TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በፈተና የሚፀና የተባረከ ነው። ፈጣሪ ለሁላችንም ትዕግስቱን ፅናቱን ያድለን። አሜን የሚል

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! 2ኛውም ፈታኝ ቀን ከፈጣሪ ጋር በሰላም አልፏል። ሁሉም ተማሪዎች በሰላም አድረዋል።

ትላንት የተወሰኑ የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች በዝናብ ሲመቱ ነው ያደሩት። ወንድ ተማሪዎች የቤተክርስቲያኑን ውስጠኛ ክፍል ለሴቶች ለቀው በረንዳ ላይ ለሊቱን ሙሉ በብርድ ሲደበደቡ በዝናብ ሲመቱ አድረዋል። ይህም ሆኖ ግን ሁሉም ተማሪዎች በሰላም ስለማደራቸው ማረጋገጥ ችያለሁ። ሌሎች በርካታ ተማሪዎችም በየሰው ቤት ለምነው አድረዋል። ዛሬም ከተማሪዎቹ ጋር በሀሳብ አብረን ውለን የሚፈጠረውን አዲስ ነገር እንሰማለን።

ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነው !
ምንጭ ፦ ደሬ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከተመረቀ አንድ አመት ያለፈው የኢትዮ- ጂቡቲ የባቡር መስመር ሰው እና እቃ ማጓጓዝ በፈረንጆቹ ጥር 1(ታህሳስ 23) በይፋ እንደሚጀምር አንድ የድርጅቱ
ሀላፊ ለENF ተናግረዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት ሀላፊው የሀይል አቅርቦት፣ የቪዛ ጉዳይ፣ ባቡሩን የመሞከር ስራ እና የመሳሰሉት ችግሮች የባቡር መስመሩ እስካሁን ስራ እንዳይጀምር ምክንያት እንደነበሩ ገልፀዋል።

ምንጭ ፦ ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ሰሜን ኮርያ አዲስ የባላስቲክ ሚሳኤል አስወነጨፈች።

ሰሜን ኮርያ አዲስ የባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏን ደቡብ ኮርያን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ አስነብቧል፡፡ ፒዮንግያንግ የባላስቲክ ሚሳኤሉን ማስወንጨፏን የአሜሪካ ወታደራዊ ምንጮችም አረጋግጠዋል፡፡ በሰሜን ኮርያ የሰዓት አቆጣጠር ለሊት አጋማሽ ላይ የተወነጨፈው ሚሳኤል እንደከዚህ ቀደሙ ጃፓንን አቋርጦ የሚጓዝ መሆኑን ግን እስካሁን ድረስ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ተገልጿል፡፡ ሰሜን ኮርያ በያዝነው የፈረንጆች አመት ተደጋጋሚ የሚሳኤል ሙከራዎችን ማድረጓ ይታወሳል፡፡

ምንጭ ፦ ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰሜን ኮሪያ ያደረገችው የሚሳኤል ሙከራ ሁሉንም የአሜሪካ ክፍል መምታት የሚችል ነው የተብሏል።

ምንጭ ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ በግቢው የትምህርት ስርዓቱ መቋረጡን ገልፆ ከዛሬ ህዳር 20 ጀምሮ ሁሉም ተማሪ ወደ ትምህርት ገበታው እንዲመለስ በጥብቅ አሳስቧል። ይህ ማይሆን ከሆነ የተለያዩ አገልግሎቶች ይቋረጣሉ ተማሪውም ለሚደርስበት እንግልት ሀላፊነቱን ይወስዳል ብሏል።

#ጅማ19
1
እኔም ለአረጋዊያን እሮጣለሁ!

በድሬዳዋ ከተማ የሚገኝው ዳዊት
የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል ግንባታ ድጋፍ ለማድረግ አገር አቀፍ የሩጫ ፕሮግራም ታህሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ተዘጋጅቷል።

መነሻ ቦታ ~ የምድር ባቡር አደባባይ
መድረሻ ቦታ ~ የምድር ባቡር አደባባይ
መነሻ ሰዓት ~ ከጠዋቱ 1:00 ፕሮግራም ተይዟል።

[የቲሸርት መሸጫ ዋጋ 100 ብር]

የሜሪ ጆይ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ሲሰተር ዘቢደር ዘውዴ ለማዕከሉ ግንባታ "እኔም ለአረጋውያን እሮጣለሁ!" ብለዋል።

ለበለጠ መረጃ ~ አቶ ዳዊት በቀለ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል
መሥራችና ሥራ አስኪያጅ +251 913353291 ወይም የማዕከሉን የክብር አምባሳደር አርቲስት ናትናኤል ግርማ (ናቲ ድሬ)ን - በፌስቡክ ገጹ ~ # Naty dire- ናቲ ድሬ ~ ጋር መነጋገር ይችላሉ።

ምንጭ ፦ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ጅማ ! ህዝቡ ችግራችንን ይወቅልን ብለን አደባባይ ብንወጣም ፌደራል ፓሊስ ደበደበን በአስለቃሽ ጭስም በተነን አሉ።

ዛሬ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተሰባስበው እቃቸውን ሳይዙ ወደ ቤት ለመሄድ ከወሰኑ በኃላ ህዝቡ ያሉበትን ችግር እንዲያውቁላቸው እጃቸውን ጭንቅላታቸው ላይ አድርገው አደባባይ ቢውጡም የፌደራል ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ብትኗልቸዋል። በርካታ ተማሪዎች በፍርሀት በየሰው ቤት ተሸሽገዋል። ጥቂት ተማሪዎችም በሁኔታው በመደናገጣቸው ወድቀው ጉዳት ደርሶባቸዋል። እቃቸውን ሳይዙ ወደ ቤት ለመሄድም ተቸግረዋል። ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚወስደው መንገድ እና ወደ መናኸሪያ የሚውስደው መንገድም ተዘግቷል። ከትምህርት ሚንስቴር የተወከለ ሰው ለውይይት ይመጣል ቢባልም እስካሁን ድረስ የመጣ የለም።

ምንጭ ፦ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ!

ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር ዩኒቨርሲቲው ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልፆ በቅጥር ግቢው ያሉ እና ግቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች በመመለስ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ምንጭ ፦ ልኡል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! ገንዘብ ከባንክ እንዳናወጣ እና ወደ ቤታችን እንዳንሄድ በጅማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት አልሰጣችሁም አለን ሲሉ የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ተናገሩ። ተማሪዎቹ ወደ ዋናው ቅርንጫፍ እና ወደ መርካቶ ቅርንጫፍ ገንዘብ ለማውጣት ቢያመሩም መከልከላቸውን በቦታው የነበረ ተማሪ ተናግሯል።

ምንጭ ፦ ኤም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለፈው አርብ እና ቅዳሜ የህዳሴ ግድብን ተመልክቶ ዘገባ ለማቅረብ ወደ ስፍራው ተጉዘው የነበሩት የመንግስት እና የውጭ ጋዜጠኞች ከፕሮጀክቱ ሀላፊ ያልጠበቁት ነገር እንደገጠማቸው ለ # ENF ተናግረዋል። ሀላፊው ጋዜጠኞቹ በፈለጉት አቅጣጫ ፎቶ እንዳያነሱ እና ቪድዮ እንዳይቀርፁ ከማገዳቸውም ባሻገር ሰራተኞችን አግኝተው ለማነጋገር ያቀረቡትን ጥያቄ ችላ ብለው አልፈዋል ተብሏል። በአንድ አጋጣሚም
የአልጀዚራው ጋዜጠኛ መሀመድ ቫል ቃለ መጠይቁን እንዲያቋርጥ አድርገውታው ብለው በስፍራው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል።

ምንጭ ፦ ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሞጆ ሃዋሳ ፈጣን መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ እየተከናወነ ነው፡፡ የመንገዱ ግንባታ 13 ቢሊየን ብር የሚፈጅ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ አለው ተብሏል፡፡

ምንጭ ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት ለሀገር የተከፈሉ መስዋትነቶች የህዝቡን አንድነት የሚያጠናክሩ እንደሆኑ የታሪክ ምሁራን ተናገሩ፡፡ ምሁራኑ የሀገሪቱ ህዝቦች የረዥም ዓመታት ትስስርና የጋራ ባህል እሴቶች ጥበቃ እንደሚያስፈልጋቸውም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! ለ3ኛ ተከታታይ ቀን የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ ተማሪዎችን አላስገባም። ውስጥ ነበሩ ተማሪዎችም ወደ ውጭ ወጥተዋል። ተማሪዎቹ ባደረጉት ስብሰባ ከሚደርስብን ስቃይ እቃችንን ጥለን መሄድ እንመርጣለን በማለት ከነገ ጀምሮ ባዶ እጃቸውን ወደ ቤት ለመሄድ ወስነዋል። ዛሬ ከትምህርት ሚኒስቴር ሰዎች ጋር ስብሰባ ይኖራል ተብሎ ቢጠበቅም ተማሪዎቹን ሊያናግር የመጣ አካል የለም። በርካታ ተማሪዎች ከ2 ቀን በፊት ለብሰው በወጡት ልብስ ነው ያሉት በተለይ ሴት ተማሪዎች ሁኔታውን መቋቋም እንደከበዳቸው እና በተወለዱበት ሀገር ይህን ስቃይ ማየታቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

ምሽቱ ምን እንደሚመስል እየተከታተልኩ መረጃዎችን አደርሳችኃለሁ።

ምንጭ ፦ ካስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1492ኛው የነቢዩ መሀመድ የመውሊድ በዓል ነገ ይከበራል።

የነቢዩ መሀመድ አስተምህሮን ሙስሊሙ ህብረተሰብ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው መልካም ተግባራት በመከወን ሊተገብረው እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ መሀመድ አሚን ጀማል አሳስበዋል፡፡

ነገ የሚከበረውን 1492ኛው የነቢዩ መሀመድ የመውሊድ በዓልን በማስመልከት ባስተላለፉት የእንኳን አደሳችሁ መልዕክት ነቢዩ መሀመድ የመፈቃቀር ፣የመረዳዳት እና የመተሳሰብ አኩሪ እሴቶችን ያስተማሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ እናም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የእሳቸውን አርአያ በመከተል ለወገኑ መልካም ተግባራትን ሊያከናውን እንደሚገባ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል፡፡

በዓሉ ነገ ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ በዋነኛነት በታላቁ አንዋር መስጊድ እንደሚከበር ተገልጿል።

ምንጭ ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሳዑዲ አረብያ በአገሪቱ ሕጋዊ የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸዉ የዉጭ ዜጎችን ወደየሀገራቸዉ መመለስ መጀመሯን መረጃዎች ያመለክታሉ። መኖርያ ፍቃድ ከሌላቸዉ 400,000 ገደማ ኢትዮጵያዊያን ዉስጥ እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት 70,000 መሆናቸዉን ዘገባዎች ጠቁሟል።

ምንጭ ፦ ዶቼ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ የምትገኙ ውድ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ከጎናችሁ እንደሆንን ዛሬም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ንፁ ኢትዮጵያዊነት የሚገለፀው የአንዱን ችግር እንደችግራችን የአንዱን ስቃይ እንደስቃያችን ቆጥረን ስንቀበል ነው። በሀሳብ ከእናተው ጋር ውለን ከናተው ጋር ማደር ከጀመርን ይኸው 3ቀን ሆኖናል። በአለም ላይ የሚገኙ የዚህ ቻናል ተከታዮች ከጎናችሁ ናቸው።

በፈተና የሚፀና የተባረከ ነው !

ህዳር 20/03/2010 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች @tikvahethiopia
ሀረማያ! ከትላንት ጀምሮ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ እንደሆነ ይታወቃል። ተማሪዎቹ ከግቢ ከወጡ በኃላ በሀረማያ ከተማ እና አካባቢው አዳራቸውን አድርገዋል። ከለሊት ጀምሮም ከ20 በላይ በሚሆኑ የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ተማሪዎች ወደየቤታቸው እንደሄዱ ተሰምቷል። ዛሬ ቀኑን ሙሉ ተማሪዎች የጉዞ ትኬት ሲቆርጡ ታይተዋል። ጥቂት ተማሪዎች ደግሞ ድሬዳዋ እና ሀረር በሚገኙ የዘመዶቻቸው ቤት ይገኛሉ።

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በ3ቀን ውስጥ ተማሪዎች ወደ ግቢው ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በማስታወቂያ ቢያሳስብም ማስታወቂያው በተማሪዎች መቀደዱ ነው የተሰማው። ዛሬ እስከ ምሽት ድረስ በግቢ ውስጥ የነበሩ ጥቂት ተማሪዎች እቃቸውን ይዘው ወጥተዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ተማሪዎቹን በነፃ እየመገቡ እና ማደሪያም እየሰጧቸው እንደሆነ በሀረማያ የሚገኝ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታይ ገልጿል።

ምንጭ ፦ M
@tikvahethiopia @tsegabwolde