TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እጅግ አሳዛኝ ዜና!

ዛሬ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ
የተሳተፉ ሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። አንደኛው ሩጫውን ካጠናቀቀ በኋላ ሁለተኛው ሰው ጎተራ አካባቢ እራሳቸው ስተው ወደ ህክምና ተቋም ቢወሰዱም
ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም።

ምንጭ ፦ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርሲ ነጌሌ👇
በአርሲ ነጌሌ ከተማ ከትላንት በስቲያ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ለመገላገል በመሀል የገባ አንድ መምህር በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል። መምህሩም የስነ ዜጋ እና የታሪክ መምህር እንደነበር መረጃዎች ጠቁመዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ብሄር ተኮር ጥቃት እና ግጭት እንዲቀሰቀስ እየተሯሯጡ ያሉ ግለሰቦች እንዳሉ እንዲሁም ብሄር በመምረጥም ቤቶችን ማቃጠላቸውን የአካባቢ ሰዎች ይናገራሉ። በተፈጠረው ሁኔታ አንድ የግል ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ወድሞል። የአካባቢው አባቶችም ችግሮችን በንግግር ለመፍታት እና ስላም እንዲሰፍን ህዝቡን በማረጋጋት ሁኔታዎች ወደ ቀድሞ መልካቸው እንዲመለሱ እየሰሩ ይገኛሉ።

ምንጭ ፦ ሳም,ቴድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታዮች ለእናት ሀገራችን ሰላም፤ ለአለም ሰላም ተግተን እንፀልይ። ፈጣሪ አንድነትን፣ ፍቅርን፣ መረዳዳትን፣ ኢትዮጵያዊነትን፣ ከዘረኝነት ፅዱ መሆንን እንዲያድለን እንለምን። ፈጣሪ ሁሉን ይችላል።

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (JiT) ተማሪዎች የድጋሚ ምዝገባውን ባለማከናወናቸው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ማስታወቁ አይዘነጋም።

ይህ ከላይ የምትመለከቱት ማስታወቂያ ደግሞ በተማሪዎች የተለጠፈ ሲሆን ለጠየቅነው ጥያቄ መልስ ባለማግኘታችን በአንድነት ሆነን ግቢውን ከዛሬ 5 ጀምሮ ለቀን እንወጣለን የሚል ነው።

ምንጭ ፦ ፋሪ,ሙሉ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአምቦ IoT እና በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የዛሬ ጥዋት ትምህርት መቋረጡ ተሰምቷል።

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለጠየቅነው ጥያቄ ምላሽ ካላገኘን ትምህርት አንማርም በማለት ወደ ክፍል ይገቡ ቀርተዋል።

ምንጭ ፦ ሳ,ኤር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእሳት አደጋ ! በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ገርጂ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ 11 የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ መድረሱን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና
መቆጣጠር ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአደጋው ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ15 ደቂቃ አካባቢ ነው የተከሰተው።

በእሳት አደጋውም በንግድ ሱቆቹ ውስጥ የነበሩ ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን አስታውቀዋል።

የባለስልጣኑ ባለሙያዎች እሳቱን ለማጥፋት ባደረጉት ርብርብም 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻላቸውን ነው አቶ ንጋቶ ያስታወቁት።

በእሳት አደጋው የሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ያሉት አቶ ንጋቱ፥ አንድ የባለስልጣኑ ሰራተኛ ግን እሳቱን ለማጥፋት በመስራት ላይ እያለ በአካሉ ላይ ጉዳት እንደደረሰበትም ገልፀዋል።

እሳቱን ለማጥፋትም 24 የባለስልጣኑ ተሽከርካሪዎች በ4 የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪ በመታገዝ 24 ሺህ ሊትር ውሃ ተጠቅመው 2 ሰዓት የፈጃ ስራ መስራታቸውንም አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ ዜና በአዲስ አበባ ከተማ
ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጎፋ መብራት ሀይል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ከ15 ላይ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ የእሳት አደጋ መድረሱንም አቶ ንጋቱ አስታውቀዋል።

በአደጋው 25 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን፥ በ10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን እንደተቻለም ገልፀዋል።

የእሳት አደጋዎቹ መንስኤ እንዳልታወቀ እና እየተጣራ መሆኑንም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ(ታሪክ አዱኛ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች።

ምንጭ ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopi
በአሁኑ ሰዓት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ እና የግብርና ኮሌጅ ተማሪዎች ተቃውሞቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ። በርካታ ተማሪዎች መንገዶችን አጨናንቀዋል። ፌደራል ፖሊስ ተማሪዎችን እያሰረ መሆኑን በቦታው የሚገኙ ተማሪዎች መረጃ አድርሰዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከተማሪዎች ጋር ቀጥተኛ ውይይት ሊያደርግ ይገባል የሚሉ አካላት እየበዙ ነው።

ምንጭ ፦ ኤፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትላንት በተካሄደው 17ኛው ታላቁ ሩጫ የሁለት ሰዎች ህይወት እንዳለፈ አይዘነጋም። ህይወታቸው ያጡት እድሜያቸው 61 ዓመት እና በ40ዎቹ መካከል የሚገኙ ሁለት ሯጮች እንደሆኑ የታላቁ ሩጫ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አየለ ገለፀዋል።

ምንጭ ፦ ዶቼ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን! ጅማ (JiT) የተማሪዎች ካፌ ምሳ ሰዓት ተዘግቷል። አዲሱን መታወቂያ ይህም ማለት ድጋሚ ምዝገባ አድርጎ የሚሰጠውን መታወቂያ ያልያዘ ተማሪ ወደ ግቢ እንዳይገባ ተደርጓል። ድጋሚ ምዝገባ ያላከናወኑ ተማሪዎች ከማንኛውም የግቢ ውስጥ መብቶቻቸው ታግደዋል። መግባት የሚፈልግ ተማሪም ፈርሞ መግባት እንዲችል የግቢው ጥበቃዎች ጋር ፎርም ተቀምጧል። ወደ ግቢው መግባት የፈለጉም ፈርመው እየገቡ ናቸው። ሌላው ከዛ የተሰማው መረጃ 1350 ብር የሚደርስ የወጪ መጋራት ክፍያ ለተመዘገቡ ተማሪዎች ብቻ ይሰጣል ተብሏል።

ቁጥራቸው በርካታ ተማሪዎች ግን አንድ ላይ ሆነን ዕቃችንን ይዘን ከግቢ እንወጣለን እያሉ ይገ ኛሉ። በግቢው ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ቁጥርም አነስተኛ ነው።

ተጨማሪ ጉዳዮችን እየተከታተልኩ አደርሳችኃለሁ። የጅማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ህዝብ ያሉበትን ሁኔታ እንዲያውቀው ለሚያደርሱት ፈጣን መልዕክትም አመሰግናለሁ።

ምንጭ ፦ ኤፊ,ፍሪ
@tsegabwolde @tikvahrthiopia
ይህ ከላይ የምትመለከቱ ምስል በአርሲ ነጌሌ ከተማ የሚገኝ ፍቃደእግዚ የተባለ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። ባለፈው ሳምንት በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ስንት ለሀገር ተስፋ የተጣለባቸው ተማሪዎች የሚመሩበት ነበር።

@tsegabwolde
ለበርካታ አመታት የተደከመበት የፈቃደእግዚ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ14/3/2010 ዓ.ም. ሁለት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ወደመ። ሙሉ በሙሉ የተቃጠሉት ላይብረሪ፣ 3 ላብራቶሪዎች፣ የኮምፒዩተር መማሪያ እና የኮምፒዩተሮች ክፍል፣ ስቶር፣ሪከርድ ክፍል፣ የፀሀፊ ክፍል፣ የር/መምህር ቢሮ፣ስታፍ ሩም ናቸው። ለሀገሬ ከልጅነቴ ጀምሮ ካለምንም እረፍት ደክማያለሁ። ብዙዎች ተሰናክለው እንዳይቀሩ የቅርብ ክትትል በማድረግ ረድቻለሁ። ለውድ ሀገሬ ኢትዮጵያ በሙያዬ መስራት የሚገባኝንን በመስራቴ አይቆጨኝም። ስራዬን ታሪክ ወደፊት ያወሳዋል።

ፍቃደ ደጀኔ~የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር እና ባለቤት (አርሲ ነጌሌ)

ለሀገራችን ለሰሩት መልካም ስራ እናመሰግኖታለን፤ፈጣሪ የድካሞን ዋጋ ይከፍሎታል።

ምንጭ ፦ ሳም,ቃል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🙏1
ጅማ ከምሽቱ 2:00 ' የJiT ተማሪዎች ማደሪያ በማጣታቸው ወደ ቤተክርስቲያን እና የሰዎች ቤት ተጠግተው ለማደር ተገደዋል። በአሁን ሰዓትም በርካታ ተማሪዎች በግቢው መግቢያ በር ተሰልፍው እየተንገላቱ ነው። በስፍራው የሚገኝ የቻናሉ ተከታይ እንደተናገረው በግቢው የሚገኘው ተማሪ 20% የሚያልፍ አይደለም። እነሱም ምግብ ሳይበሉ እንዳሉ ጨምሮ ገልጿል። ከዩኒቨርሲቲው ጋር አለመግባባት ውስጥ የገቡት ተማሪዎች የተዘጋጀውን ፎርም ከመሙላት መሞትን እንደሚመርጡ ገልፀዋል።

ለዚህ ሁሉ መነሻው ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም የቅደመ ምረቃ የትምህርት ዘርፎች እንዲተገበር የደነገገው የመውጫ ፈተና ነው።

ምንጭ ፦ ካስ,ኤፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ JiT ተማሪዎች በሩ አሁንም እንዳልተከፈተ ተናግረዋል። ቁርስ፣ምሳ እና እራት ሳይበሉ ከፍተኛ መንገላታት እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልፀዋል። በረሀቡ ላይ ብርዱ ተደርቦ ሁኔታውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ቃላቸውን ሰጥተዋል። ሴቶችም እየመሸ በሄደ ቁጥር ጥቃት እንዳይደርስባችው እንደሚሰጉ ተናግረዋል። የሚመልከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ድረሱልን ብለዋል!

ይህን መልዕክት ለክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ለማ መገርሳ ማድረስ የምትችሉ እባካችሁ ተማሪዎቹን በዚህ ምሽት ከመንገላታት ታደጓቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲታገዱ ተወሰነ!

የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራሩ ያለበትን ሁኔታ በመገምገም ጥልቀት ያለው የሂስና ግለሂስ መድረክ
እንደከፈተ ይታወቃል፡፡

በድርጅቱ አመራር ዘንድ ከመድረካዊ ተልዕኮ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የታዩ ስር የሰደዱ ድክመቶችን በጥልቀት የገመገመው ማዕከላዊ ኮሚቴው የድክመቱ የከፋ ጫፍ የሆነውን ስራ አስፈጻሚ እንደ አካልም ሆነ እንደ ግለሰብ አባላት በመገምገም የእርምት ዕርምጃዎችን ወስዷል።

የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ👇

1.አቶ አባይ ወልዱ ከስራ አስፈፃሚነት ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ

2. አቶ በየነ መኩሩ ከስራ አስፈፃሚነት ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ

3. ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከማእከላዊ ኮሚቴ እንዲታገዱ ወስኗል።

ምንጭ ፦ ኢቢሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋናው ግቢ ጅማ ! በማጥናት ላይ የነበሩ ተማሪዎች ከላይብረሪ በግፊት በግዴታ እንዲወጡ ተደርገዋል። ወድሞቻችን ወገኖቻችን በብርድ እየተደበደቡ እኛ ማጥናት አንችልም ያሉ ተማሪዎች ደግሞ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን የተማሪዎች ጥያቄ እንዲመልስ ተሰባስበው ለመጠየቅም እያሰቡ እንደሆነ በቦታው የሚገኝ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰው ምልዕክቱን ልኳል። ሁኔታውን ተከታትዬ አደርሳችኃለሁ!

@tikvahethiopia
ጅማ JiT ! ለረጅም ሰዓታት በበር ላይ የነበሩ በርካታ የJiT ተማሪዎች ግቢው አላስገባም አላቸው። ተማሪዎቹም አዳራቸውን በቤተክርስቲያን ለማድረግ ተግደዋል ቁጥራቸው እጅግ ብዙ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

ምንጭ ፦ ደሬ
@tikvahethiopia
ኡሁሩ ኬንያታ ለሁለተኛ እና የመጨረሻው የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ፡፡ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በቃለ መሃላ ስነስርአቱ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከነዚህ መካከልም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከሚገኙት መሪዎች መካከል ናቸው᎓᎓የኢትዮጵያ ልዑክን ጨምሮ የ24 አገራት ከፍተኛ ሹማምንት በበዓለ ሲመቱ ላይ እንደሚገኙም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ ፦ ቢቢሲ አፍሪካ
@tsegabwolde @tikvahethiopia