TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሁን ASTU 👉 ተማሪዎች በአሁኑ ሰዓት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት DR. Lame ጋር ውይይት እያደረጉ ነው። ተማሪዎቹ መንግስት የትምህርት ጥራቱን ሳያሳድግ "laboratory"ሳያሟላ፣በቂ ነገር ሳያመቻችልን ልንፈተን አይገባም እያሉ ነው። ለጥያቄዎቻቸው ትምህርት ሚንስቴር ፈጣን መልስ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል። ምላሽ የማያገኙም ከሆነ ትምህርት እንደማይማሩ ገልፀዋል። አስተዳደሮች ተማሪዎችን ለማስረዳት እና ለማግባባት እየሞከሩ ነው።

ምንጭ ፦ AlA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቱርክ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ቻናሉን ስለተቀላቀላችሁ አመሰግናለሁ!

ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነው!
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ዛሬ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማስተማር ወደ ክፍል የገቡት መምህራን ተማሪዎችን ሳያገኙ ቀርተዋል። ዩኒቨርሲቲው ሁሉም ተማሪ ከዛሬ ጀምሮ በትምህርት ገበታው ላይ እንዲገኝ ብሎ አሳስቦ ነበር። ተማሪዎቹ ለጥያቄያችን መልስ ካላገኘ በአቋማችን እንደ ፀናን እንቆያለን ብለዋል።

@tikvahethiopia
👍3
የትግራይ ጠገዴና የአማራ ጠገዴ በሚባሉ አዋሳኝ ወረዳዎች የነበሩ የወሰን ችግሮች፣ መፈታታቸውን የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ ፦ አቶ ንጉሱ ጥላሁን

@tikvahethiopia @tsegabwolde
የዚምባቡዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን ለቀቁ። የሀገሪቱ ፓርላማ አፈጉባዔ ፕሬዘዳንቱ ስልጣን መልቀቃቸውን ካሳወቁ በኋላ ዚምባቡዌያውያን አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን እየገለጽ ነው።

ሰውየው ላለፉት ድፍን 37 ዓመታት በስልጣን ቆይተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወዳጅዎ ፖስት ካርድ ይስጡ!!
አድራሻ 👇
#1መርካቶ ጣና ገበያ 2ኛ ፎቅ ቁ.58
#2መገናኛ ስለሺ ስህን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቁ.107
👍 facebook.com/Opiacard
Telegram Join https://tttttt.me/opia1
📌የማስታወቂያ ጊዜ📌

ፍፁም ሀገርኛ የሆኑ ፖስት ካርዶችን ያሰሩ። ለወዳጆ ፖስት ካርድ ይስጡ!

የሚሰሩትን አስገራሚ ፖስት ካርዶች በዚህ አድራሻ ተከታተሉ @opia1 @opia1 @opia1

የራሳችን ፊደል፣ቋንቋና ባህል ያለን መስጠትን የምናውቅ የንግስተ ሣባ ውብ ህዝቦች ነን!

@tikvahethiopia
ሰው ሆይ ሟች መሆንህን አትዘንጋ! ቢያንስ ደግ ሰው ሁን፤በጎ ነገር ስራ፤እራስህን አትከምር፤ተቆልለህ አትኩራ።

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ የቀንጥቻ ቀበሌ ነዋሪዎች ትላንት ብዙ ሰው የተሣተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ጥያቄዎቻቸው ከአካባቢ ጥበቃ፣ የልማት ተጠቃሚነትና የሥራ ዕድል ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የባከኑትን የትምህርት ጊዜያትን ለማካካስ ለዚህ ሴሚስተር ቅዳሜን እንደመደበኛ የትምህርት ቀን ልጠቀመው ነው ብሏል። ሌሎች የማካካሻ መንገዶችንም ገልጿል። ማስታወቂያውን ከላይ ያንብቡ👆

ምንጭ ፦ ሄሊ,ሙዳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በባህርዳር ከተማ የሚገነባው የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ የመሬት ጠረጋ ስራው መከናወን ጀመረ፡፡ የፓርኩ የሁለቱም ምእራፎች ግንባታ ሲጠናቀቅ ለ12
ሺህ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው ማስታወቂያ በጥቂት ተማሪዎች ምክንያት የመማር ማስተማር ስርአቱ እየተስተጓጎለ መሆኑን ገልጿል። ተማሪዎችን ድጋሚ ምዝገባ እንዲያደርጉም በጥብቅ አሳስቧል። ድጋሚ ምዝገባውን የማያከናውኑ ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያ እንደማይከፈላቸው፣ ወደ ክፍል ገብተው ትምህርት መከታተል እንደማይችሉ እና ሌሎች እገዳዎች ተጥለዋል። ዛሬ የወጣውን ሙሉ ማስታወቂያ ከላይ ያንብቡ👆

ምንጭ ፦ አቡኪ , ፍሬዘር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፍሪካ ህብረት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የቀድሞውን የዚምባብዌ መሪ ሮበርት ሙጋቤን "ፍርሀት የለሽ የአፍሪካ ልጅ" በማለት አሞካሽቶ ስልጣን
መልቀቃቸውንም በፀጋ እንደተቀበለው ገልፁዋል። ህብረቱ አክሎም የሙጋቤ ስልጣን መልቀቅ የፖለቲካ ብስለታቸውን የሚያሳይ እና ለዚምባብዌ እንደሚያስቡ ያሳያል ብሏል።

ምንጭ ፦ ENF

@tikvahethiopia @tsegabwolde
🥰1
ከዘመኑ የልምድ አዋላጆች ይሰዉረን በተለይ ያለ ቦታቸዉና ያለሙያቸዉ ግራ ገብቷቸዉ ግራ ከሚያጋቡ !! ሞትም የሚያምረዉ በቦታችን ስንሆን ነዉ፡፡ መክሊታችንና ሞያችንን በአግባቡ እንጠቀም፡፡

አሼ ታለንቶች ነን !

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍጥጫው📜 የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፍጥጫ ቀጥሏል። ዩኒቨርሲቲው ትላንት ድጋሚ ምዝገባ እዲያደርጉ በጥብቅ ቢያስጠነቅቅም ተማሪዎቹ በዛው ምሽት ከላይ የምትመለከቱትን ማስታወቂያ ለጥፈዋል። በራሪ ወረቀቶችንም አሰራጭተዋል።

ምንጭ ፦ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኤርትራ በወርቅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ኔቭሰን የተሰኘው የካናዳ ኩባንያ በካናዳ የቀረበበትን የጉልበት ብዝበዛ ክስ በኤርትራ እንዲታይ የጠየቀው ማመልከቻ
ውድቅ ሆነ።

ምንጭ ፦ ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቻናሉ በሴቶች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ በየሚማሩበት ተቋማት እንዲሁም በሚሰሩበት የስራ ቦታ የሚደርስባቸውን በደሎች ማዳላቶች ለብዙሀኑ ማድረስ ይፈልጋል። ስለሆነም አሳማኝ መረጃዎችን እና 100% የተፈጋገጡ በተለይ በራሳቹ ላይ የደረሱ በደሎችን በዚህ አድራሻ ማድረስ ይቻላል @tsegabwolde

እስካሁን ያደረሳችሁ አላቹ ማጣራቶችን እየተደርገ ስለሆነ የምናቀርባቸው ይሆናል።
በህይወት ፈተና ውስጥ መታገል ያለብን እስክንሸነፍ ሳይሆን መኖር እስክናቆም ድረስ መሆን አለበት። ሽንፈት የትግል መጨረሻ ሳይሆን የትግል መማሪያ ነው።

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia