲመረቁ ለማስቻል በኃላፊነት ተከታታይ ምዘና በማካሄድ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ክፍተቶች
እንዲሞሉ፣ ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎችም በተማሪው ላይ አመኔታ እንዲያሳድሩና ብቃት አላቸው ብለው እንዲያምኑ እንደሚያስችላቸው ሚኒስትር ደኤታው አብራርተዋል።

በመሆኑም ባለፉት ዓመታት በህክምና እና በህግ ትምህርት ከተገኘው ልምድ በመነሳት ከመጪው ዓመት ጀምሮ የመውጫ ምዘና በ35 የመንግስት
ዩኒቨርሲቲዎች የቅደመ -ምረቃ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች የመውጫ ምዘና እንዲወስዱ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

የመውጫ ፈተና በውጤታማ ትግበራ ስኬት አሠራር በአጭር ጊዜ አመርቂ
ውጤት ለማስመዝገብ ትኩረት ከተሰጣቸው ሰባት የትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብሮች አንደኛው መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🙏1😭1
ወላይታ ሶዶ ! ዛሬ ጥዋት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች በግቢው እየገጠሟቸው ስላሉ ችግሮች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር አስቸኳይ ስብሰባ እያደረጉ እንደነበረ መረጃ አድርሻቹ ነበር። ለመሆኑ ስብሰባው በምን ተቋጨ ምንስ ጉዳዮች ተነሱ ?

የተወሰኑ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በተገኙበት ሴት ተማሪዎቹ እነዚህ አብየት ጉዳዮች አንስተዋል።👇

በካምፓስ ውስጥ ጥበቃ ያደርጋሉ የተባሉት ወንድ የጥበቃ ሰራተኞች ስራቸውን ዘንግተውታል በሴቶች መኖሪያ ግቢ ውስጥ ዝርፊያም እየፈፀሙ ነው ስለሆነም የመኖሪያ ግቢያችን ውስጥ አይግቡ አልያም በሴት ጥበቃዎች ይቀሩልን።

ጥበቃዎቹ ለደህንነት በማለት በየጊዜው ዶርሞች መቆለፋቸውን ለማረጋገጥ ይመጣሉ ይህ እንዲሆን አንፈልግም እናረጋግጣለን በሚል ሰበብ ዝርፊያ እየተፈፀመብን ነው።

በተለያየ ጊዜ ወደ ሴቶች ቅጥር ግቢ የሚገቡ ወንዶች ቢቻል በሴት ቢቀየሩ ካልሆነም መለያ እንዲሰጣቸው።

ወንድ የካምፓስ ጥበቃዎች በሴቶች ግቢ ውስጥ በየህንፃው እየተዘዋወሩ ምቾት እየነሱን ነው ይህ ተግባር ይቁም እንዲሁም ከሴት ፕሮክተሮች ጋር ረጅም ሰዓት በመቀመጥ ሴት ተማሪዎችን ምቾት እየነሱ ስለሆነ ይህም እንዲቀር ጠየቀዋል።

እስከ ዛሬ ለጠፉት ንብረቶች ዩኒቨርሲቲው በማጣራት ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።

ከላይ ያሉት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በዛሬው ስብሰባ ተነስቷል። በስብሰባው የተካፈሉ ተማሪዎች እንዳሉትም ከአመራሮቹ አጥጋቢ መልስ ሳይገኝ ስብሰባው ተጠናቋል። ከስብሰባው መፍትሄ እናገኛለን ብለን ብንጠብቅም ይህ ሳይሆን ቀርቷል አሁም በስጋት መኖራችን ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል ሴት ተማሪዎቹ።

ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰራ እና አግባብነት ያላቸው የተማሪ ጥያቄዎችን ለማስተናግድ እና ለመመልስ ጥረት እንደሚያደርግ ገልጿል።

ምንጭ ፦ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች

@tikvahethiopia
👍1
ስፖርት ፦ የ2018ቱ የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል። ሩሲያ በምታዘጋጀው የ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ምድብ ድልድል በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት፡
ምድብ 1፡ ሩሲያ፤ ሳኡዲ አራቢያ፤ ግብጽ፤ ኡራጋይ

ምድብ 2፡ ፖቹጋል፤ እስፔን፤ ሞሮኮ፤ ኢራን

በምድብ 3፡ ፈረንሳይ፤ አውስትራሊያ፤ ፔሩ፤ ዴንማርክ

በምድብ 4፡ አርጄንቲና፤አይስላንድ፤ ክሮሺያ፤ ናይጄሪያ

ምድብ 5፡ ብራዚል፤ ስዊዘርላንድ፤ ኮስታሪካ፤ ሰርቢያ

ምድብ 6፡ ጀርመን፤ ሜክሲኮ፤ ስዊድን፤ ደቡብ ኮሪያ

ምድብ 7፡ ቤልጂየም፤ ፓናማ፤ ቱኒዚያ፤ እንግሊዝ

ምድብ 8፡ ፖላንድ፤ ሴኔጋል፤ ኮሎምቢያ፤ ጃፓን ሆነው
ተደልድለዋል፡፡

ከተደለደሉት ምድቦች መካከል በጠንካራ ቡድኖች ስብስባቸውም ደረጃ ወጥቶላቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡
ምድብ 6፡ ጀርመን፤ ሜክሲኮ፤ ስዊድን፤ ደቡብ ኮሪያ በጠንካረነቱ የመጀመሪያውን ደረጃ ሲይዝ

2ኛ- በምድብ 3፡ ፈረንሳይ፤ አውስትራሊያ፤ ፔሩ፤ ዴንማርክ

3ኛ - ምድብ 2፡ ፖቹጋል፤ እስፔን፤ ሞሮኮ፤ ኢራን

4ኛ- በምድብ 4፡ አርጄንቲና፤አይስላንድ፤ ክሮሺያ፤ ናይጄሪያ

5ኛ - ምድብ 7፡ ቤልጂየም፤ ፓናማ፤ ቱኒዚያ፤ እንግሊዝ
6ኛ - ምድብ 8፡ ፖላንድ፤ ሴኔጋል፤ ኮሎምቢያ፤ ጃፓን

7ኛ - ምድብ 5፡ ብራዚል፤ ስዊዘርላንድ፤ ኮስታሪካ፤ ሰርቢያ

እንዲሁም የመጨረሻው 8ኛ ቀላል ምድብ ድልድል ምድብ 8፡ ፖላንድ፤ ሴኔጋል፤ ኮሎምቢያ፤ ጃፓን ናቸው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር ማህበር ያዘጋጀው ኤግዚቢሽን ዛሬ በይፋ ተከፍቷል።👇
👍1
ኤግዚቢሽን ! ዛሬ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር አሶሴሽን ፕሬዘዳንት አርክቴክት መስከረም ታምሩ እና ምክትሉ አርክቴክት ሮዳስ ስዩም የተገኙበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል። ከፓናል ውይይቱ በተጨማሪም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር አሶሴሽን ያዘጋጀው ኤግዝቢሽን በይፋ ተከፍቷል። ኤግዚቢሽኑ በነገው ዕለትም እንደሚቀጥላም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተላኩት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ምንጭ ፦ በዩኒቨርሲቲው የአርክቴክቸር ተማሪዎች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገዳ ስርዓት ከትውልድ ትውልድ ሳይበረዝ እንዲተላለፍ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከወትሮው የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሣ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ ፦ ኢቢሲ
@tikvahethiopia @tsegabwolde