TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዚምባቡዌ የሮበርት ሙጋቤ የልደት ቀንን ብሄራዊ የወጣቶች በዓል አድርጋ አወጀች።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አይቼ እንዳላየ፤ ሰምቼም እንዳልሰማ ማለፍ አልችልም ምክንያቱም የሰው ህመም የሚያመኝ የሰው ችግር የእኔ ነው ብዬ የምቀበል የሰው ስቃይ የኔም ነው ብዬ የማምን ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነኝ !

እባካችሁ እኔ መረጃዎችን የማጋራው ችግር ሲፈጠር ስለምወድ እልያም ሀገር ስትታመስ፤ ትውልድ ሲጎዳ ማየት ስለምፈልግ አይደለም። እኔ ሀገሬን እወዳለሁ። መረጃዎቹን የማጋራው የሌሎችን ችግር እንደራሳችን እንድናይ ነው። ግማሹ ወዶ ግማሹ ተግዶ ግማሹ ጉዳት እንዳይደርስበት በመፍራት ያላመነበት ነገር ውስጥ የገባ ይኖራል።

እኔ መረጃዎቹን የማጋራው እና የምለቀው የሌላውን ችግር እንደራሳችን እንዲሰማን የሌላው ጭንቀት እንዲያስጨንቀን ምንም መፍጠር ባንችል እንኳን ተግተን እንድንፀልይ ነው።

ከምንም በላይ ሰውነታችን የሚገለፀው ኢትዮጵያዊነታችን የሚንፀባረቀው አንዳችን የሌላችንን ችግር ስንረዳ፤ ህመሙ ሲያመን ፤ውጋቱ ሲወጋን ነው። አይቶ እንዳላየ ሰምቶም እንዳልሰማ ማለፈ ያሳፍራል። እናተ ሰላም ስለሆናችሁ ሌላው ሰላም ነው ማለት አይደለም እናተ ደልቷቹ ስለተማራችሁ ሁሉም ደልቶት እየተማረ ነው ማለት አይደለም።

ውድ ተከታዮቼ የሌላው ህመም ይመመን የሌላው ጭንቀት ይጭነቀን ይህ ሲሆን ነው ሰው መሆናችን ሲቀጥል ኢትዮጵያዊ መሆናችን ማረጋገጫ የሚያገኘው።

ለምን ሰልፍ ወጡ ትላለህ ለምን ይሄን ትፅፋለህ አላማህ ግጭት መቀስቀስ ነው እያላችሁ ዝባዝኬ የምትልኩልኝ ሰዎች ምንም አልላችሁም ፈጣሪ ማስተዋልን እና የሰው ባህሪን እንዲሰጣችሁ ለምንላችኃለሁ።

እኛ ቤት የጎደለን ፍቅር ነው። ፍቅር የሌለበት ቤት ደግሞ ሁሌም ችግር እና መከራ የበዛበት ነው። በልባችን ፍቅር ይንገስ ያንጊዜ ዘራችንን እንረሳለን። በልባችን ፍቅር ይንገስ ያንጊዜ ብሄራችንን ረስተን ስለ ሰውነታችን እናስባለን።

በመላው ዓለም በአሁን ሰዓት የምንሰማው ሁሉ ምናልባት የፈጣሪ ቁጣም ሊሆን ይችላል እና ሙስሊሙም አላህ አላህ እያለ ክርስትያኑም እግዚያብሄር እግዚያብሄር እያለ ይጩኸ።

እንፀልይ ፈጣሪ ሁሉን ይችላል !

ፀጋአብ ወልዴ - ኢትዮጵያ ~ ህዳር 18/03/2010 ዓ.ም.

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ JiT ተማሪዎች ሁሉም ሰላም ማደራቸውን ማረጋገጥ ችያለሁ። ተማሪዎቹ በመስጅድ እና ቤተክርስቲያን እንዲሁም በየሰው ቤት ነው ያደሩት። ዛሬ ደግሞ ምን እንደሚፈጠር አብረን እናያለን። በየሰዓቱ የሚፈጠሩትን ጉዳዮች ለእናተ አደርሳለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከJiT ልብ የሚነካ መልዕክት'በፀሎታችሁ አትርሱን እያሉ ነው ተማሪዎቹ...

"እንዴት አደርክ ጸግሽ እኔ የ jit ተማሪ ነኝ ግን የ አአ ልጅ ነኝ ወደ ቤት እንዳንመለስ መኪናም ተከልክለናል። ትላንት ሙሉ ቀን ከቁርስ በስተቀር በረሀብ ተገርፈን ነው የዋልነው እቺንም ሽሮ ከለከሉን ወላሂ ነው ምልህ በታም ተስፋ እየቆረጥን ነው ያለነው ለሊት ግማሹ መስጊድ ግማሹ ቤተ ክርስቲያን የቀረው ደሞ ጎረቤት ምናምን ለምነው እያደሩ ነው ዛሬ ደሞ ከ ቁርስ ጀምሮ እንደሚቀጡን ነው ሚወራው።

21ኛው ክ/ዘመን ላይ አይደል እንዴ ያለነው የሰው ልጅ እንዴት በረሀብ ይቀጣ? የፈለገ ቢያረክ እኮ እህል አይከለልም አይደል እንዴ? ደሞ እኛ ምንም አላረግንም ውሳኔውን ተቃወምን እንጂ በአሁን ሰዓት ጸግሽ እኛ የ jit ተማሪዎች እጅግ ከፍተኛ የሚባል እንግልት እየደረሰብን ነው።

. ምግብ ተከልክለናል
. ዶርም ተከልክለናል
. በፌደራል እየተደበደብን ነው
. ትራንስፖርት ተከልክለናል
. ተማሪው ለብርድ እና ለጸሀይ ተዳርጉዋል
. ትምርት ሙሉ በሙሉ ተቊርጧል

እኔ እዚ የማውቀው ሰውም ዘመድም የለኝም ምን እንደምሆን አስበው ጅማ ውስጥ ያለው እየመሰለኝ አደልም። በትረፋ ጸግሽ አንተን በጣም አደንቅሀለው ጎብዝልኝ! እባካቹ ህዥብ እንዲያውቀው ምትችሉትን ያክል ጣሩልን። በጸሎታቹ አትርሱን መልካም ቀን ተመኘው!

ቃ~ጅማ ኢትዮጵያ(በጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪ) ህዳር 19/03/2010 ዓ.ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትላንት ለሊቱን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተኙበት በየዶርሙ በራሪ ወረቀቶች ሲበተኑ አድረዋል። በራሪ ወረቀቶቹ ተማሪዎች ከዛሬ 3 ሰዓት ጀምሮ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የሚያሳስቡ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ በሰከነ መንፈስ እንነጋገር ችግሮችን መፍታት እንችላለን ብሏል።

ምንጭ ፦ ኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሺ የሚቆጠሩ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እቃቸውን ይዘው ግቢውን ለቀው ወጡ። ዩኒቨርሲቲው 5 ሰዓት ላይ ስብሰባ ለማድረግ ጥሪ አቅርቦላቸው ነበር።

ምንጭ ፦ ኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopi
ጅማ JiT ! እቃችንን ይዘን ወደ ቤታችን እንዳንሄድ ግቢው አልስገባም ብሎናል አሉ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች። የሚሰማ አካል ካለ ይህን ሰምቶ መፍትሄ ይስጠን በረሀብ ልንሞት ነው ብለዋል። በተለይ ሴት ተማሪዎች ሁኔታውን መቋቋም እንዳቃታቸው ተናግረዋል።

ምንጭ ፦ ተካ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! በትምህርት ሚንስቴር ስር በሚተዳደረው ዩኒቨርሲቲ ሰሚ ያጡት የጅማ ቴክኖሎጂ እንስቲትዩት ተማሪዎች በከተማው አደባባይ ታዩ። ተማሪዎችን ሊያናግር ፍቃደኛ የሆነ የመንግስት አካልም ጠፍቷል። ፎቶዎችን አስደግፌ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዤ እመለሳለሁ።

ምንጭ ፦ እስቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! ገንዘብ የሌላቸው ተማሪዎች በረሀብ ልንሞት ነው እያሉ ይገኛሉ። እቃቸውን ይዘው እንዳይሄዱም ግቢው አሁንም አላስገባም እቃችሁንም አታወጡም ብሏል። የሚሰማ አካል ካለ እንዚህን ወጣት ኢትዮጵያዊያን ያሉበትን ሁኔታ ተርድቶ አስፈላጊውን መፍትሄ እንዲሰጣቸው በ17 ሺ ሰው ስም እለምናለሁ። እባካችሁ እባካችሁ !!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
«ሴቶች አደርጋለሁ፤ እሠራለሁ ብለው ራሳቸውን ያቅርቡ። ራሳቸውን ለአመራርነት ያቅርቡ» የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኾና የተመረጠችው ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያሳዝናል ሀረማያ! ረጅም ኪሎ ሜትር አቆራርጠው ለትምህርት በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የተገኙ ተማሪዎች በተፈጠረው ሁኔታ ግቢው ለቀው ወደየቤታቸው እየሄዱ ነው። ግቢው ለስብሰባ ቢጠራቸውም ስብሰባውን ጥለው ጓዛቸውን ጠቅልለው ሄደዋል። ሁሉም ተማሪ በሚባል ደረጃ ግቢውን ለቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! ትላንት በቀን 18-03-2010 ዓ.ም. እንደድንገት ከግቢ የወጡ የጅማ JiT ተማሪዎች ምግብ ለመመግብ እና ለማደር ተመልሰው ሲመጡ ግቢው በሩን ዘግቶ አላስገባም ካላቸው ይኸው ከ24 ሰዓት በላይ ሆኗል።

ደጋሚ ምዝገባውን የማይመዘገብ ተማሪ ከማንኛውን አይነት መብቶቹ እንደሚታገድ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው ይህንም ተግባራዊ እያደረገው ይመስላል።

በርካታ ተማሪዎች ትላንት በለበሱት ልብስ፣ ሳይበሉ፣ ሳይጠጡ አሁንም ያሉ አሉ። ገንዘብ እንኳን ለማውጣት የባንክ ደብተራቸውን እንኳን ሊያወጡ አልተፈቀደላቸውም። በተለይ ሁኔታው ለሴቶች ከሚገመተው በላይ ከባድ ነው።

ግቢው ሊያናግራቸው ፍቃደኛ ባለመሆኑ ተማሪዎቹ ተሰብስበው የከተማውን ከንቲባ ቢጠይቁም ከአቅም በላይ መሆኑን አስረድተዋቸዋል።

ዛሬ ተማሪዎቹ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር ከቀኑ 9 ሰዓት ስብሰባ እንዳላቸው የተሰማ ሲሆን ቢያንስ ግቢ ገብተው እንዲያድሩ አልያም እቃቸውን ይዘው እንዲወጡ ይጠይቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። የስብሰው ቦታ አቡነ እስጢፋኖስ ህንፃ ነው። ተማሪውም በስብሰባው ላይ እንዲገኝ ጥሪ ቀርቧል።

የዚህ ሁሉ መነሻው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመውጫ ፈተና ይሰረዝ የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ እንደምክንያትነት ያስቀመጡት በቂ የሆነ ነገር በሌለበት የትምህርት ጥራቱም ባልተጠበቀበት 5 ዓመት የተለፋበትን ድግሪ መከልከል ተቀባይነት ስለማይኖረው ነው ብለዋል።

@tsegabwolde @tikavhethiopia
ከ20 በላይ የሀገራት መሪዎች የኬንያውን ፕሬዝደንት በአለ ሹመት ለመሳተፍ ናይሮቢ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናትም በበአለ ሹመቱ ላይ ተካፋይ ናቸው። የተቃዋሚ መሪዎች በአንፃሩ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ አፍሪካ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መደወላቡ ! በግቢ ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች ስብሰባ አድርገው የነበር ሲሆን ዩኒቨርስቲው ዳግም ምዝገባ ወይም Re Register አድርጉ ቢልም አንመዘገብም ጭራሹኑ አንማርም ብለው ከውሳኔ ላይ ደርሰዋል።

👉 ግቢውም ከነገ ረቡዕ ጀምሮ በግቢ ውስጥ የቀሩትን ተማሪዎች እቃቸውን ይዘው እንዲወጡ አዟል።

👉 ከሰኞ ጀምሮ ሩቅ አከባቢ ያሉ ልጆችም መጓዝ ጀምረዋል።

ምንጭ :- Tav

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር በመሆን በግቢ ለማደር ወይም እቃቸውን ለማውጣት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ሙሉ መረጃውን እና ውሳኔውን ከሰዓታት በኃላ አደርሳችኃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንዲታወቅ ! ትላንት በጅማ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ ያደሩ ተማሪዎች አብዛኞቹ ተመራቂ(GC)ናቸው። ጥቂት የሌላ አመት ተማሪዎች ደግሞ በጫካው በኩል የገቡ ሲሆኑ እንዚህም ተማሪዎች የምዝገባውን ፎርም የሞሉ እና የተመዘገቡ አይደሉም። ምሽት ፖሊስ ተማሪዎቹ ቢመዘገቡ ምንም እንደማይሆኑ ሲነግራቸው የቆየ ቢሆንም የተመዘገበ ተማሪ አልነበረም። ምግብም በማጣታቸው ባዶ ሆዳቸውን እንዳደሩ ተናግረዋል። ዛሬ ግን ከግቢ ወጥተው ሌሎቹን ተቀላቅለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ JiT ! ስብሰባው ለውጥ አላመጣም።

ከሰብዓዊ መብት ኮምሽን ጋር የተደረገው ስብሰባ ለውጥ አላመጣም ተባለ። ተማሪው ጥሩ ነገር ይኖራል ብሎ በበር አካባቢ ቢጠብቅም አንድ ተወካይ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመነጋገር አንድም ፈርሞ ትምህርት መቀጠል አልያም በራስ ፍቃድ ትምህርት እንዳቆሙ ፈርሞ እቃ ይዞ መውጣት እንደሚችሉ ተናግሯል። ዛሬም ተማሪዎቹን ዩኒቨርሲቲው አላናገርም በርም አልተከፈተም የትላንት ምሽቱ እጣ እንደሚያጋጥማቸው ተማሪዎቹ ተናግረዋል።

እዛው የሚገኙ ተማሪዎች ተነጋግረው በወሰኑት መሰረትም ምዝገባውን መቼም እንደማያደርጉ ከስምምናት ላይ ደርሰዋል።

ምንጭ ፦ ካስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ጀይላን እና ኡስታዝ ካሚል ለተፈናቀሉ ወገኖች በኦሮሚያ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ሲሄዱ በዛሬው እለት በአወዳይ የተደረገላቸው አቀባበል።

ምንጭ ፦ አብዱረሂም አህመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
ሀረማያ! ይድረስ ምስጋናችን ለባቴ፣ ገንደጄ፣ ስቴሽን ነዋሪዎች በሙሉ የሐረማያ እና አካባቢው ነዋሪዎች በአጠቃላይ ተማሪዎችን በምግብ፣ በገንዘብ፣ በማደሪያ፣ በትራንስፖርት እንዳትቸገሩ በማለት የቤታቸሁን ደጃፍ በመክፈት ምግብ እየሠራችሁ ላበላችሁን እናቶች ፣ ገንዘብ በማሠባሠብ ቀኑን ሙሉ ደከመን ሰለቸን ሳትሉ ተማሪን ስትረዱ ለዋላችሁ ወጣቶች በሙሉ እናመሰግናለን!

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ~ ህዳር 19/03/2010 ዓ.ም.

@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
ያሳዝናል! የጅማ JiT ተማሪዎች ዛሬም ማደሪያ አጥተው በየእምነት ተቋማቱ እንዲሁም ሰዎችን በመለመን በየሰው ቤት ለማደር ተገደዋል። ቤተሰብ ልጆቹን እንዲጠብቅለት ለዩኒቨርሲቲ ሀላፊነት ቢሰጥም ይህን ማድረግ ሳይችል ቀርቷል። ተማሪዎቹ የት እንዳሉ በምን ሁኔታ ላክ እንዳሉ እንኳን ለማወቅ ጥረት አላደረገም። በጣም ያሳዝናል! በነገው እለት የትምህርት ሚኒስቴር ሰዎች ተማሪዎችን ያናግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ተማሪዎች በበኩላቸው ምንም ቢመጣ በፎርሙ ላይ እንደማይፈርሙ የመውጫ ፈተናን በምክንያት እንደሚቃወሙ ገልፀዋል።

እኛ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች እና ችግራችሁን የሰማ መላው ኢትዮጵያዊ በፀሎት ከጎናችሁ ነው።

እኔም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ችግራችሁን እንደ ችግሬ ስቃያችሁን እንደ ስቃዬ ተቀብዬ የናተ ጉዳይ መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ መፃፌን እቀጥላለሁ። ምንም ክፉ ነገር አያጋጥማቹ! ባላችሁበት የፈጣሪ ጥበቃ አይለያችሁ!

ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ~ህዳር 19/03/2010 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia